
01/09/2021
ደስታ፣ አሸናፊነት እና ስኬት አዕምሮ አላቸው!
#ራዕይ:- ብሩህ እና ጤናማ አዕምሮ ያለው ማሕበረሰብ በመፍጠር ደስተኛ፣ አሸናፊና ስኬታማ የሆነ ኑሮ እንዲኖር ማስቻል
#ራዕያችን በሶስት (3) ክፍሎች ሊገለፅ ይችላል
#ጠንካራ አዕምሮ :- የሚያጋጥሙንን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በድል እንድንወጣ የሚረዳ ነው
የራስን የማጥፋት፣ የወንጀል ፣ የሱስ፣ የፍቺ፣ የስንፍናና ሌሎች ችግሮች ዋና ምክንያት የሆነውን ደካማ ልብ (አዕምሮ ) በስልጠናና ማማከር በማጠንከር ማሕበረሰቡ የላቀ ህይወት እንዲመራ ለማገዝ ይረዳል
#ራስን መግራት(መግዛት ):- ተገቢ ባልሆነ ስሜታዊነት ምክንያት የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመከላከል ያግዛል ::
ሁሉንም ፍላጎቶታችንን ማሟላት ስለማንችል ራስን ስለ መግዛትና መግራት መማርና መሰልጠን ለአሸናፊ ፣ ደስተኛና ስኬታማ ህይወት ይግዛል::
#ለውጥና ተገዳዳሪ መንፈስ
የራስን መለኪያ መስበር የለወጥና የተገዳዳሪነት መጀመሪያ ነው። ይህ ከራስ ይልቅ የሌላውን ስሜት እና ፍላጎት ለመረዳት እና ለማስቀደም የሚደረግ ተግባር ደስታን ይፈጥራል ።
የሌሎችን ተሞክሮ በማነሳሳት ለውጥ ይከሰታል እንዲሁም ተሰጥኦ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ለመቀስቀስና ለማሰልጠን ይጠቅማል ።
# ተልዕኮና ግብ
ብሩህ እና ጤነኛ አዕምሮ በመፍጠር ደስተኛ፣ አሸናፊና ስኬታማ ማህበረሰብ መፍጠር።