11/09/2025
አንዲት አሜሪካዊ ሴት በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ማርቼዲስ በአንድ ዶላር እንደምትሸጥ ማስታወቂያ አወጣች። ይህን ያየ ሁሉም ሰው ማስታወቂያውን እንደቀልድ ነበር ያሰቡት። ነገር ግን አንድ ሽማግሌ ደውሎ እድሉን ሞከረና አገኛት። እና መኪናውን ከሞተሩ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ቢፈትሸው ምንም እንከን ሊያገኝበት አልቻለም። በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ማርቼዲስ ነው፡፡
ሽማግሌው፦"የመጨረሻ ዋጋ ስንት ትያለሽ?"
ሴትየዋ፦"ማስታወቂያው ላይ እንዳወጣውት በአንድ ዶላርመውሰድ ትችላለህ"
ሽማግሌው አንድ ዶላር ሰጥቶ መኪናውን ተቀበላት። ቢሆንም በሆነው ነገር ተገርሟል። እና ወደሴትየዋ ተመልሶ ጠየቃት፦“የምር ግን ይህ በሚልየን ዶላር የሚያወጣ መኪናን በአንድ ዶላር ብቻ ለመሸጥ መነሳሳትሽ ግርምትና ጥያቄ ጭሮብኛል። ቆይለምንድነው በዚህ ዋጋ የሸጥሽው?"
ሴትየዋ፦"የባሌን ፍላጎት ለማስፈጸም"
ሽማግሌው፦“ባለቤትሽ መኪናው በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ ፈልጎ ነበር?"
ሴትየዋ፦“አይ አልፈለግም፡፡ ምን መሰለህ ባለቤቴ ከአንዲት ፀሃፊ ጋር በድብቅ የፍቅር ግንኙነት ነበረው፡፡ እና ከመሞቱ በፊት በኑዛዜው ላይ ይህን ማርቼዲስ መኪና ሽጬ ገንዘቡን ሙሉ ለሙሉ ለፀሃፊዋ እንድሰጣት ተናዟል፤ እኔ ደግሞ በተፈጥሮዬ አደራ በል አይደለውም!"
ያ መሐመድ ጀማል