Ethioscandic Clinics

Ethioscandic Clinics ኢትዮ ስካንዲክ የቀድሞ የወንድይራድ ተማሪዎች እና የኮተቤ ልጆች የተቋቋመ ሲሆን አላማው ለአካባቢው ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነው

የፕሮስቴት እጢ እድሜ ከ 45 አመት ሲዘል ማደግ ወይም መፋፋት ይጀምራል፡፡ ነገር ግን ስላደገ ብቻ ህክምና ይፈልጋል ማለት አይደለም፡፡ የሚከተሉት ሁኔታዎች ካሉ ብቻ ፕሮስቴት እጢ ህክምና ያ...
02/09/2025

የፕሮስቴት እጢ እድሜ ከ 45 አመት ሲዘል ማደግ ወይም መፋፋት ይጀምራል፡፡ ነገር ግን ስላደገ ብቻ ህክምና ይፈልጋል ማለት አይደለም፡፡

የሚከተሉት ሁኔታዎች ካሉ ብቻ ፕሮስቴት እጢ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡

1. መካከለኛ እና ጠንካራ የሽንት ምልክቶች ካሉ፡ ሽንት በቀጭኑ መውረድ፣ ሲወርድ ማስቸገር፣ ሌሊት ማመላለስ፣ ማጣደፍ ብሎም አጣድፎ ማምለጥ

2. ሽንት ከነጭራሹ አልወርድ ካለ (ከዘጋ)

3. ተያያዥ መዘዞች ካስከተለ፡ ለምሳሌ ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን፣ የፕሮስቴት መድማት ችግር፣ ሽንት በመዘጋቱ ምክንያት የመጣ የኩላሊት መጎዳት፣ የሽንት ፊኛ ጠጠር፣ ኸርኒያ (ቡዓ)

4. ዝቅተኛ/መጠነኛ ምልክቶች ኖረው ታካሚው ህክምናውን ከፈለገ፡ የሽንት ችግሮች ዝቅተኛ ሆነው ታካሚውን ከረበሹት፣ አኗኗር ዘይቤው ላይ እክል ከፈጠረ

የተለመዱ ስህተቶች

1. የፕሮስቴት እጢ ስላደገ ብቻ ህክምና ይፈልጋል የሚል እምነት የተሳሳተ ነው፡፡ የፕሮሰቴት እጢው እድገት መጠን በፍጹም ከህክምና ውሳኔ ጋር አይገናኝም፡፡

2. የፕሮሰቴት ካንሰርን ለመከላከል ገር የፕሮሰቴት እጢ መፋፋትን ማከም

ሕክምና

የፕሮስቴት እጢ መፋፋት ህክምናው በመድሃኒት የሽንት ምልክቶችን ማስተካከል ወይንም በቀዶ ህክምና ፕሮሰቴቱን ማስወገድ ሊሆን ይችላል፡፡

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

👉 ቴሌግራም👈 (https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0) 👉 ቲክቶክ (https://www.tiktok.com/) 👈

👉ፌስቡክ👈 (https://web.facebook.com/ethioscandicclinic) 👉ዌብሳይት (https://ethioscandicclinics.com/) 👈

#ኩላሊት #ጠጠር

አንዳንድ ታካሚዎቻችን ‘የኩላሊት ጠጠር አለብኝ ያፈርስልሻል ተብዬ ይህ መድሃኒት ተሰጠኝ’ ይሉናል፡፡ይህ ምን ያህል ተቀባይነት ያለው ህክምና ነው?ኩላሊት ውስጥ ላለ ጠጠር መድሃኒት የሚታዘዘው...
01/09/2025

አንዳንድ ታካሚዎቻችን ‘የኩላሊት ጠጠር አለብኝ ያፈርስልሻል ተብዬ ይህ መድሃኒት ተሰጠኝ’ ይሉናል፡፡

ይህ ምን ያህል ተቀባይነት ያለው ህክምና ነው?
ኩላሊት ውስጥ ላለ ጠጠር መድሃኒት የሚታዘዘው
1. ህመም ካለ ህመሙን ለማስታገስ
2. በልዩ ልዩ የቀዶ ህክምና ዘዴዎች ጠጠሩ ከወጣ እና የጠጠሩ ኬሚካል ይዘት ከታወቀ ጠጠር በድጋሚ እንዳይከሰት ለመከላከል
3. ከጠጠሩ ጋር ተያይዞ ኢንፌክሽን ከተከሰተ ኢንፌክሽኑን ለማከም
4. ከቀዶ ህክምና ውጪ ለመውጣት እድል ለሌለው የጠጠር መጠን በመድሃኒት ለማፍረስ እና ለማስወጣት የሚባል ህክምና የለም፡፡
5.የዪሪክ አሲድ ጠጠር በመድሃኒት ሊታከም የሚችል ብቸኛ የጠጠር አይነት ሲሆን፤ አንደኛ ጠጠሩ አይነቱ ሳይታወቅ፤ ሁለተኛ የዚህ አይነት ይዘት ያለው ጠጠር በጣም አልፎ አልፎ ብቻ የሚታይ ስለሆነ መድሃኒት መጠቀም በአብዛኛው አስፈላጊ አይደለም፡፡
6. ከኩላሊት ወደፊኛ የሚወስደው የሽንት መውረጃ ቱቦ ውስጥ ጠጠር ከገባ እና የጠጠሩ መጠን አነስተኛ ከሆነ መስመሩን የተሻለ ክፍት ለማድረግ የሚረዱ መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

ድምዳሜ፡ የኩላሊት ጠጠር በመድሃኒት አይፈርስም፤ አይወጣም፡፡ ጠጠሩ ከተወገደ እና የጠጠሩ ኬሚካላዊ ይዘቱ ከታወቀ ለመከላከል መድሃኒት ሊሰጥ ይችላል፡፡

መፍትሄ፡ የኩላሊትም ሆነ ሌላ የሽንት መስመር ጠጠር ካለብዎ ዩሮሎጂስቶችን ማማከር ትክክለኛውን ምክርና ህክምና ለማግኘት ይረዳዎታል፡፡ ኢትዮ ስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ቢመጡ ሲኒየር ዩሮሎጂሰታችንን ዶ/ር መዝገብ ገደፌን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ደውለው ቀጠሮ ይያዙ፡፡

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

ቴሌግራም👉 (https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0) https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0

ቲክቶክ👉 (https://www.tiktok.com/) https://www.tiktok.com/

#ኩላሊት #ጠጠር

ከላይ ከጠቀስናቸው በተጨማሪ ማስቲካ ማኘክ አንዳንዴ ነቃ ለማለትም ይጠቅማል። ነገር ግን ከበዛ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። እርስዎ በቀን ለምን ያህል ሰዓት ማስቲካ ያኝካሉ?ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊ...
29/08/2025

ከላይ ከጠቀስናቸው በተጨማሪ ማስቲካ ማኘክ አንዳንዴ ነቃ ለማለትም ይጠቅማል። ነገር ግን ከበዛ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። እርስዎ በቀን ለምን ያህል ሰዓት ማስቲካ ያኝካሉ?

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

ቴሌግራም 👉 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/

#ማስቲካ #ጤና

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን ቢያንስ ለ8 ሰዓታት ያህል ተቀምጠን እናሳልፋለን ይህም ረጅም ሰዓት ከመቀመጥ ጋር ተያይረዘው ለሊመምጡ የጤና እክሎች የሚኖረን ተጋላጭነት ከፍ ያለ እንዲሆን ያደር...
28/08/2025

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን ቢያንስ ለ8 ሰዓታት ያህል ተቀምጠን እናሳልፋለን ይህም ረጅም ሰዓት ከመቀመጥ ጋር ተያይረዘው ለሊመምጡ የጤና እክሎች የሚኖረን ተጋላጭነት ከፍ ያለ እንዲሆን ያደርጋል።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

ቴሌግራም 👉 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/

ከ2 ሳምንት ፆም በኋላ ጨጓራችን ጠንካራ ምግቦችን የመፍጨት አቅሙ ይቀንሳል። ስለዚህ ፆም ለመፍታት እንደ ጥሬ ስጋ፣ ጥብስ፣ በርገር እና ፒዛ ያሉ ምግቦችን መመገብ አይመከርም። ከተቻለ ለስለ...
22/08/2025

ከ2 ሳምንት ፆም በኋላ ጨጓራችን ጠንካራ ምግቦችን የመፍጨት አቅሙ ይቀንሳል። ስለዚህ ፆም ለመፍታት እንደ ጥሬ ስጋ፣ ጥብስ፣ በርገር እና ፒዛ ያሉ ምግቦችን መመገብ አይመከርም። ከተቻለ ለስለስ ባለ ሾርባ ፆም መፍታት ካልሆነም የፍስግ ምግቦችን ከአትክልት ጋር አብሮ መመገብ እንዲሁም እንደ ፓፓያ እና ሃባብ ያሉ ፍራፍሬ ዎችን መመገብ ጨጓራ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ ይመከራል።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

ቴሌግራም👉 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/

#ፆም

በስራ የደከመ አዕምሮን ነቃ ለማድረግ ከምሳ በኋላ ቡና መጠጣት የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ ልማድ ጉበትዎትን እየጎዳው ይሆን?ክሬም የበዛባቸው እንደ ማኪያቶ ያሉ የቡና አይነቶችን ማዘውተር...
20/08/2025

በስራ የደከመ አዕምሮን ነቃ ለማድረግ ከምሳ በኋላ ቡና መጠጣት የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ ልማድ ጉበትዎትን እየጎዳው ይሆን?

ክሬም የበዛባቸው እንደ ማኪያቶ ያሉ የቡና አይነቶችን ማዘውተር፣ ስኳር የበዛበት ቡና እንዲሁም ከ2 እና 3 ስኒ በላይ ቡና ደጋግሞ መጠጣት ጉበት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ይህ ማለት ግን ቡና በፍፁም አይጠጡ ማለት አይደለም። በቀን የሚጠጡትን ቡና መጠን በመቀነስ እንዲሁም ስኳር ሳያበዙ ወይም ያለስኳር በመጠጣት ጉበትዎን ሳይጎዱ አዕምሮዎን ነቃ ማድረግ ይችላሉ።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

👉 ቴሌግራም https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0
👉 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/

#ቡና #ጉበት

በተደጋጋሚ ከፍተኛ ስብ እና ከፍተኛ ጨው ያላቸውን ምግቦችን ደጋግሞ መመገብ የደም ግፊት ከመጨመርም አልፎ ለልብ ህመም ያለንን ተጋላጭነት ይጨምራል።ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክአድራሻ - ኮ...
12/08/2025

በተደጋጋሚ ከፍተኛ ስብ እና ከፍተኛ ጨው ያላቸውን ምግቦችን ደጋግሞ መመገብ የደም ግፊት ከመጨመርም አልፎ ለልብ ህመም ያለንን ተጋላጭነት ይጨምራል።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

👉 ቴሌግራም https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0

👉 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/

ስለ ፕሮስቴት መፋፋት እና የፕሮስቴት ካንሰር ጠቃሚ 5 ነጥቦች1. የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች በጣም በብዛት የሚገኝ ሲሆን ከ ስምንት ሰዎች አንዱን ሊያጠቃ የ...
08/08/2025

ስለ ፕሮስቴት መፋፋት እና የፕሮስቴት ካንሰር ጠቃሚ 5 ነጥቦች

1. የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች በጣም በብዛት የሚገኝ ሲሆን ከ ስምንት ሰዎች አንዱን ሊያጠቃ የሚችል ችግር ነው። ነገር ግን ሁሉም የፕሮስቴት መፋፋቶች ካንሰር አይደሉም።

2. የፕሮስቴት እጢ ከ45 እስከ 50 እድሜ ጀምሮ ማደግ ይጀምራል። ይህ ማደግ በአብዛኛው ገር መፋፋት ሲሆን አልፎ አልፎ ደግሞ ካንሰር ሊሆን ይችላል፡፡

3. BPH የምንለው ገር የፕሮሰቴት እጢ መፋፋት ለሃያም ሆነ ለሰላሳ አመታት አብሮን ቢቆይም ወደ ካንሰር የመቀየር እድል የለውም፡፡ በቀላሉም በቀዶ ጥገና መስተካከል ይችላል። ካንሰር ከተፈጠረ ግን ለገር የፕሮስቴት መፋፋት የሚደረገው ህክምና ካንሰሩን የሚያስወግድ አይደለም።

4. የፕሮስቴት ካንሰርን በግዜ ለማወቅ PSA የሚባለውን የፕሮሰቴት ካንሰር ጠቋሚ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የፕሮስቴት ካንሰር በግዜ ከታወቀ በቀዶ ህክምና ወይንም በጨረር ሙሉ በሙሉ መዳን ይችላል። በግዜ ካልተገኘ ደግሞ እድገቱንና ስርጭቱን ለመቀነስ የሚያስችል ህክምና አለው፡፡

5. የፕሮሰቴት እጢ ቢያድግም ባያድግም ከሃምሳ አመት እድሜ በኋላ PSA በየሁለት አመቱ ቼክ ማድረግ ይመከራል፡፡ እንደ ሁኔታው ሃኪምዎ በየአመቱ ወይንም ከዛበታች ሊያዝልዎ ይችላል። ደካማ የሽንት አወራረድ፣ ሌሊት ለሽንት መመላለስ፣ የሽንት ማጣደፍና ሌሎች ሽንት ላይ የሚታዩ ምልክቶች እድሜአቸው ከሃምሳ በላይ ሰዎች ላይ ከታየ ገር የፕሮሰቴት እጢ መፋፋት ወይንም ካንሰር ሊሆን ስለሚችል ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ

👉 ቴሌግራም👈 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0

👉 ቲክቶክ 👈 https://www.tiktok.com/

መርሳት የሌለብን ነገር መድሀኒት ውሰድ ብቻ ለስኳር ህመም መፍትሄ አይሆንም። አመጋገብን በማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማዘውተር በተፈጥሯዊ መንገድ የስኳር መጠናችንን መቆጣጠር...
07/08/2025

መርሳት የሌለብን ነገር መድሀኒት ውሰድ ብቻ ለስኳር ህመም መፍትሄ አይሆንም። አመጋገብን በማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማዘውተር በተፈጥሯዊ መንገድ የስኳር መጠናችንን መቆጣጠር መቻል ይኖርብናል። ይህ ከሆነ የምንወስደውን መድሃኒት መጠን ቀስ በቀስ እየቀነስን በመሄድ ከተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶች ራሳችንን መከላከል እንችላለን።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ዋናው መንገድ ላይ

👉 ቴሌግራም https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0

#ስኳር #የጤናምክር #ህከምና

ጥሩ እና በቂ እንቅልፍ ለማግኘት የሚቸገሩ ከሆነ እነዚህን ነገሮች በማድረግ የተሻለ እንቅልፍ ማግኘት ይችላሉ።- ከሰዓት ወይም ከእንቅልፍ ሰዓትዎ እስከ 8 ሰዓት በፊት ቡና አይጠጡ።- ሰውነት...
05/08/2025

ጥሩ እና በቂ እንቅልፍ ለማግኘት የሚቸገሩ ከሆነ እነዚህን ነገሮች በማድረግ የተሻለ እንቅልፍ ማግኘት ይችላሉ።

- ከሰዓት ወይም ከእንቅልፍ ሰዓትዎ እስከ 8 ሰዓት በፊት ቡና አይጠጡ።
- ሰውነትዎን የማይቀያየር የመተኛ እና የመነሻ ሰዓት ያስለምዱ
- ከመተኛትዎ ከ30 ደቂቃ በፊት ስልክ አይጠቀሙ!
- የመኝታ ቤታችሁን ምቹ እና ሙቀት ያልበዛበት ለማድረግ ሞክሩ።

ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ዋናው መንገድ ላይ

ቴሌግራም ግሩፕ 👉 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0

ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/

ፌስቡክ 👉 https://web.facebook.com/ethioscandicclinic

ዌብሳይት 👉 https://ethioscandicclinics.com/

#ሆስፒታል #የጤናምክር #ህከምና #የህክምናምክር

Address

የካ ክ/ከ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ
Addis Ababa

Telephone

+251930031317

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethioscandic Clinics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram