
02/07/2025
እግዚአብሔር ልመናየን ና ጸሎቴንም ሰማኝ ከብዙ ፈተናና ውጣውረድ በሗላ ለዚህ ስኬት በቅቻለሁ። በቅድሚያ የስከቴ ምንጭ እና ባለቤት የሆነውን: የረዳኝን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ስምህም ለዘላለም የተመሰገነ የከበረም ነው:: በመቀጠልም በትምህርት ላይ እያለሁ ላትመለስ ለተለየችኝ የህይወት ዘመኔ ና የምንጊዜም ጀግናየ ውድ ና ወደሬለሽ እናቴ ወ/ሮ በላይነሽ ተመስጌን ምንም እንኳ በአካለ ስጋ አጠገቤ ባትኖሪም የአመታት ድካምሽ ና ልፋትሽ እንሆ ዛሬ እውን ሁኗል። እናም አፈር ይቅለልሽ ነፍስሽን በደጋጎች አባቶች በአብርሃም ና በይሳቅ ጎን በአጸደ ገነት ያስቀምጥልኝ። ባለ ብዙ ባለውለታየ ነሽ ና በልቤ ውስጥ ታትመሽ ና አቅፌሽ እኖራለሁ። በመጨረሻም በትምህርት ቆይታየ ወቅት ለረዳችሁኝ ና ላገዛችሁኝ እንዲሁም በምርቃቴ ፕሮግራም ላይ ተገኝታችሁ የደስታየ ተካፋይ ለሆናችሁ ሁሉ በተለይም ለዶ/ር መለሰ ታምሩ፣ ለብሩክ መለሰ፣ ለአብ ስራ መለሰ ከሀገረ አሜሪካ ድረስ መጥታችሁ ላሳያችሁኝ ፍቅር ከልብ የመነጨ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ::
ይህዓለም ታምሩ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጰያ
ሴኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም