18/09/2025
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ግልፅ ምልክት ሳያሳዩ ለብዙ አመት በመቆየት ለከባድ የጤና ችግር ሊዳርጉን እንደሚችሉ ይውቃሉ?
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ በጣም የተለያዩ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ያሉ ሲሆን የተለመዱትና በብዛት ከሚገኙት ዉስጥ ወስፋት፣ የመንጠቆ ትል፣ ጊኒ ትል ፣ ስተሮንግሎይድስ፣ የኮሶ ትል፣ ጃርድያ እና አሜባ ይገኛሉ
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነታችን የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫና በተበከለ ዉሃና ምግብ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ በመራባት የህመም ስሜቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ
✔ ምልክቶች
◈ የአንጀት ስርዓት ለዉጥ መኖር (የሆድ ድርቀት፣ ተቅማጥ ወይም ልል ሰገራ)
◈ የምግብ ፍላጎት መለወጥ
◈ ማቅለሽለሽና ማስመለስ
◈ የሆድ ህመም
◈ አንጀት ዉስጥ ከነበሩና ከአንጀት ዉጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች ከተሰራጩ ህመሙ ከአንጀት ዉጪ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል እንዲከሰት ያደርጋሉ
◈ ጉንፋን መሰል የህመም ምልክቶች፣ የሆድ መነፋትና ጋዝ መብዛት፣ በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት፣በፊንጥጣ ዙሪያ ማሳከክና የመሳሰሉት ናቸዉ
✔ መንስኤዎች
◈ በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
◈ የተበከለ ዉሃ
◈ ቆሻሻ የእጅ ጣቶች ጥፍር በአግባቡ ለመቆረጥ
◈ በደንብ ያልበሰለ/ ያልተቀቀለ/ ለብ ለብ የተደረገ ስጋ መመገብ
◈ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ባህሪይ መኖር
◈ እንደ መንጠቆ ትል ያሉ የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በባዶ እግር የምንሄድ ከሆነ ትሉ የእግር ቆዳን በስቶ ወደ ሰዉነታችን ይገባል
◈ የግል ንፅህና አጠባበቅ አነስተኛ መሆን
◈ የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ መሆን
◈ በጥገኛ ትላትሎች የተያዘ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
✔ የመከላከያ መንገዶች
◈ ሁሉንም አትክልትና ፍራፍሬዎች ከመመገብዎ በፊት በደንብ ማጠብ
◈ ከመመገብዎ በፊት ምግብዎን በደንብ ማብሰል ፓራሳይቶችን ለመግደል ይረዳል
◈ ፈልቶ የቀዘቀዘ አልያም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
◈ የግልና የአካባቢ ንፅህ መጠበቅ
◈ ከመመገብዎ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅዎን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ/ካጫወቱ በኃላ እጅዎን በደንብ መታጠብ
✔ ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚደረገዉ ህክምና እንደጥገኛ ትላትሉ አይነት የሚለያይ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎን በማማከር አስፈላጊዉን ህክምና ማግኘት ይገባል
ተገቢውን ህክምና ሳያገኝ የቆየ የሆድ ትላትል እስከ ሞት ሊያደርሱ የሚችሉ የውስጥ የሰውነት አካላት ጉዳቶች እና የጤና ችግሮችን ሊፈጥር ይችላል