ጤና ለአዳም

ጤና ለአዳም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጤና ለአዳም, Adiss Abeba, Addis Ababa.

22/08/2025
👉 አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር እንደተፈታ ወደ አያቶቹ ቤት ለጥየቃ እየተጓዘ እያለ ይመሽበትና ሰው ቤት ለማደር ፈልጎ የአንድን ሰው ቤት ያንኳኳል...
12/08/2025

👉 አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር እንደተፈታ ወደ አያቶቹ ቤት ለጥየቃ እየተጓዘ እያለ ይመሽበትና ሰው ቤት ለማደር ፈልጎ የአንድን ሰው ቤት ያንኳኳል ሰውየው ሲከፍት ልጁ እባካቹ ተጓዥ መንገደኛ ነኝ እንድታሳድሩኝ ስል በፈጣሪ ስም እለምናልው ሲል ጠየቀ ሰውየው በለሰለሰ ድምፅ ይቅርታ አምኜ ላሳድርህ አልችልም ሴት ልጅ አለችኝ ይለውና በሩን ይዘጋል ።ሁለተኛውም ቤት ሄዶ ጠየቀ ተመሳሳይ መልስ ሰጠው እና በሩን ዘጋ። ሶስተኛው ቤት አንኳኩቶ ሲጠይቅ ግባ ብለው አስገብተው እራት አበሉት ልጁ ማሰብ ጀመረ ወንድ ልጅ ቢኖራቸው ነው ብሎ አሰበ ግን ወደ ማደሪያው ሲሄድ ቆንጂዬ ሴት ልጅ ተኝታለች። ሰውየው ያረገውን ኮፍያ አውልቆ መሃላቸው ላይ አስቀምጦ ማንም ወደ ማንም እንዳይጠጋ አለና ልጁን አምንሀለው ብሎ ኩራዙን አጥፍቶላቸው ይተኛሉ።

👉 ልጁ በመደነቅ ምንም ሳያቀኝ እንዴት አመነኝ ብሎ እንቅልፍ ሳይወስደው አደረ በጠዋት ሊሄድ ሲወጣ ምግብ ቋጥረው ሰጡት። ልጁ ከግቢው እንደወጣ ልጂትዋ በረንዳ ላይ ሆና ስታየው ተመለከተ ። ገብቶ ሰላም እንዳይላት በሩ ተዘግቷል አጥሩ ላይ ሆኖ ቆይ መጥቼ ሰላም ልበልሽ ሲል ልጂቱ ያባቴን ኮፍያ ያልዘለልክ ልጅ አሁን አጥር ልትዘል ነው ብላ አሾፈችበትና ሄዳ በሩን ከፈተችለት። ልጁም ፀጉርዋን እየዳበሰ እምነት ትልቅ እስር ቤት ነው እምነትን ስትቀበይ መንቀሳቀስ አትችይም እኔ ብዙ ጊዜ ታስሬ አቃለው ግን ምንም አይመስለኝም የእምነት እስር ቤት ግን ከምንም በላይ ትልቅ ነው አላት ይባላል። እና አምነሀት ወይም አምነሺው ከጎዳሽ አትበሳጪ(ጭ) የጎዳህ ሰው እድሜ ልክ ፀፀት ይሆንበታል።

03/08/2025

ተኮርጆ የተኮረጀ
ባለቤቴ በለሊት ቀሰቀሰችኝ።
«አንተ ተነስ! ተነስ ብዬሃለሁ ተነስ!»

ደንግጬ ተነሳሁ «ምን ሆንሽ?»

«ይሰማሃል?»

«ምኑ?»

«ድምፁ ነዋ! ሌባ ገብቷል መሰለኝ» አለችኝ እየተርበተበተች ...

«እና ምን ያስፈራሻል? የሚዘረፍ እቃ እንደሁ የለን» አልኳት ሌባውን እንዳልረብሸው ድምፄን ቀነስ አድርጌ።

አበደች! «አንተ ወንድ አይደለህ እንዴ? እንዴት ሌባ ገብቶ ተጠቅልለህ ትተኛለህ? » ዘራፍ አለች!

ሌባው የሚሰረቅ ስላጣ ተበሳጭቶ ነው መሰለኝ ሳሎን ውስጥ ያሉትን እቃዎች እያተረማመሰ ነው። የሚሰባበሩ ብርጭቆዎች ድምፅ ስትሰማ ባለቤቴ

«አረ ስለፈጠረህ ተነስተህ ይሄን ሌባ ልክ አስገባው!»

«እኔ የማይጠቅም ጠብ ውስጥ አልገባም። አርፈሽ ተኚ» አልኳት።

«ማለት?» አለች በንቀት እያየችኝ።

«ሌባው የመጣው ቸግሮት ነው እንጂ ከኔጋ የግል ጠብ ኖሮት አይደለም። ከርሱ በላይ ችግረኛ እንደሆንን ሲያውቅ የተሳሳተ ቤት ውስጥ እንደገባ ይረዳና ጥሎን ይሄዳል።

አስቢው እስቲ ማሬ ... ገንዘብ የለን። ከተሸራረፉ ብርጭቆዎች ውጪ ደህና እቃ የለን ታዲያ ለምኔ ብዬ ከሌባ ጋር ልፋለም?»

«ክብራችንስ?» አለችኝ ...

«ሂሂሂ ... ክብር አልሽኝ? ደሃ ምን ክብር አለው ደሞ ማሬ? ኑሮ ችጋር የሚሉት ሪንግ ውስጥ ከትቶ ሲደበድበው የኖረ ሰው ምን ክብር አለው? ይልቅስ እኛንም ከሰው ቆጥሮ ሳይንቀን ስለመጣ ልናመሰግነው ነው ሚገባው» ብዬ ተጠቅልዬ ተኛሁ።

ለጠቅላላ እውቀት የሰውነታችን ብዛት ※ የአጥንታችን ብዛት ~ 206※ የጡንቻዎቻችን ብዛት ~ 639※ የኩላሊቶቻችን ብዛት ~ 2※ የወተት ጥርሶቻችን ብዛት ~ 20※ የጐን አጥንቶቻችን ብዛት ...
29/07/2025

ለጠቅላላ እውቀት የሰውነታችን ብዛት

※ የአጥንታችን ብዛት ~ 206
※ የጡንቻዎቻችን ብዛት ~ 639
※ የኩላሊቶቻችን ብዛት ~ 2
※ የወተት ጥርሶቻችን ብዛት ~ 20
※ የጐን አጥንቶቻችን ብዛት ~ 24 (12 ጥንዶች)
※ የልባችን ውስጥ ክፍሎች ብዛት ~ 4
※ ትልቁ ደም ቅዳ ~ አኦርታ
※ ጤናማ አማካይ የደም ግፊት መጠን ~ 120/80
※ የደም ፒ ኤች (PH) መጠን ~ 7.4
※ አዲስ የተወለደ ህፃን የአጥንት ብዛት ~ 300
※ በጀርባ ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 30
※ በአንገት ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 7
※ በፊት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 14
※ በጭንቅላት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 22
※ በደረት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 25
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የአጥንት ብዛት ~ 6
※ በሰው እግር ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 33
※ በእያንዳንድ የእጅ አንጓ (wrist) ላይ የሚገኙ
የአጥንቶች ብዛት ~ 8
※ በእጅ ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 27
※ በእያንዳንድ ጆሮአችን ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት
~ 3
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የጡንቻዎች ብዛት ~ 72
※ ትልቁ ኦርጋን ~ ቆዳ
※ ትልቁ ዕጢ ~ ጉበት
※ ትንሹ ሴል ~ የደም ሴል
※ ትልቁ ሴል ~ የዕንቁላል ሴል
※ ትንሹ አጥንት ~ ሰታፕስ (stapes)
※ የመጀመሪያው ንቅለ ተከላ የተደረገው የሰውነት ክፍል
~ ልብ
※ አማካይ የትንሹ አንጀት ቁመት ~ 7 ሜትር
※ አማካት የትልቁ አንጀት ቁመት ~ 1.5 ሜትር
※ አዲስ የተወለደ ህፃን አማካይ ክብደት ~ 2.6 ኪሎ
ግራም
※ የልብ ምት በአንድ ደቂቃ ውስጥ ~ 72 ጊዜ
※ የሰውነት ሙቀት ~ 36.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ (98.4
ዲግሪ ፋራናይት)
※ አማካይ የደም መጠን ~ ከ 4-5 ሊትር
※ ቀይ የደም ሴል በህይወት የሚቆዮበት ጊዜ ~ 120
ቀናቶች
※ የእርግዝና የጊዜ ቆይታ ~ 280 ቀናቶች
※ ትልቁ የኢንዶክራይን ዕጢ ~ ታይሮይድ
※ ትልቁ የሊምፋቲክ (lymphatic) ዕጢ ~ ጣፊያ
※ ግዙፉ ሴል ~ ነርቭ ሴል
※ ትልቁ የአእምሮ ክፍል ~ ሰርብረም
※ ትልቁና ጠንካራው አጥንት ~ ፌሙር (Femur)
※ ትንሹ ጡንቻ ~ ስታፒደስ (Stapedius)
(የመካከለኛው ጆሮ)
※ በሴል ውስጥ ያለ የክሮሞዞም ብዛት ~ 44 (23
ጥንዶች)
※ ትልቁ ጡንቻ ~ መቀመጫ (ቂጥ)
ምንጭ አፍሪ መረጃ

"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ። ... በጊዜው የሚፈፀመው ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ!" ሉቃስ 1 ፥ 19 - 22"የእግዚአብሔር መልአ...
26/07/2025

"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ። ... በጊዜው የሚፈፀመው ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ!"
ሉቃስ 1 ፥ 19 - 22

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"
መዝሙር 34 ፥ 7
🥰
❤️
"ገናም በፀሎት ስናገር አስቀድሜ በራዕይ አይቼ የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ። በማታም መስዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ 🥰"
ዳን 9 ፥ 21

የምህረት አማላጅ፤
የሰው ልጆች ወዳጅ፤
አንተነህ ገብርኤል፤
የምትቆም በቅድመ እግዚአብሔር።
አብሳሪው መልዓክ ተሸክመህ ዜና፤
ለእኛ ለልጆችህ ምስራች ይዘህ ና።

ሠለስቱ ደቂቅን፣ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ እየሉጣን ከሚነደው እሳት ፈጥነህ ያዳንካቸው ኃያሉ መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ "ቃልን" ለወለደችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ደስ የሚል የምስራችን እንዳበሰርካት ሁሉ ለእኛም መልካሙን የምስራች አብስረን፤ የምንፀድቅበትንና የምንድንበትን ዜና አሰማን 🙏🙏

ለመጋቤ ሀዲስ፣ ለኃያሉና ለአብሳሪው መልዓክ ለቅዱስ ገብረኤል አመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን። የብስራታዊው መልዓክ ፀጋ፣ ረድኤት፣ በረከትና ምልጃ አይለየን!
የሕይወትን ቃል ያሰማን!
የዓመት ሰው ይበለን 🙏🙏🙏

የጥቅል ጎመን 8 አስደናቂ የጤና ጥቅሞችጥቅል ጎመን በቀላሉ የማይገመት የጤና በረከት ያለው አትክልት ነው። የአጥንትና የልብ ጤናን ከማሻሻል ጀምሮ በርካታ ጥቅሞች አሉት። በውስጡ በሚገኘው ፋ...
26/07/2025

የጥቅል ጎመን 8 አስደናቂ የጤና ጥቅሞች

ጥቅል ጎመን በቀላሉ የማይገመት የጤና በረከት ያለው አትክልት ነው። የአጥንትና የልብ ጤናን ከማሻሻል ጀምሮ በርካታ ጥቅሞች አሉት።

በውስጡ በሚገኘው ፋይበር (fiber)፣ ቫይታሚን ሲ እና ቫይታሚን ኬ ምክንያት ለጤናችን ተመራጭ ያደርገዋል።

በተጨማሪም ካሎሪው በጣም ዝቅተኛ ነው፤ አንድ ኩባያ የተከተፈ ጥሬ ጥቅል ጎመን 17.5 ካሎሪ ብቻ ይይዛል።

ጥቅል ጎመን መነሻው ከአውሮፓ ሲሆን፤ በጥሬውም ሆነ አብስለን መመገብ እንችላለን።

ጠቃሚ ምክር

ሁሉንም ወይም ሙሉ ጥቅሞቹን ለማግኘት፣ አብስሎ ከመመገብ ይልቅ በጥሬው ሰላጣ ሠርቶ መመገብ ወይም ለትንሽ ጊዜ በዘይት ጠብሶ መጠቀም ይመከራል። ለረጅም ጊዜ ሲበስል አንዳንድ ንጥረ ነገሮቹን ሊያጣ ይችላል።

የጥቅል ጎመን የጤና ጥቅሞች

1.ዋጋው ተመጣጣኝ እና ዝቅተኛ ካሎሪ ስላለው

ክብደት ለመቀነስ እየሞከሩ ከሆነ፤ ከፍተኛ የካሎሪ ይዘት ያላቸውን ምግቦች ዝቅተኛ ካሎሪ ባላቸው መተካት ተገቢ ነው።

አንድ ኩባያ የተከተፈ ጥሬ ጎመን 17.5 ካሎሪ ብቻ ስላለው ክብደትን ለመቆጣጠር ወይም ለመቀነስ ተመራጭ ያደርገዋል።

ብዙ ንጥረ ነገር ያላቸው ምግቦች ውድ ሲሆኑ፤ ጥቅል ጎመን ግን በዋጋው በጣም ተመጣጣኝ ነው።

2.የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል

በዓለም ላይ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሰዎች ለልብ ህመም እና ለስትሮክ (ለአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ) የሚያጋልጥ ከፍተኛ የደም ግፊት ችግር አለባቸው።

ጥቅል ጎመን የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዳውን ፖታሺየም በውስጡ ይዟል። ፖታሺየም የነርቭ እና የጡንቻን ሥራ የሚያግዝ፣ እንዲሁም የልብ ምትን የሚያስተካክል ንጥረ ነገር ነው።

በሰውነታችን ውስጥ የሶዲየም (ጨው) መጠን ሲበዛ የደም ግፊት ስለሚያስከትል፤ ፖታሺየም ይህንን የጨው ተጽዕኖ ለመቀነስ ይረዳል።

3.የካንሰር ሴሎች እድገትን ሊከላከል ይችላል

እንደ ጥቅል ጎመን ያሉ አትክልቶች ግሉኮሲኖሌትስ (glucosinolates) የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይይዛሉ።እነዚህ ሰልፈር ያላቸው ኬሚካሎች ለጥቅል ጎመን መራራ ጣዕም ተጠያቂ ወይም መንስእኤዎች ናቸው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ሰውነታችን እነዚህን ንጥረ ነገሮች ወደ ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ ወዳላቸው ውህዶች ይለውጣቸዋል።

ይህ ማለት ግን ጥቅል ጎመን መመገብ ካንሰርን ሙሉ በሙሉ ይከላከላል ማለት አይደለም፤ ተጨማሪ ምርምር ቢያስፈልግም፥ ጥቅል ጎመንን በአመጋገብ ውስጥ ማካተት ጤናማ ምርጫ ነው።

4.የአጥንት ጤናን ሊያሻሽል ይችላል

ጥቅል ጎመን ለአጥንት ጤና እና ለደም መርጋት ወሳኝ የሆነውን ቫይታሚን ኬ በውስጡ ይዟል።

አንድ ኩባያ ጥሬ ጥቅል ጎመን 53 ማይክሮግራም ቫይታሚን ኬ ሲይዝ፤ ወንዶች በቀን 120 እንዲሁም ሴቶች 90 ማይክሮግራም ያስፈልጋቸዋል።

የቫይታሚን ኬ እጥረት ኦስቲዮፖሮሲስ (የአጥንት መሳሳት) እና ለደም መፍሰስ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል።

5.ከልብ ሕመም ይከላከላል

ጥቅል ጎመን ለልብ ጤና ጠቃሚ መሆኑን ላያስቡ ይችላሉ፤ ነገር ግን በአመጋገብዎ ውስጥ ቢጨምሩት ይመረጣል።

በውስጡ ያሉት ንጥረ ነገሮች በሰውነት ውስጥ እብጠትን በመቀነስ ለልብ ህመም ያለውን ተጋላጭነት እንደሚቀንሱ ጥናቶች ያሳያሉ።

አንድ ጥናት እንዳመለከተው፤ ብዙ ጥቅል ጎመን የሚመገቡ ሴቶች ለልብ ህመም ተጋላጭነትን ሊያመለክት ከሚችል የደም ቧንቧ መጥበብ (AAC) በ46% ያነሰ ተጋላጭ ነበሩ።

6.ኢንፍላሜሽንን (እብጠትን) ይቀንሳል

የረጅም ጊዜ ኢንፍላሜሽን (Chronic inflammation) በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ሴሎችን ሊጎዳና እንደ አርትራይተስ (የቁርጥማት በሽታ

ለጠቅላላ እውቀትኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከ...
09/06/2025

ለጠቅላላ እውቀት
ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤

ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና...
02/06/2025

ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና ከሚስቱ ጋር ተፋታ፡፡ ወደ ጓደኛውም ቤት ሄደ፡፡ ጓደኛው አልጋ አንጥፎ ተቀበለው፡፡
ማታ ራት ቀረበ፡፡ ምን የመሰለ ነጭ ጤፍ ላይ አልጫና ቀዩ ተጋድሞ ቀረበለት፡፡ በአንድ በኩል ቃሪያው፣ በአንድ በኩል ስልጆው፣ በአንድ በኩል ፍትፍቱ፣ በአንድ በኩል አተር ክኩ ተሰለፈ፡፡ «ወይ ሞያ እኔማ ኖርኩ አይባልምኮ» እያለ ያማርር ጀመር፡፡ «አንተማ ታድለህ» ይለዋል ጓደኛውን፡፡ «ይሁን እስኪ» ይላል ያኛውም፡፡ ጠላው ሲቀርብ ደግሞ እያደነቀ ጠጣ፡፡ «ከኖሩ ላይቀር እንዲህ ነው» ይል ጀመር፡፡ ያችንም ባለሞያ ሚስት በምስጋናና በአድናቆት አረሰረሳት፡፡

በልተው ሊያጠናቅቁ ሲሉ ጋባዡ ሊጠጣበት ያነሣው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡ ደነገጠ፡፡ ሚስት ከጓዳ መጣች፡፡ «ምንድን ነው የተሰበረው?» አለች፡፡

«ያ የምትወጅው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡» አላት ባሏ በተስለመለመ ድምፅ፡፡ ተናደደችና አንዴ በጥፊ አላሰችው፡፡ ጓደኛው ደነገጠ፡፡ «እንዲህ ሰብረህ ሰብረህ የአባት የናቴን ስጦታ ጨረስከው፡፡ አንተ ምን ታደርግ ተንቀባርረህ ከነ ጓደኛህ ትልፋለህ» እያለች ቁም ስቅሉን ታሳየው ጀመር፡፡ ባልዬው ፀባይዋን ያውቃልና ዝም አለ፡፡ ያም ጓደኛው «ምን ለብርጭቆ ደግሞ ነገ ይገዛል፤ ዋናው ጤና ነው» አለ ነገር ያበረደ መስሎት፡፡ «አንተ ደግሞ አርፈህ ተቀመጥ፤ ሚስትህን እንደዚህ አማረሃት ይሆናል ይኼኔ፤ ቀላዋጭ» አለችና አቀመሰችው፡፡ ተፈታተነው ስሜቱ፡፡ ግን እንግድነቱ በልጦበት «ኧረ የኔዋስ እንዳንቺ» አለና ጀምሮ ተወው፡፡ ወደ ጓዳ ገባችና አንድ ፍልጥ ይዛ መጣች፡፡ እስኪ ጨርሰው አለቺው፡፡ ዓይኑ ተቁለጨለጨ፡፡ «እንዳንቺ የባሰባት አይደለችም» ሲላት ፍልጡን ይዛ መጣች፡፡

ይህንን ሲያይ ባልዬው «ቀስ ብለህ አምልጥ» አለው፡፡
በዚያ ሌሊት እየገሠገሠ የሚስቱ እናት ጋ ሄደ፡፡

እናቲቱም «ምነው ልጄ» አሉት
«እማማ፤ ከሌሊት ፍልጥ፣ የቀን ሊጥ ይሻለኛል ብዬ መጣሁ፡፡ አላቸው ይባላል፡፡
ወዳጄ ያለህን ካላሰብከው የባሰው ላይ ትወድቃለህ ያልኩ ለዚህ ነው፡፡
እስኪ ወዳጄ ያለህን ዕወቀው፤ አክብረው፤ አሟጠህ በሚገባ ተጠቀምበት፤ በዚያ ኑርበት፤ አጊጥበት፡፡ ከዚያ ሌላውን ለመያዝ ፈልግ፡፡ ባለህ የማትረካ ከሆንክ ግን ሩጫህ የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ ይሆናል፡፡

"በእጅ የያዙት ወርቅ....."

ወዳጄ ውዷ ሚስትህን አጥብቀህ ያዝ የባሰ አለና!
ከተመቻችሁ ፎሎ ላይክ ሼር ማረጉ አይሠሳ
👇👇👇👇👇👇

01/06/2025

25ቱ የአለማችን የሳይንስ አባቶች
----------------------------//////--------------
1. ጋሊሊዮ ጋላሊ = የፊዚክስ አባት
2. አሪስጣጣሊስ = የባዮሎጂ አባት
3. ዳቢር ኢብን ሀያን = የኬሚስትሪ አባት
4. ሚካኤል ፋራዳይ=የኤሌክትሪክ ሲቲ አባት
5. ዳዮፋንተስ = የአልጄብራ አባት
6. ኢዩክሊስድ = የጂኦሜትሪ አባት
7. ሒፖክራተስ = የህክምና አባት
8. ፍላሎረንስ ናይቲንግ= የነርሲንግ እናት
9. ግሪጎር ሜንዴል = የጄኔቲክስ አባት
10. ፊጣጎራዝ = የቁጥር አባት
11. ኒኮስ ማኪያቬሊ = የፖለቲካ ሳይንስ አባት
12. ኢሜል ደርካይም = የሶሺዮሎጂ አባት
13. አዳም ስሚዝ = የኢኮኖሚክስ አባት
14. አይዛክ ኒውተን = የካልኩለስ አባት
15. ካርል ማርክስ = የኮሙኒዝም አባት
16. ማርኮኒ = የሬዲዮ አባት
17. ኧርነስት ሩዘርፎርድ = የኒውክሌር ፊዚክስ አባት
18. አልበርት ኢንስታይን = የአንፃራዊ ቲዎሪ አባት
19. ማክስ ፕላንክ = የኳንተም ቲዮሪ አባት
20. ዱሜትሪ ሜንዴሌቭ = የፔሬዲክ ቴብል አባት
21. ቬሳልየስ = የአናቶሚ አባት
22. መሀመድ ዮኑስ = የማይክሮ ክሬዲት አባት
23. ሜሪ ኩሪ = የኒውክሌር አባት
24. ሉክ ሆዋርድ = የሜትሮሎጂ አባት
25. ኧርነስት ሀኬል = የኢኮሎጂ አባት

©️ከዕውቀት ማህደር

"አልችልም ስትልበሰው ዘንድ የማይቻል በእኔ  ዘንድ ይቻላል ይልሃል::          (ሉቃስ 18_27)"እጨነቃለሁ ስትልየሚስጨንቅህን ሁሉ በኔላይ ጣል ይልሃል::             (1ኛ ጰ...
01/06/2025

"አልችልም ስትል
በሰው ዘንድ የማይቻል በእኔ
ዘንድ ይቻላል ይልሃል::
(ሉቃስ 18_27)

"እጨነቃለሁ ስትል
የሚስጨንቅህን ሁሉ በኔ
ላይ ጣል ይልሃል::
(1ኛ ጰጥ 5:7)

"ደክሞኛል ስትል
አሳርፍሃለሁ ይልሃል::
(ማቴ 11:28 _30)

"አቅቶኛል መቀጠል አልችልም ስትል
ጸጋዬ ይበቃሃል ይልሃል:;
(2ኛ ቆሮ 12:9)

"ማድረግ አልችልም ስትል
ኃይልን በምሰጥህ በእኔ ሁሉን
ትችላለህ ይልሃል::
(ፊል 4:13)

"ብቃት የለኝም ስትል
ብቃት አለህ ይልሃል::
(2ኛ ቆሮ 9:8_9)

"ፈርቻለሁ ስትል
የፍርሃት መንፈስ
አልሰጠሁህም ይልሃል::
(2ኛ ጢሞ 1:7)

"እራሴን ይቅር ማለት አልችልም ስትል
እኔ ይቅር እልሀለሁ ይልሃል::
(1ኛ ዮሐንስ 1:9)

ይሄ ለኔ አይገባኝም ነበር ለምን እኔ ላይ ሆነ ስትል
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይልሃል::
(ሮሜ 8:28)

"ብለሃት የለኝም ስትል
ጥበብን እሰጥሃለሁ ይልሃል::
(1ኛ ቆሮ 1: 30_31)

02/04/2024
02/04/2024

Address

Adiss Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጤና ለአዳም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram