17/03/2022
የቀጠለ...
የባይፖላር ዲስኦርደር መለያ አብይ ገጽታዎች ፦
ህመሙ በዋናነት መገለጫው በዉስጡ ሁለት የህመም ስሜቶችን አቅፎ መያዙ ነው ።
እነዚህም የህመም ስሜቶች ሽቅበት (ማንያ) እና ድባቴ ይባላሉ የሽቅበትና የድባቴ ስሜቶች እራሳቸውን ችለው በሰዎች ላይ የሚከሰቱበት እድል ያለ ቢሆንም ባይፓላር በሆነ ታማሚ ሰው ላይ ግን በተለያዩ ጊዜያት በመፈራረቅ የሚከሰቱ በመሆናቸው ለዚህ የአእምሮ ህመም አብይ መገለጫዎች ናቸው ።
የሽቅበት(ማንያ) ህመም መገለጫዎች(ምልክቶች )የሚከተሉት ናቸው ፦ ከመጠን ያለፈ ደስታ ፤እራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ፤ከመጠን በላይ መቅበጥበጥና መናገር ፤እንቅልፍ ማጣት፤መዝፈን /መዘመር ማብዛት ፤እጅግ አብዝቶ ብስጩ መሆንና መረበሽ፤ ባልተለመደ መልኩ የተዛባ አመለካከትና የተሳሳተ እምነት መያዝ ፤ለወሲብ ያለ ተነሳሽነት ከልክ በላይ መሆን ፤ ለአደንዛዥ እፆች የበዛ ፍላጎት ማሳየት ፣የጠበኛነት፤የበጥባጭነት፤ጣልቃ ገብነት ሀይለኝነትና የቁጡነት ባህሪ ማሳየት ፤ ገንዘብ ያለአግባብ ማጥፋት ፤ሌሎች የማይሰሙትን ድምፅ መስማት ሲሆኑ በቀጣይ የድባቴ ምልክቶችን እናያለን ።
ይቀጥላል
ያለ አእምሮ ጤና ጤንነት የለም ።!!!