Osho Welcome to
Chandra Mohan Jain, Bhagwan Shree Rajneesh, Osho

...ከራስህ ተሞክሮ በመነሣትም ታውቀዋለህ። በስቃይ፣ በእንግልት ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔርን ታስታውሳለህ። ደስተኛ ስትሆን፣ ሕይወትም ፈንጠዝያ ስትሆን ስለፈጣሪ ምንም አትጨነቅም፤ አታስታውስ...
07/11/2022

...ከራስህ ተሞክሮ በመነሣትም ታውቀዋለህ። በስቃይ፣ በእንግልት ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔርን ታስታውሳለህ። ደስተኛ ስትሆን፣ ሕይወትም ፈንጠዝያ ስትሆን ስለፈጣሪ ምንም አትጨነቅም፤ አታስታውስምም። ቀላል ተሞክሮ ነው፤ ለማየት ሳይኮሎጂስት አያስፈልግም። ሁሉም በራሱ ሕይወት ሊያስተውለው ይችላል።

በርግጥ ነገሮች ጥሩ ስሄዱ ወደ ቄስ ሄደህ አታውቅም ነበር። ነገሮች ውብ ሆነው ስሄዱ፣በሕይወትም ስኬታማ ስትሆን፣ ሕይወትም የአበባ ማስቀመጫ ስትሆን፣ ፈጣሪን አላስታወስክም። ሕይወት የብስጭት ቦታ ስትሆን ግን በድንገት እግዚአብሔርን ታስታውሳለህ።
#እግዚአብሔር ማምለጫህ ይሆናል።

👇

አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅ የህሊናህና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ትክክለኛዉን እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክምና!"መቶበመቶ ትክክለኛ ባት...
04/11/2022

አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅ የህሊናህና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ትክክለኛዉን እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክምና!"

መቶበመቶ ትክክለኛ ባትሆን እንኳን መቶበመቶ የሌላ ቅጂ አትሁን!

#ኦሾ

You can view and join right away.

 #የፖለቲካ ቁማርተኞች ጥቅመኛ ፖለቲካን ይፈጥራሉ!!ጥቅመኛ ፖለቲካ በአግባቡ ያልታነፁ ዜጎችን ሲያፈራ፣ ያልታነፁ ዜጎችም የማይስማማ ማህበረሰብ ይሆናሉ። የዚህ አሳዛኝ ውጤት ደግሞ  መፍጠሩ ...
03/11/2022

#የፖለቲካ ቁማርተኞች ጥቅመኛ ፖለቲካን ይፈጥራሉ!!
ጥቅመኛ ፖለቲካ በአግባቡ ያልታነፁ ዜጎችን ሲያፈራ፣ ያልታነፁ ዜጎችም የማይስማማ ማህበረሰብ ይሆናሉ።
የዚህ አሳዛኝ ውጤት ደግሞ
መፍጠሩ ሲሆን ፍፃሜው የአንድ ጉልበተኛ ሽፍታ ቁማሩን አጠቃሎ መብላት ይሆናል።
:
#ኦሾ/Osho/
:
OShO Views

You can view and join right away.

“የፈጣሪ ያለህ … ጭራሽ  #ፍልስፍና የምትማረው የፈላስፎችን መንገድ ለመዋጋት ነው? እንዲህ አይነት ነገር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ የምትል ከሆነ ብር የሚልክልህን ...
03/11/2022

“የፈጣሪ ያለህ … ጭራሽ #ፍልስፍና የምትማረው የፈላስፎችን መንገድ ለመዋጋት ነው? እንዲህ አይነት ነገር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ የምትል ከሆነ ብር የሚልክልህን ፈልግ” አሉኝ፤

እኔም ተዉት አልኳቸው !!!

ከማትሪክ ውጤት በኋላ መላው ቤተሰቤ ተበጠበጠ … ምክንያቱም አንዱ ዶክተር እንድሆን ይፈልጋል፣ አንዱ ሳይንቲስት እንድሆን ይፈልጋል፣ ሌላው መሐንዲስ እንድሆን ይሻል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሙያዎች ሕንድ ውስጥ በጣም የሚያስከብሩ፣ ‘የሚያበሉ’ የሚባሉ ሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሙያዎች ውስጥ ከገባህ #ሃብታም፣ ዝነኛ፣ የተከበርክ ትሆናለህ ነው የሚሉት፡፡

እኔ ግን “የማጠናው ፍልስፍና ነው…” ስላቸው ሁሉም ጮሁ፡፡

“አብደሃል ? የማይሆን ነገር ነው የምታወራው !! ማንም ሰው ሞኝ ካልሆነ በስተቀር ፍልስፍና ላጥና አይልም፡፡ ፍልስፍና ተምረህ ምን ለመሆን ነው ? ስድስት ዓመት ሙሉ ዋጋ የሌለው ነገር እየተማርክ ጊዜህን በከንቱ ልታጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ ብለህ ከንቱ ሆነህ እንዳትቀር፡፡ ተራ ሥራ እንኳ አታገኝም…”

እናም ትክክል ናቸው፡፡

ሕንድ ውስጥ ተራ ለሚባል ሥራ፣ የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ወረቀት ብቻ ለሚጠይቅ የፖስታ አመላላሽነት ሥራ፣ በፍልስፍና የማስተርስ ዲግሪህን፣ ከዩኒቨርሲቲው አንደኛ የወጣህበትን የወርቅ ሜዳሊያህን ብታቀርብ፣ ማንም እሺ ብሎ የሚቀጥርህ የለም፡፡ አዎ … በነዚህ ባቀርብካቸው ነገሮች ሳቢያ እምቢ ትባላለህ !!! ያቀረብካቸው ነገሮች የብቃት ማረጋገጫ ሳይሆኑ #አደገኛ ሰው ነህ ማለት ነው !!! ‘ሆ … ለፖስታ አመላላሽነት ፈላስፋ ቀጥረን ደግሞ እንቃጠል እንዴ…’ ነው የሚሉት !!!

“እድሜ ልክህን ችግር ውስጥ ነው የምትገባው - ብታስብበት ይሻላል” አሉኝ…

“ፈፅሞ #አላስብበትም፡፡ ደግሞ ታውቁኛላችሁ፡፡ እኔ በቀጥታ ነው የማየው፡፡ ምርጫ የሚሉት ነገር እዚህ ውስጥ አይገባም፡፡ ምን ማጥናት እንዳለብኝ እኔው ራሴ ነኝ የማውቀው፡፡

የትኛው ሙያ ያዋጣል አያዋጣም የእኔ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለማኝ ብሆን እንኳ ፍልስፍና ማጥናቴን አልተውም” ስላቸው፣

ምን እንደሚሉ ግራ ገባቸው፡፡

“ቆይ ግን” አሉኝ፣ “ለመሆኑ ለምንድነው ፍልስፍና ለመማር የፈለግከው ?”
“ምክንያቱም መላው ሕይወቴን ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ፡፡ ስለዚህም ስለእነሱ ሁሉንም ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ”

“የፈጣሪ ያለህ…” አሉ፣ “ይሄ ነው ምክንያትህ ? በቃ ? አንድ ሰው የፈላስፎችን ሐሳብ ለመዋጋት በሚል ፍልስፍና እንደሚያጠና አናውቅም ነበር !!! ይሄ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነገር ነው”

“እስከዛሬ ካልሰማችሁት እንግዲህ አሁን ከእኔ ስሙታ … ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ - እድሜ ልኬን፡፡ ለዚህ ደግሞ ፍልስፍና ማጥናት አለብኝ፡፡ የፍልስፍና #የክርክር ስልቶች በጣም ነው የሚጥሙኝ፡፡ ስለዚህም የእያንዳንዱን ፍልስፍና የክርክር ነጥቦች በጥልቀት መመርመር እፈልጋለሁ፡፡

ጠልቄ ማየት እሻለሁ፡፡ ዋንኛ ዓላማዬ ግን ፈላስፎችን መፋለም ነው፡፡ ምክንያቱም ከልምዴ እንዳየሁት አንድም የበራለት (Enlightened) ፈላስፋ የለም፡፡ እንዲሁ ነው በቃላት የሚጫወቱት፤ በአመክንዮ ጅምናስቲክ የሚተጣጠፉት፡፡ መቼም ከአንጎላቸው በላይ ወጥተው አያውቁም፡፡ በአንጎላቸው ትልልቅ ሥራዎች ሰርተዋል - ግን አእምሮ ብቻ ሆነው ቀርተዋል”

ነገር ግን … ያው … እብድ ብጤ መሆኔን ስለሚያውቁ፣ “ለነገሩ እንደዚህ አይነት ነገር እንደምታደርግ የሚጠበቅ ነው” አሉ፡፡

ቢሆንም የቻሉትን ያህል ሞከሩ፡፡

“ጊዜ አለ … እስቲ አስብበት … ዩኒቨርሲቲዎቹ እስኪከፈቱ አንድ ወር ያህል ጊዜ ስላለ አስብበት” አሉኝ፡፡

“አንድ ወርም፣ አንድ ዓመትም፣ አንድ ሕይወትም ለውጥ የለውም - ምክንያቱም እኔ አልመርጥም፡፡ ይህ የእኔ ምርጫ አልባው ኃላፊነቴ (choiceless responsibility) ነው”

ከአጎቶቼ አንዱ እንዲህ አለ [የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነው]፣ “ከእሱ ጋር መነጋገር በጣም ከባድ ነው፡፡ ምንም ትርጉም ያላቸው የማይመስሉ ቃላት ነው የሚጠቀመው፡፡ ምርጫ አልባነት … ኃላፊነት … ንቃተ ሕሊና - እነዚህን ነገሮች ከሕይወት ጋር ምን ያገናኛቸዋል ? እንዴ … ገንዘብ ያስፈልግሃል፣ ቤት ያስፈልግሃል - #ቤተሰብ መስርተህ ቤተሰብህን መደገፍ አለብህ”
“ቤተሰብ አልመሰርትም፤ ቤትም አይኖረኝም፣ ማንንም አልደግፍም” አልኩት፡፡

እናም ማንንም አልደግፍም፤ ቤትም አልሰራሁም፡፡ የዓለማችን የመጨረሻው ደሃ ሰው ማለት እኔ ነኝ፡፡

ዶክተር፣ ኢንጂነር ወይም ሳይንቲስት ሊያደርጉኝ ሞክረው ስላልተሳካላቸው በጣም ተናደዱ፡፡

እናም ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፤ “ፍልስፍና የምታጠና ከሆነ ገንዘብ አንልክልህም” አሉኝ፡፡
“እንዲህ ማለትም አይጠበቅባችሁም፡፡ እኔም ራሴ አልቀበላችሁም፡፡ #ምክንያቱም የምማረው ራሴ የመረጥኩትን አይደለ ? ስለዚህ ራሴው እወጣዋለሁ፡፡ እናንተ ተማር ያላችሁኝን አልመረጥኩም፡፡ ስለዚህ ከእናንተ ገንዘብ መቀበል የማይታሰብ ነው፡፡ ለምን ብዬ ነው ገንዘብ ከእናንተ የምቀበለው ? ለምን ብዬ ? ብትሰጡኝም አልቀበልም” ስላቸው፣
ክው አሉ…

እንዴት ብሎ ይችለዋል ብለው ነበር - እኔ ግን ቻልኩት፡፡ ለሊት ጋዜጣ ላይ አዘጋጅ ሆኜ እሰራለሁ፡፡ ቀን ዩኒቨርሲቲ እማራለሁ፡፡ በዚህ መሃል ባገኘሁት አጋጣሚ እተኛለሁ፡፡
በስተመጨረሻ #ጥፋተኝነት ተሰማቸው፡፡ አባቴ፣ “እባክህን ይቅርታ አድርግልንና የላክንልህን ገንዘብ ተቀበል” እያለ ይፅፍልኛል፡፡

በፖስታ ቤት የሚልኩልኝን የገንዘብ ማዘዣ መልሼ እልክላቸዋል፡፡ አንድ ቀን አባቴ ዩኒቨርሲቲ ድረስ መጥቶ፣ “ይቅርታ አታደርግልንም ? እባክህን ሁሉን ነገር እርሳው” አለኝ፡፡

“ይቅር ልል እችላለሁ፡፡ ግን መቼም አልረሳውም” አልኩት፣ “ምክንያቱም በገንዘብ አስገድዳችሁ የማልፈልገውን ትምህርት እንድማር ልታደርጉኝ ሞክራችኋል…” ለእነሱ ገንዘብ ትልቅ ነገር ነው፡፡

“ከእኔ ይልቅ ገንዘባችሁ ነው ያሳሰባችሁ፡፡ እናም አስፈራራችሁኝ፡፡ ከእናንተ ገንዘብ አልፈልግም፡፡ እዛው ያዙት ብራችሁን፡፡ እኔ በደምብ እየኖርኩ ነው”
አባቴ ገንዘቡን የማትቀበለኝ ከሆነ ከዚህ አልሄድም አለ፡፡

በእኔ ምክንያት ማንም ሰው ጥፋተኛነት እንዲሰማው ስለማልፈልግ ገንዘቡን ተቀበልኩት፡፡

Source: Osho
#ኦሾ and please

“እነሆ ሁላችሁም ባላችሁበት ከዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ማዕረግ አንደኛ ወጥተሃል ብላችሁ የሰጣችሁኝን የወርቅ ሜዳሊያ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ እጨምረዋለሁ፡፡ ማንም ሰው እንዲቀናብኝ አልፈልግም፡፡ ይ...
02/11/2022

“እነሆ ሁላችሁም ባላችሁበት ከዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ማዕረግ አንደኛ ወጥተሃል ብላችሁ የሰጣችሁኝን የወርቅ ሜዳሊያ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ እጨምረዋለሁ፡፡ ማንም ሰው እንዲቀናብኝ አልፈልግም፡፡ ይኸው፡ የወርቅ ሜዳልያውን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጨመርኩት፡፡
ከዚህ በኋላ እኔ ማንም ነኝ፤ ማንም ሊቀናብኝ አይችልም፡፡ ቅናት የሚፈለፈለው ከማወዳደር ነው፡፡ ማንም ከማንም አይበላለጥም፡፡ ሁሉም ሰው በራሱ ሙሉዕ ነው፡፡ አንዱ በሆነ መስክ ከሌሎች ሊሻል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ በሌላ መስክ ልቆ ይገኛል፡፡
ይሄ ደግሞ ሰዎች የተለያየን መሆናችንን ነው የሚያሳየው፤ ውድድር እዚህ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ማንም ነኝ፡፡ ማንም ሊቀናብኝ አይችልም፡፡ የወርቅ ሜዳሊያውን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ጨምሬዋለሁ - አበቃ”

#ኦሾ፣ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት በአንዲት ማለዳ ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ማዕረግ አንደኛ በመውጣት የተሰጠውን የወርቅ ሜዳሊያ መላው የዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰሮችና ተመራቂ ተማሪዎች በተገኙበት የዩኒቨርሲቲው የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ሲጨምር የተናገረው…

and 🙏

You can view and join right away.

01/11/2022

#ቅናት ውድድር ወይም ንጽጽር ነው፡፡ እንድናወዳደር እና እንድናነጻጽር ተምረናል፡፡ ሁሌም እንድናነጻጽር ተገርተናል፡፡
👉 አንድ ሰው የተሻለ ቤት አለው፡፡
👉 አንድ የሆነ ሰው ያማረ አካል አለው፡፡
👉 አንድ ሌላ ሰው ብዙ ገንዘብ አለው፡፡
👉 አንድ ሰው ማራኪ ስብእና አለው።
ራሳችሁን ከአላፊ አግዳሚው ጋር አነጻጽሩ እናም ታላቅ ቅናት የሚያንሰራራ ይሆናል፡፡
ቅናት የንጽጽር ውጤት ነው፡፡ ንጽጽርን እና ውድድርን የምታስወግዱ ከሆነ ቅናት ይጠፋል። ከዚያም ራሳችሁን እንደሆናችሁት ብቻ ታውቁታላችሁ፡፡

እናንተ ማንንም አይደላችሁም፡፡ ማንንም መሆን አያስፈልጋችሁም። #ውድድር እና #ንጽጽር በጣም ቂላቂል አመላካከት ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው ልዩ እና የማይነጻጸር በመሆኑ ነው፡፡

ይህ ግንዛቤ አንድ ጊዜ በውስጣችሁ ከሰፈነ ቅናት ይጠፋል፡፡
እያንዳንዱ ሰው ልዩ እና የማይወዳደር ነው። እናንተ ራሳችሁን ብቻ ናችሁ። ማንም ፈጽሞ እናንተን አይመስልም፡፡
እናንተም ፈጽሞ ማንንም መምሰል አትችሉም።

#ኦሾ

Please and

https://t.me/EthioOsho

የህይወት ጣእሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤ በየእለቱ ተመሳሳይ ሕይወት የሚኖሩና በሕይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች አሉ። |ሕይወትን በማሰብ ( በአእምሮ ) ብቻ የሚኖሯት...
31/10/2022

የህይወት ጣእሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤ በየእለቱ ተመሳሳይ ሕይወት የሚኖሩና በሕይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች አሉ። |
ሕይወትን በማሰብ ( በአእምሮ ) ብቻ የሚኖሯት ሰዎች ሕይወት ትርጉም አልባ ሆናባቸዋለች። ኦሾ የምዕራባውያንን ፈላስፎች የሚከሳቸው አንደኛው በዚህ ነው ፣ "ሕይወትን በአእምሮ ተግባራት ብቻ በመሙላት አሰልቺ ያደረጉ ፤ የልብ ቋንቋ የማይገባቸው ፤" ይላቸዋል።
ህይወትን በአእምሮ ሳይሆን በልብ ኑሯት ፤ ህይወታችሁን በልባችሁ ቋንቋ ስትመሯት አእምሯችሁ ታላቅ ተፈጥሮውን ያሳያችኋል፡፡ በአእምሯችሁ ስትኖሩ ፖለቲከኛ ፣ ዘረኛ ፣ አክራሪ ... ወዘተ ትሆናላችሁ ፤ በልባችሁ ስትኖሩ ግን መንፈሳዊ ትሆናላችሁ። በልባችሁ ስትኖሩ የህይወት ጣዕሙ ይገባችኋል፤ የፍቅር ሙቀቱ ይሰማችኋል፡፡
ተልእኳችሁን ስታቁና በተሰጥኦዋችሁ ስትኖሩ የሕይወታችሁ ገዢ ሀይል ከልባችሁ ይመነጫል፤ አእምሯችሁም የልባችሁ ታዛዥ ይሆናል፡፡ ሴቶች ከወንዶች የሚበልጡትና ከወንዶች ይልቅ ደስተኞች የሆኑት ለዚህ ነው፤ ወንድ ሕይወቱን የሚዘውረው በአእምሮው ሲሆን ፣ የሴቷን ሕይወት የሚዘውረው ግን ልቧ ነው፡፡
ከአእምሮ ሎጂክና ምክንያት ሲወጣ ፣ ከልብ ግን ፍቅር ይወጣል። ሎጂክና ምክንያት ብዙ ነገሮችን ትርጉም አልባ እና አሰልቺ ሲያደርጋቸው፤ ፍቅር ግን እያንዳንዱን የሕይወት ስንጣሪ በትርጉም የተሞላችና አስደሳች ያደርጋታል።

Please and
https://t.me/EthioOsho

"ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው!"             ❤         ❤        ❤ #በፍቅር በተሞላ ልብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው።የፍቅር አመለካከት ሁላችንም ውስጥ ሊኖ...
25/10/2022

"ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው!"
❤ ❤ ❤
#በፍቅር በተሞላ ልብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው።የፍቅር አመለካከት ሁላችንም ውስጥ ሊኖር ይገባል።ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው፤በፍቅር ልብ ውስጥ ጥልቅ የደስታ ስሜት ይኖራል።ትንሽ ፍቅር ለሰው ከለገሷችሁ በኃላ የሚሰማችሁ የሀሴት ስሜት አስተውላችሁ ታውቁታላችሁ?
መስፈርት በሌለው ፍቅር(unconditional love) ወስጥ ሆናችሁ የሚኖረውን ሰላም አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?
ንፁህ ፍቅር ሊኖር የሚችለው በምክንያቶችና በመሥፈርቶች ካልታጀበ ብቻ ነው፤በሁኔታ የሚወሰን ፍቅር (conditional love) #ፍቅር አይደለም የማታውቁትን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት ፈገግታውን ተመልክታችሁ የሚሰማችሁን ደስታ አስተውላችሁታል?
የወደቀን ስታነሱ የደከመን ስትረዱ የታመመን አበባ ስታበረክቱና ስጠይቁ የሚሰማችሁ የደስታ ስሜት ወሰን የለውም፤ ይህን የምታደርጉት አባታችሁ ወይም እናታችሁ ስለሆኑ አይደለም በሰውነት የምታበረክቱት ስጦታ ለእናንተ በተራው ታላቅ ደስታና እርካታና ስለሚያበረክት እንጂ።ለዚህም ነው ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው የምላችሁ።

#ኦሾ

https://t.me/EthioOsho

https://t.me/Ethio_Osho_group
https://t.me/Ethio_Osho_group

 #ማወዳደር ታላቁ በሽታ✦✦✦//✦✦✦//✦✦✦ማወዳደር በሽታ ነው።ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ በሽታ።እናትህ ከሌሎች ልጆቿ ጋር ታወዳድራሃለች፤አባትህ አስተማሪህ ሁሉም ያወዳድሩሃል።እየው እሱን እንዴ...
24/10/2022

#ማወዳደር ታላቁ በሽታ
✦✦✦//✦✦✦//✦✦✦
ማወዳደር በሽታ ነው።ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ በሽታ።
እናትህ ከሌሎች ልጆቿ ጋር ታወዳድራሃለች፤አባትህ አስተማሪህ ሁሉም ያወዳድሩሃል።እየው እሱን እንዴት እንደተሳካለት አንተ ግን ምንም ዋጋ የለህም ይልሃል።
#ከመጀመርያ ጀምሮ እራስህን ከሌሎች ጋር እንድታወዳድር ነው የምነግርህ። ይህ ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ ነው። እኔ እኔ ነኝ አንተ ደግሞ ራስህ ነሀ በቃ።
ማንጎና ፖምን ታወዳድራለህ?አታወዳድርም።
እያንዳንዱ ሰው ፍጹም የተለየ ነው።ስለዚህ ማወዳደር የሚባል ነገር ሊታሰብ አይገባም።
#ኦሾ

https://t.me/EthioOsho

https://t.me/Ethio_Osho_group
https://t.me/Ethio_Osho_group

ከጨለማ ባሻገር የብርሃን ፀዳል አለ✨"እስቲ ትንሽ ስለራሳችን እንማማር ሰዎች ከህይታችሁ ሊወጡ ሲያስብ መጀመሪያ የሚሰማችሁን ነገሮችን እንደገና የናንተን ድክመት ነቅሰው በማውጣት እና አስፍተ...
24/10/2022

ከጨለማ ባሻገር የብርሃን ፀዳል አለ✨

"እስቲ ትንሽ ስለራሳችን እንማማር ሰዎች ከህይታችሁ ሊወጡ ሲያስብ መጀመሪያ የሚሰማችሁን ነገሮችን እንደገና የናንተን ድክመት ነቅሰው በማውጣት እና አስፍተው በመተንተን ነገሮች ሁሉ ፤ እንዳከተመላቹ ተስፋም እንደሌላቹህ በቀጥታም ይሁን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይነግሯቹሀል ። ደስ የማይል ስሜት እንዱሰማቹህ የደርጋሉ ፤ እናንተ ግን ይህን ስሜት በተቃራኒው ማየት አለባችሁ ፤ የሚሰማቹህን ያንን ስሜት አትፍሩት ። የቻላቹሁትን ያህል እዘኑ ። ነገር ግን በውስጥ ህሊናቹህ ነገሮች እንደሚያልፍ የሚነግራቹህን ጥቂት ጥንካሬ በውስጣቹህ ያዙት ። ስሜቱ ተመላልሶ ተመላልሶ ይመጣል ። እናም እራሱን ይገልፅ ዘንድ ፍቀዱለት እንደ ጥንካርያቹህ መጠን ጊዜው አንድ ቀን አንድ ሳምንት አንድ ወር አንድ አመት ሊወስድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከሩቅ የብርሃን ፀዳል ሲወጣ ታያላቹህ ። በርግጥ ሁሉም ነገር መጨረሻ ላይ መልካም ይሆናል ። ተዛንፎ የሚቀር ፤ ወድቆ የማይነሳ ሰው ተስፋ የቆረጠ ብቻ ነው ።

#ኦሾ

https://t.me/EthioOsho

https://t.me/Ethio_Osho_group
https://t.me/Ethio_Osho_group

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Osho posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category