Acıbadem Hospitals Group Ethiopia

Acıbadem Hospitals Group Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Acıbadem Hospitals Group Ethiopia, Hospital, ቦሌ መድሃኒአለም አንበሳ ባንክ ህንፃ አንደኛ ፎቅ, Addis Ababa.

በኢስታንቡል ከተማ ተመሳሳይ ስያሜ ባለው አውራጃ ውስጥ አ.ኤ.አ በ 1991 ተመሠረተ። አሁን የአቺባደም ኸልዝኬር ግሩፕ 22 ሆስፒታሎችን እና 19 የህክምና ማዕከላትን ያቀፈ ሲሆን ወደ 22 000 የሚጠጉ ሰራተኞች አሉት፡፡ አቺባደም በቱርክ እና በቀጣናው የጤና ክብካቤ አገልግሎት ዘርፍ መሪ ነው።
የአቺባደም አለም ዓቀፋዊ የዕድገትና የልማት ጉዞ እ.ኤ.አ. በ 2012 ተቋሙ በሩቅ ምስራቅ ከሚገኙት ትላልቅ ተቋማት አንዱ ከሆነው ከአይ ኤች ኤች ኸልዝኬር ግሩፕ ቤርሃድ ጋር ሽርክና በመፍጠር በዓለም ላይ በግዝፈቱ ሁለተኛው የጤና እንክብካቤ ሰንሰለት አካል ከሆነበት ጊዜ የጀመሩ ነው፡፡
ቶኩዳ እና ሲቲ ክሊኒክን መግዛታቸውን ተከትሎ እ.ኤ.አ ከ2016 ወዲህ አቺባደም ሲቲ ክሊኒክ በቡልጋሪያ ትልቁ የግል የጤና አገልግሎት አቅራቢ ሆኗል።
አቺባደም ሄልዝኬር ግሩፕ በሁሉም የህክምና ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃዎች ማረጋገጫ የተሰጣቸውን እና የላቀ ጥራት ያላቸውን አገልግሎቶች ያቀርባል። የአቺባደም የጤና አገልግሎቶች ሰንሰለት አቺባደም ላብሜድ (ላቦራቶሪ)፤ አቺባደም ኢንሹራንስ (መድህን) እና አቺባደም የፕሮጀክት ማኔጅመንት (የሆስፒታል ፕሮጄክቶች) በመሳሰሉ በርካታ ተመጋጋቢ ኩባንያዎች የተጣመረ ነው፡፡ በተጨማሪም እ.ኤ.አ ከ2007 አንስቶ አቺባደም ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የዳበረ ልምድ እና እውቀትን በሙያው ውስጥ ለሚመጡ ትውልዶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡

ነፃ የህክምና ማማከር አገልግሎት በአሚን አጠቃላይሆስፒታልቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው አጂባደም ሆስፒታል ከአሚንአጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የቆየ የኩላሊት ችግርያለባቸውን ህሙማንን(CKD...
29/07/2025

ነፃ የህክምና ማማከር አገልግሎት በአሚን አጠቃላይ
ሆስፒታል
ቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው አጂባደም ሆስፒታል ከአሚን
አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የቆየ የኩላሊት ችግር
ያለባቸውን ህሙማንን(CKD) ብሎም ተያያዥ የኩላሊት
ችግሮች ዙሪያ ላይ ነፃ የቀዶ ህክምና ማማከር አገልግሎት
አዘጋጅትዋል።
ዶር አሊ ኦዜር ከአጂባደም ሆስፒታል የመጡ ባለሙያ

ሲሆኑ ከአሚን ሆስፒታል ስፔሻሊስቶች ጋር አንድ ላይ
በመሆን የነፃ ህክምና ማማከር አገልግሎቱን ነሐሴ 15
ያካሂዳሉ።
በነጻ የህክምና ምክር አገልግሎቱ በመገኘት -
· አማራጭ (ሁለተኛ) የሕክምና አስተያየት
· በአለም አቀፍ ባለሙያ የተዘጋጀ የህክምና እቅድ
· በሆስፒታላችን ያሉ የላቁ የሕክምና አማራጮችን መረጃ
ማግኘት ይችላሉ።
የዚህም አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የህክምና
ዶክመንቶን በማዘጋጀት ከታች ባሉት ቁጥሮች እየደወሉ
ቀጠሮ ይያዙ።
ኢሜል፡ KDAF@acibadem.com ,
amingeneralhospital2012@gmail.com

ነፃ የሕክምና የምክር አገልግሎት ከቱርክ አጂባደም ሆስፒታል በሚመጡት ፕሮፌሰር ሃካን በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል አጂባደም ሆስፒታል ከአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጭንቅላትና የነ...
24/04/2025

ነፃ የሕክምና የምክር አገልግሎት ከቱርክ አጂባደም ሆስፒታል በሚመጡት ፕሮፌሰር ሃካን በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል
አጂባደም ሆስፒታል ከአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጭንቅላትና የነርቭ ችግር ለሚሰቃዩ ህሙማን ነፃ የህክምና የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
ፕሮፈሰር ሃካን ግንቦት ፯ እስከ ፰ ቀን ፳፪፭ ከአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ነፃ የህክምና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ ።
አጂባደም የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ክፍል በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈር ቀዳጅ መሪዎች ከሆኑት አንዱ ነው። አጂባደም የነርቭ ቀዶ ጥገና ቡድን በሁሉም ዓይነት የአንጎል ዕጢዎች ፣ የሕፃናት የነርቭ በሽታዎች እና የአከርካሪ በሽታዎች ፣ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ ባሉ የነርቭ በሽታዎች ላይ በማተኮር ይሰራል።

በዚህ ነጻ የህክምና ምክክር ላይ በመገኘት የሚከተሉትን ማግኘት ይችላሉ፡፡
• አማራጭ(ሁለተኛ) የህክምና አስተያየት
• በአለም አቀፍ ስፔሻሊስት የተዘጋጀ የህክምና እቅድ
• በአጂባደም ሆስፒታል ላይ ያሉ የላቁ የሕክምና አማራጮችን መረጃ ማግኘት

የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የህክምና ዶክመንቶን በማዘጋጀት ከታች ባሉት ቁጥሮች እየደወሉ ቀጠሮ ይያዙ

Email: KDAF@acibadem.com , amingeneralhospital2012@gmail.com
WhatsApp: +251 99 598 2567 , +90 541 209 41 77, 0947101010

Acibadem International Patient Center is a one-stop international patient center that provides medical tourism and healthcare tourism for global patients.

ነፃ የህክምና ማማከር አገልግሎት  በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታልቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው አጂባደም ሆስፒታል ከአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የቆየ የኩላሊት ችግር ያለባቸውን ህሙማንን...
29/03/2025

ነፃ የህክምና ማማከር አገልግሎት በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል

ቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው አጂባደም ሆስፒታል ከአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የቆየ የኩላሊት ችግር ያለባቸውን ህሙማንን(Chronic kidney disease) ብሎም ተያያዥ የኩላሊት ችግሮች መፍትሄ ላይ የነፃ ማማከር አገልግሎት አዘጋጅትዋል።

ዶር አሊ ኦዜር ከአጂባደም ሆስፒታል የመጡ ባለሙያ ሲሆኑ ከአሚን ሆስፒታል ስፔሻሊስቶች ጋር አንድ ላይ በመሆን የነፃ ህክምና ማማከር አገልግሎቱን ሚያዚያ 9 - 10 ያካሂዳሉ።

በነጻ የህክምና ምክር አገልግሎቱ በመገኘት -

· አማራጭ (ሁለተኛ) የሕክምና አስተያየት
· በአለም አቀፍ ባለሙያ የተዘጋጀ የህክምና እቅድ
· በሆስፒታላችን ያሉ የላቁ የሕክምና አማራጮችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የዚህም አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የህክምና ዶክመንቶን በማዘጋጀት ከታች ባሉት ቁጥሮች እየደወሉ ቀጠሮ ይያዙ።

ኢሜል፡ KDAF@acibadem.com , amingeneralhospital2012@gmail.com
Whatsapp: +251995982567 , +90 5412094177 , +251947101010/8080

አዲስ ዘመን ሲለወጥ፣ ላልተለወጠው የእርስዎ ታማኝነት እና እምነት አመስጋኞች ነን። ዓመቱን በሙሉ ደስታን እና ስኬትን እንመኝልዎታለን። መልካም አዲስ ዓመት 2024!
29/12/2023

አዲስ ዘመን ሲለወጥ፣ ላልተለወጠው የእርስዎ ታማኝነት እና እምነት አመስጋኞች ነን። ዓመቱን በሙሉ ደስታን እና ስኬትን እንመኝልዎታለን። መልካም አዲስ ዓመት 2024!

ለ2024 የጤና ግቦች አለዎት? አጠቃላይ የጤና ግምገማ በማድረግ መጀመርዎ ለጉዞዎ ግሩም መነሻ ይሆናል። በአቺባደም ቀደም ብለን የማወቅ እና አስቀድሞ የመከላከል እርምጃዎችን እናስቀድማለን። ...
25/12/2023

ለ2024 የጤና ግቦች አለዎት? አጠቃላይ የጤና ግምገማ በማድረግ መጀመርዎ ለጉዞዎ ግሩም መነሻ ይሆናል። በአቺባደም ቀደም ብለን የማወቅ እና አስቀድሞ የመከላከል እርምጃዎችን እናስቀድማለን። ምኞትዎን ወደ ተግባራዊ እርምጃዎች ለመቀየር ጊዜው አሁን ነው! የእኛን ልዩ የአዲስ ዓመት የጤና ምርመራ ጥቅል ለመጠቀም አሁኑኑ እኛን ያግኙን። ጤናዎን እንጠብቅልዎ!

18/12/2023

ሴቶች፤ በአዲሱ አመት ለጤንነታችሁ ቅድሚያ ስጡ፡፡ የእኛ "የሴቶች የጤና ምርመራ ፕሮግራም" የእናንተን ልዩ የጤና ፍላጎቶች ለማሟላaት በጥንቃቄ የተነደፈ ነው። ከማሞግራም (አነስተኛ ጨረር በመጠቀም የሚካሄድ የጡት ኤክስሬይ) እስከ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ድረስ፣ የጤና ጉዞዎን እና እርስዎን ለማገዝ ተዘጋጅተናል። ጤናዎን በማስቀደም 2024ን ይጀምሩ!
ያሉትን ሁሉንም የጤና ምርመራ ጥቅሎች ዝርዝሮች ለማግኘት አሁኑኑ ያግኙን።

11/12/2023

ክቡራን፣ ይህ አመት ለጤንነታችሁ ቅድሚያ የምትሰጡበት ነው። የአቺባደም የወንዶች ጤና መርሃ ግብር lዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው። በዚህም ከልብ ህክምና ምርመራዎች አንስቶ እስከ የአእምሮ ጤና ምዘናዎች ድረስ የእርስዎን ደህንነት ቅድምያ ሰጥቶ ይመለከታል። ወደ ጤናማ 2024 የመጀመሪያዎን እርምጃ ይራመዱ!
ያሉንን ሁሉንም የጤና ምርመራ አገልግሎት ዝርዝሮች ለማግኘት አሁን ያግኙን።

04/12/2023

በኢስታንቡል ከተማ ውስጥ ከሚገኙት 10 የአቺባደም ግሩፕ ሆስፒታሎች አንዱ አቺባደም አልቱኒዛዴ ሆስፒታል ነው፡፡ የአልቱኒዛዴ ሆስፒታል የምርመራ ክፍል ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዶክተሮች እና ለታካሚዎች የተደራጀ እንዲሁም ምቹ የምርመራ ሂደት ለማደረግ የሚያስችሉ የተሟሉ መሠረተ ልማቶች አሉት። ለሙሉ የጤና ምርመራ የቀረቡላችሁን ሁሉንም የአገልግሎት ጥቅሎች ዝርዝሮች ለማግኘት አሁኑኑ ያግኙን።

አቺባደም ዩሮሎጂክ ኦንኮሎጂ የህክምና ክፍል የሽንት ማስወገጃ ስርዓት ካንሰር ላለባቸው ታካሚዎች በዓለም ዝነኛው መዳረሻ ነው። በአቺባደም ከቀዶ ሕክምና እስከ የጨረር ሕክምና፣ ከኬሞቴራፒ እስ...
27/11/2023

አቺባደም ዩሮሎጂክ ኦንኮሎጂ የህክምና ክፍል የሽንት ማስወገጃ ስርዓት ካንሰር ላለባቸው ታካሚዎች በዓለም ዝነኛው መዳረሻ ነው።
በአቺባደም ከቀዶ ሕክምና እስከ የጨረር ሕክምና፣ ከኬሞቴራፒ እስከ ኢሚውኖቴራፒ፣ እና ከፎካል ቴራፒ እስከ ኒውክሌር ሕክምና ድረስ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን እናቀርባለን። የኛ የኡሮሎጂ ቡድን ለፕሮስቴት ፣ ለኩላሊት ፣ ለፊኛ እና ለቴስቲኪዩላር ካንሰር በአነስተኛ ሽንቁር ረቂቅ ቀዶ ሕክምናዎች በማድረግ ላይ የተካነ ነው።
እያንዳንዱ ታካሚ በአሲባደም ቡድን ውስጥ በኦንኮሎጂ መማክርት ቡድን ውስጥ በሚሳተፉ ሁሉም የቡድኑ አባላት በጋራ ይገመገማል። የመማክርቱ ቡድን አባላት ታማሚውን ይገመግማሉ፡፡ በተጨማሪም የሕክምና ክትትል መርሃ ግብር ያዘጋጃሉ፡፡ ስለዚህም ለታካሚዎች በግል የሚዘጋጅ እና ከአንዱ ስፔሻሊስት ወደ ሌላ በመምራት ሳይጉላሉ ሁሉን አቀፍ የሕክምና የሚያገኙበት ነው፡፡ የእኛ የሕክምና አቀራረብ ለእያንዳንዱ ታካሚ ከፍተኛ ከህመም የመዳን ስኬት እና የተሻለ ህይወት ጥራት እንዲያገኙ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ቢሮአችን ያግኙ።

የ49 አመቱ ሰርቢያዊ ሚሮስላቭ የፊኛ ካንሰር እንዳለበት ታወቀ። በቤልግሬድ እና በዛግሬብ የተለያዩ ምርጥ ዶክተሮች እና የተሻሉ የተባሉ የሕክምና አማራጮችን ለማግኘት ቻሎ ነበር፡፡አንድ ቀን፣...
20/11/2023

የ49 አመቱ ሰርቢያዊ ሚሮስላቭ የፊኛ ካንሰር እንዳለበት ታወቀ። በቤልግሬድ እና በዛግሬብ የተለያዩ ምርጥ ዶክተሮች እና የተሻሉ የተባሉ የሕክምና አማራጮችን ለማግኘት ቻሎ ነበር፡፡
አንድ ቀን፣ በአጋጣሚ በኢንስታራም ላይ ማስታወቂያ ተመለከተ፡፡ ማስታወቂያው በቱርኪዬ በሚገኘው የአቺባደም ሆስፒታል የዩሮሎጂ ፕሮፌሰር በሆኑት ሙስጠፋ ሶፊከሪም ላይ ነበር። ወዲያው ቅጹን ሞልቶ ከፕሮፌሰር ሶፊከሪም ጋር ምክር ለማግኘት ቀጠሮ ያዘ። "" ፕሮፌሰር ሙስጠፋ ሶፊከሪምን በአካል አግኝቼ ስሀመሜ እና ስለ ህክምናዬ ጥልቅ ውይይት ካደረግኩ በኋላ ኢስታንቡል ወደሚገኘው አቺባዳም ሆስፒታል ለመሄድ እንዲሁም ህክምና ለማድረግ balሙሉ ተስፈኛ ነበርኩ" ሲል ሚሮስላቭ ተናግሯል።
የሚሮስላቭ የህክምና ጉዞ በአቺባደም ሆስፒታል ተጀመረ። የታመመውን ፊኛውን ለማስወገድ ቀዶ ጥገና ተደረገ፡፡ ፊኛው ከተወገደለት በኋላ የትናንሽ አንጀት ክፍልን በመጠቀም አዲስ የሽንት ከረጢት ለማበጀት የቀዶ ጥገናው ሂደት ተከተለ። አጠቃላይ ሂደቱ 6 ሰዓት ያህል የወሰደ ሲሆን ቀዶ ጥገናውም በጣም የተሳካ ነበር:: “ከቀዶ ጥገናው በኋላ ያለውም ሂደት መልካም ነበር፡፡ ምንም ዓይነት ኬሞቴራፒ ወይም ራዲዮቴራፒ አንሰጠውም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ላሉት አይነት እጢዎች በጣም የተሳካው ህክምና ራዲካል ሳይስቴክቶሚ ነው:: እናም ፊኛው ከተወገደ በኋላ ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አያስፈልግም" ያሉት የዩሮሎጂ ፕሮፌሰሩ ሙስጠፋ ሶፊከሪም ናቸው፡፡ ተጨማሪ የሕክምና አስተያየት በነጻ ለማግኘት አዲስ አበባ የሚገኘውን የመረጃ ጽህፈት ቤታችንን ያነጋግሩ።

በካንሰር የተጠቃውን ፊኛ ካስወገዱ በኋላ ሽንትን ለማከማቸት እና ከሰውነት ውስጥ ለማውጣት ሌላ መንገድ ማበጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ሁለት አማራጮች አሉ:: እነዚህም (Urostomy) ሽንት...
13/11/2023

በካንሰር የተጠቃውን ፊኛ ካስወገዱ በኋላ ሽንትን ለማከማቸት እና ከሰውነት ውስጥ ለማውጣት ሌላ መንገድ ማበጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ሁለት አማራጮች አሉ:: እነዚህም (Urostomy) ሽንት በተፈጥሯዊው ቱቦ ሳይሆን በቀዶ ጥገና ማስወገድ እና (Neobladder) ተተኪ ፊኛ ማበጀት ናቸው፡፡
• Urostomy ሽንት ከሆድ ውጭ በሚገጠም ልዩ ከረጢት ውስጥ ይሰበሰባል:: ከከረጢት ጋር መኖር በታካሚዎች የዕለት ተለት ህይወት እና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል::
• Neobladder በታማሚው አንጀት ውስጥ የሚገኙ ሕብረ ህዋሳት በመጠቀም አዲስ ፊኛ መገንባት ሲሆን ይህም ሰው ሰራሽ የሽንት ማጠራቀሚያ ከረጢት የግድ አስፈላጊ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ይህም ለታካሚዎች መደበኛ የሆነ የሽንት ማስወገድ (በተለመደው መንገድ መሽናት) ያስችላቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቀዶ ጥገና ውስብስብ በመሆኑ የባለሞያዎችን ከፍተኛ ችሎታ እና ልምድ ይጠይቃል፡፡ አዲስ ፊኛ መልሶ ማበጀት ከትንሹ አንጀት ውስጥ የተወሰነውን ክፍል በመጠቀም አዲስ ፊኛ መፍጠር እና ከዋናው ፊኛ ይልቅ በማስቀመጥ እንዲሁም የሽንት ቱቦዎችን ወደ አዲሱ ፊኛ የላይኛው ክፍል ጋር መስፋትን ያካትታል። ስለዚህ ሽንት ከኩላሊቶቹ ውስጥ በሽንት ቱቦዎች በኩል ወደ አዲሱ ከረጢት በመውጣት ተከማችቶ ታካሚው እንደተለመደው መሽናት ይጀምራል፡፡
በአቺባደም እንደ መጀመሪያ አማራጭ ለእያንዳንዱ ታካሚ እንደተገቢነቱ የአዲስ የሽንት ከረጢት መልሶ ግንባታን እንተገብራለን። በአለም ዙሪያ ላሉ የፊኛ ካንሰር ታማሚዎች የአዲስ ፊኛ መልሶ ግንባታ የሚያካሂዱ በቁጥር ውስን ማዕከላት አሉ። በዚህ ምክንያት፣ ብዙ ታማሚዎች ይህን ሕክምና ለማግኘት አቺባደምን ይጎበኛሉ። ስለ ህክምናው የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ የአቺባደምን በአዲስ አበባ የመረጃ ፅህፈት ቤት እንዲያነጋግሩ እናበረታታዎታለን።

06/11/2023

ለፕሮስቴት የተለየ አንቲጅን (PSA) ምርመራ በደም ውስጥ ያለውን የ PSA መጠን የሚለካ የደም ምርመራ ነው። PSA በፕሮስቴት አመንጪ እጢ የሚመረት ንጥረ ነገር ነው። በደም ውስጥ ያለው የ PSA መጠን ከፍ ያለ ሆኖ ሲገኝ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎች በፕሮስቴት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሌሎች ሁኔታዎች የ PSA መጠን መጨመር ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በተለምዶ ከፍ ያለ የ PSA ደረጃ ከፍ ያለ የፕሮስቴት ችግር መኖሩን ይጠቁማል። ሆኖም ዕድሜ እና የዘር ሀረግን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶች በPSA መጠን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ልብ ሊባል ይገባል። በተጨማሪም የPSA መጠን በግለሰቦች መካከል ሊለያይ ይችላል፡፡ አንዳንድ የፕሮስቴት እጢዎች ከሌሎች የበለጠ PSA ያመርታሉ። ተጨማሪ የህክምና አስተያየትን ለማግኘት የደም ምርመራ ውጤቱን ወደ ባለሙያዎቻችን ይላኩ።

Address

ቦሌ መድሃኒአለም አንበሳ ባንክ ህንፃ አንደኛ ፎቅ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Acıbadem Hospitals Group Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Acıbadem Hospitals Group Ethiopia:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category