
08/06/2022
✍️ ጓደኝነት የሰው ልጅ ከሌላው መጣበቅ የመፈልግ ተፈጥሮአዊ መገለጫ፣ ከራስ ሲሸሹ የሚያገኙት መጠጊያ፣ ከአብሮ መኖር ጭቆና የአፍታ ነጻነት ማግኛ፣ ብሶትን በቀልድ ማምለጫ፣ ችግርን በድጋፍ መውጫ መሆኑን ለማወቅ የኚህ አራት ሴቶች ጓደኝነት ጥሩ ምስክር ነው።
“አየሽ እዚህ ደሳሳ ሻይ ቤት እስጥ መምጣት ከተቀበልሽ የሚያፈስ ሽንት ቤት ያለበት ሆስፒታል ውስጥ ኢንፌክሽንን ማከም ይቻላል ከአልሽ የሚያፈስ ክፍል ውስጥ አስተምራለው ከአልሽ ሰባራ ወምበሩን ተቀምጠሽበታል ማለት ነው”…”ሰባራ ወንበሩን መጸየፍሽ ጥሩ ነው። ባትጸየፊው ነው ሊደንቅ የሚገባው ካልተጸየፍሺው ልቀይሪው አትሞክሪም።”ህክምና መታደል ነው። ቤትኛውም አጋጣሚ ከታመመ ሰው ፊት ስትቆሙ ምን ያህል የታደላቹ መሆናችሁን አትርሱ የታመማቹት እናንተ ባለመሆናቹ ብቻ ሳይሆን ለመፍትሄ የተመረጣችሁ እናተ በመሆናቹ”
“ህክምና መታደል ነው። ሰው የደበቀውን ሚስጥሩን፣ ህመሙን፣ ብሶቱን ፣ጭንቀቱንና ደስታውን ከማንኛውም በላይ ህይወቱን አሳልፎ በጃቹ ውስጥ የሚያኖርበት ስለሆነ”
“ህክምና እዳም ነው። በእምነት የተቀበሉትን የሰው ህይወት በአግባቡ የመንከባከብና የመጠበቅ ሲሆን በተሻለ አሊያም በነበረበት መልክ ማቆየትና መመለስ ስለሆነ”
“ህክምና መስዋትም ነው። ጎዳኝ ብለህ የማትሸሸው ከፋኝ ብለህ የማትተወው ተቸገርኩ ብለህ የማትሸጠው ምክኒያት የለሽ መሰዋት ነው። ንጹህ መሰዋትነት በጎ ስለሆነ ብቻ የምታደርገው”
“ህክምና መጠራትና መመረጥ ነው። በሰው መኖርና አለመኖር መሃል ከውልደት እስከሞት በደስታና በመከራ በተሞላ ህይወት ወስጥ የፈጣሪን የመፍጠር የማኖር የማሳመም የማጥፋት ፍላጎት ተባባሪ መሆን።
በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው፤ ረሀብ የለም፡፡ በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው፤ ብርድ የለም፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም፡፡ መስራትም የለም፡፡ በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል፡፡ መተንፈስ ግድ ይላል፡፡ ረሀብን ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን፡፡ ይበርደናል፤ ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን፡፡ ለመኖር፡፡ አለበለዚያ መኖር የለም፡፡ መታፈን፣ በረሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሀታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ፡፡ በእናታችን ማህፀን የምናውቀው መኖርን ብቻነው፡፡ መወለድ አለመኖርን አመላካች ነው፡፡”
✍️ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ አለመኖር
"መልካም የጓደኝነት ቀን♥"