Melo koza woreda Belita health center

Melo koza woreda  Belita health center Health info

23/01/2024
 #መጠንቀቅ ይበጃል ✍️
23/01/2024

#መጠንቀቅ ይበጃል ✍️

መሎ ኮዛ ወረዳ ማይዘሎ ቀበሌ በጤና ሞዴል ምረቃ መረሃ ገብር በደማቅ ሁኔታ ተካህዷል። በፕሮጋራሙ ላይ የተለያዩ የዕውቅና ሽልማት ሥነ-ሥራዓቶችም ተደርጓል።                      ...
10/07/2022

መሎ ኮዛ ወረዳ ማይዘሎ ቀበሌ በጤና ሞዴል ምረቃ መረሃ ገብር በደማቅ ሁኔታ ተካህዷል።

በፕሮጋራሙ ላይ የተለያዩ የዕውቅና ሽልማት ሥነ-ሥራዓቶችም ተደርጓል።

ሐምሌ 2/11/2014 ዓ/ም

በመሎ ኮዛ ወረዳ በቀን 19/10/2014 ዓ.ም / በአንድ ቀን / 10 ቀበሌያት በጤና ምዴል ሆኖ ተመረቀ ።  መሎ ኮዛ ወረዳ  በጤናው ሴክተር የህብረተሰቡን  በየደረጃው አሳታፊ ያደረጉ ተግ...
26/06/2022

በመሎ ኮዛ ወረዳ በቀን 19/10/2014 ዓ.ም / በአንድ ቀን / 10 ቀበሌያት በጤና ምዴል ሆኖ ተመረቀ ።

መሎ ኮዛ ወረዳ በጤናው ሴክተር የህብረተሰቡን በየደረጃው አሳታፊ ያደረጉ ተግባራት ቅድሚያ ለጤና ለማረጋጥ እንደሚያስችል የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋ/አስተዳደር አቶ ኤርሚያስ ወሰኔ አስታውቋል።

አስተዳዳሪው እንደተናገሩት ቀበሌው ሞዴል ሆኖ ሲመረቅ በአራት የሞዴል ቀበሌ መስፈርት መሠረት ሲሆን ማለትም የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት አጠቃቀም 85% በቀበሌው ያሉት ትምህርት ቤቶች በጤና የሞዴል ትምህርት ቤት መስፈርት ከ85% በላይ ነፍሰጡር እናቶች ጠቅላላ 85% በጤና ተቋም መውለዳቸው ፣ ሞዴል ቤተሰብ በ18ቱም የጤና ኤክስቴንሽን ማዕቀፎች 85% በላይ መሆን መቻሉ ተጠቅሷል።

በምርቃቱ ወቅት የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙኔ በትሶ የሆኑት እንደገለፁት አምራች እና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የጤና ጉዳይ ቅድምያ ሰጥተን እንሰራል ብለዋል።

የመሎ ኮዛ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አቶ ጥላሁን ገባራ በተገኙበት በባንካ ቀበሌ እንዳሉትም አስቀድሞ ቀበሌው ሞዴል ለማድረግ አጠቃላይ በቀበሌ ደረጃ ንቅናቄ ማድረግና በወረዳው መንግስት ትኩረት በመስጠት እና አመራሮች በልማት ቡድኑ ስምሪት በመውሰድ ሰፊ ስራዎች ለመስራት ተችሏል።

የፅ/ቤቱ የበሽታ መከላከል ጤና ማጎልበትና የጤና የኤክስቴሽን ፕሮግራም ተጠሪ አቶ ቦጋሌ ቦካቼ መንደር -1 የተገኙት እንዳሉት በዛሬ ዕለት ቀበሌ ሞዴል ሆኖ ሲመረቅ በተለይ በ4 ሞዴል ቀበሌ መስፈርቶች መሰረት ሁሉም የቀበሌው ቤተሰብ ሞዴል እንዲሆን በ18ቱ ጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆች እማወራዎች ላይ ስፍ ርብርብ በማድረግ እንዲመረቁ በመደረጉ ገልጿል።

ሁለተኛ ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ከቅድመ ልየታ ጀምሮ እስከ ወሊድ ያለውን ጊዜ በሰለጠነ ባለሙያ እንዲወልዱ መደረጉ ፤ የቀበሌው አባወራው ሁሉም የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት እና የጎዳና መፀዳጃ ቤቶች በየልማት ቡድኑ ገንብተው በመጠቀማቸው እንዲሁም በቀበሌው ያለው ት/ት ቤት በጤናው የሚጠበቅበትን እስታንዳርድ መሰረት ያሟላ በመሆኑ እነዚህ ተግባራት በጠቅላላ ከ85% በላይ ሆኖ በመገኘቱ ቀበሌው ሞዴል እንዲሆን አሰኝቶታል ብሏል።

አጠቃላይ በጤናው ዘርፍ በመንግስትና በፓርቲ በኩል በ2014 ዓ.ም የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ወደ ግብ ለማድረስና ህዝባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ ሁሉም የወረዳው አመራር እርብርቦሽ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ገባራ ከልብ ምስጋና እያቀረቡ ይህንን በመተጋገዝና አብሮነትን በሁሉም ዘርፍ አጠናክረው እንድቀጥልም ጠይቀዋል ።

የዘገበው መሎ ኮዛ ወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት
ሰኔ 19/2014 ዓ.ም
ላሃ

በመሎ ኮዛ ወረዳ  በልጣ ቀበሌ ጤና ሞዴል  ዕውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ።በመርሀ ግብሩ የተገኙት  አቶ ሰለሞን ስባቱ የላ ከተማ ከንቲባ ፣ ሳምሶን ሻምበል የመሎ ኮዛ ወረዳ ብ/ፓ/ሪ/ዓለም ዘ...
20/06/2022

በመሎ ኮዛ ወረዳ በልጣ ቀበሌ ጤና ሞዴል ዕውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት አቶ ሰለሞን ስባቱ የላ ከተማ ከንቲባ ፣ ሳምሶን ሻምበል የመሎ ኮዛ ወረዳ ብ/ፓ/ሪ/ዓለም ዘርፍ ኃላፊና የመሎ ኮዛ ወረዳ ብ/ፓ/አ/ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገለሡ ጋሻው እንደገለጹት እንደገለፁት ጤናው ዘርፍ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዉ በዚህም መሰረት ሕብረተሰቡ ጤናው በእጃቸው ላይ እንዳለ ቁጥጥር ስርዓት እስከ ጤና ተቋማት ድረስ በተደራጀ መልኩ እየተተገበረ ሲሆን ከጤና ተቋማት በታች ወርዶ ማህበረሰቡ ጋር መድረስ ላይ ክፍተቶች እንዳይታዩ ተናግረዉ እነዚህን ክፍተቶች በመሙላት እንዲሁም ማህበረሰቡን በሕብረተሰብ በጤና ቀጥተኛ ተሳታፊ ለማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የሴቶች ጤና ልማት ሠራዊት ቁልፍ እስትራቴጂ እንደሆነ ገልፀዋል።

አክለዉም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች እና ማህበረሰቡ የጤና ፓኬጆችን በቀላሉ እንዲረዱት የበልጣ ጤና ጣቢያ ደጋፍ ባለሙያዎች ድጋፍ ለማጠናከር ያስችለን ዘንድ ፓኬጆቹ በጤና ኤክስቴንሽን የዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎች ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለፕሮግራሙ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አመራሮች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጤና ባለሞያዎች ልባዊ ምስጋና በማቅረብ ኘሮግራሙን አጠናቀዋል።

✴እንቀጥላለን ወይም እንቀጥላለን ❗❗

ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት
ሰኔ 12/2014 ዓ.ም

ለህብረተሰቡ ኮቪድ -19 መከላከያ  ክትባት  ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ።በ7 ቀን በወረዳችን ለህብረተሰቡ ኮቪድ -19 መከላከያ...
13/06/2022

ለህብረተሰቡ ኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ።

በ7 ቀን በወረዳችን ለህብረተሰቡ ኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ለ35,840 ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ የተጀመረው ዘመቻ 4ኛ ቀኑን አሰቆጥሯል።

እድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋ/አሰተዳደር አስታውቋል፡

የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋ/አስተዳደር በአቶ ኤርሚያስ ወሰኔ የ3ኛ ቀን የክትባት አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ከዕቅድ ስናነጻጽር በቀጣይ ልዩ ትኩረት የሚሹ በመሆኑ በኮቪድ -19 መከላከያ ክትባት ተደራሽ ሊደረጉ የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ አንዲሆኑ የሚያስችል ሥራ መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል።

የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ እንደ ወረዳችን 35,840 ዜጎችን ለመከተብ ከተያዘው እቅድ 16,120 /44.9%\ ሽፋን መከተብ መቻሉን ቀረበው ሪፖርት እየተገመገመ ስሆን ፤ በቀሩት ቀናት ከፍተኛ ርብርብ እንድደረግ አሳስበዋል ።


ከመሎ ኮዛ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት
✴ ሰኔ 5/2014 ዓ.ም

እናቶች ጤና በሁሉም ቀበሌያት ደረጃ የትኩረት አጀንዳ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ ።የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤና አገልግሎትን የማጠናከር የወረዳ ጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አንዱ ከመ...
30/05/2022

እናቶች ጤና በሁሉም ቀበሌያት ደረጃ የትኩረት አጀንዳ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ ።

የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤና አገልግሎትን የማጠናከር የወረዳ ጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አንዱ ከመሆኑም በላይ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ጉልህ ምና እንዳለውም ገልጸዋል ።

በመሎ ኮዛ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ገባራ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎትን የማጠናከር ተግባር በቀጣይነት ይሰራል ብለዋል።

በመሆኑም በወረዳችን በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት የእናቶችን ጤና በማስጠበቅ ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታት የእናቶች ማቆያ በትክክል ከመስራት ፣እርጉዝ እናቶችን ቀድሞ ከመለየትና መዝግቦ ከመያዝ፣ የነፍስ ጡር እናቶች ፎረም ለማዘጋጀት የጋራ ጥረት ያሻል ብለዋል።

ተከታታይነት ያለው የነፍስ ጡር እናቶች ፎረም ከማድረግ፣ አንቡላንስ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የሪፈራል ቅብብሎሽና ለሎች መሰል ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት በማመን የመሎ ኮዛ ወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ባለሙያዎችና የሁሉም ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች በሁሉም ቀበሌያት ከፎረሙ ባሻገር የተለያዩ የምርመራ አገ/ቶችን በመስጠት ላይ ፍጹም ቁርጠኝነት መንፈስ እየተረባረቡ እንደሚገኙ ገልጸዋል ።

በመሆኑም ችግሮቹን በመቅረፍ የእናቶችን ጤና ለማስጠበቅ የጋራ ጥረትና ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም አክለዋል ።

➦ግንቦት 22/2014 ዓ.ም

Address

Melo Laha
Dhaka
BELITA

Telephone

+251941666001

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Melo koza woreda Belita health center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram