Abdu nasir

Abdu nasir No health with out mental health !

03/04/2024

ቤጉማ
====
የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ካልተጫወቱ ይጨንቃቸዋል፡፡
ሲጫወቱ ደግሞ የበለጠ ይጨንቃቸውና ከፍ ባለ ገንዘብ
ይጫወታሉ፡፡ አንዳንዴ በቁማሩ ምክኒያት ገንዘብ እያባከኑ ወይም
ከቤተሰብ ጋር እየተጣሉም መጫወታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንዴት
እንደሚያስቡ ካልተረዳን ድርጊታቸው ትርጉም አይሰጥም፡፡
የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች የሚስቡበት መንገድ በጥቂቱ፦
ሲያሸንፉ በችሎታ ነው፤ ሲሸነፉ በእድል ነው፡፡
-------------------------------------------------------
ችሎታ የሚያስፈልጋቸው የቁማር ጨዋታዎች አሉ፡፡ እንደ ፑል
ወይም አንዳንድ የካርታ ጨዋታዎች፡፡ ወይም እውቀት የሚፈልጉ
ውርረዶች እንደ የስፓርት ውድድሮች፡፡ ነገር ግን የፈለገ ችሎታ
ቢጠይቁ ሁሉም የቁማር ጨዋታዎች እድል ይፈልጋሉ፡፡
ማሸነፍም መሸነፍም ውስጥ ከችሎታ በተጨማሪ( አንዳንድ
ጨዋታዎች ላይ ሙሉ በሙሉ) እድል አለ፡፡ የቤቲንግ ሱስ
ያለባቸው ሰዎች ግን ሲያሸንፉ በችሎታ፣ ሲሸነፉ ግን በእድል
እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡
መርጦ ማስታወስ፦
------------------------
የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ያሸነፉባቸውን ጥቂት ጨዋታዎች
ጥርት አድርገው ሲያስታውሱ የተሸነፉባቸውን ብዙ ጨዋታዎች
ይረሳሉ፡፡ በተጨማሪም 'ለጥ..ቂት!' የተሸነፉትን እንዳሸነፋ
አድርገው ነው የሚያስታውሱት፡፡ ይህ የወደፊቱን ጨዋታ
የማሸነፍ እድላቸውን ሲያሰሉ በተዛባ መንገድ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡ "ሁሉንም ልክ ነበርኩ። ማንቺስተር ባይሸነፍ 20ሺ
በላ ነበር" ይላሉ።
ዞሮ ዞሮ የተበሉትን ያስመልሳሉ፦
----------------------------------------
የተወሰነ ጨዋታ ቢበሉም ቁማሩን ከፍ ባለ ገንዘብ እስከቀጠሉ
ድረስ የተበሉትን እንደሚያስመልሱ ያስባሉ፡፡ በዚህ ምክኒያት
ለሌላ ሰው የሚያስደነግጥ ብር እየተበሉም ምንም
አይመስላቸውም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ከተሸነፉ እድል
ወደ እነሱ እንደምታዘነብል ያምናሉ፡፡ (they commit Monte
Carlo fallacy) ልክ አንድ ልጅ ሲወለድ ሴት ወይም ወንድ
የመሆን እድሉ ግማሽ ለ ግማሽ ቢሆንም ከዚህ በፊት ሁለት
ሴቶች መውለድ የሚቀጥለውን ወንድ የመሆኑን አድል
የሚጨምረው እንደሚመስላቸው ሰዎች፡፡
ስለ ቤቲንግ ሱስ ፌስቡክ ላይ መረጃ ስፈልግ አንድ ግሩፕ
አጋጠመኝ። ቤጉማ ይባላል። 26 ሺ አባላት አሉት። የቤቲንግ
ጉዳተኞች ማህበር ማለት ነው። የቤቲንግ ሱስ የሚታከም
የአእምሮ ህመም ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/04/2024

የንግግር የስነ ልቦና ህክምና እንዴት ነው የሚሰጠው?
=================================
የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ስንሰጥ ለታካሚ "ምን ማድረግ
እንዳለብህ አውቃለሁ፤ ልንገርህ።" የምንል የሚመስላቸው
ሰዎች አሉ። የምንለው ግን በተቃራኒው ታካሚን "ምን ማድረግ
እንዳለብህ ታውቃለህ፤ ንገረኝ።" ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ
የተለያዩ የስነ ልቦና ህክምና አይነቶች ቢኖሩም አሰራራቸው
በሶስት ደረጃዎች ሊጠቃለል ይችላል።
1) ታካሚው ጭንቀት የሚፈጥሩበት የህይወቱ ክፍሎችን
መመርመር የሚችልበት ሁኔታ ማመቻቸት፦ የጭንቀቱ ምንጭ
አስተዳደጉ ወይም አሁን ያለበት ሁኔታ፤ ከሰዎች ጋር ያለው
ግንኙነት ወይም የሚያስብበት መንገድ ሊሆን ይችላል። እዚህ
ደረጃ ላይ የሀኪሙ ሚና መደገፍ፣ ማበረታታት እና በጣም
አልፎአልፎ መጠቆም ነው። ብዙ ሰዎች ስለ ጭንቀት ለጓደኛ
ወይም ለቤተሰብ ሲያወሩ ንግግራቸውን ሳያስጨርሱ ጓደኛቸው
አቋርጦ መፍትሄ ይጠቁማቸዋል። የንግግር ህክምና ላይ ግን
መጀመሪያ ላይ ጊዜ ሰጥተን እናዳምጣለን።
2) ግንኙነቶችን እንዲረዳ ማገዝ፦ አስተዳደጉና አሁን ባለበት
ሁኔታ እንዲሁም በሀሳብ ስሜትና ፀባይ መካከል ያለውን
ግንኙነት እንዲገነዘብ ማገዝ። እዚህ ደረጃ ላይ የሀኪሙ ሚና
ነገሮችን በታካሚው አይን ለማየት መሞከርና ታካሚ ሀሳቡንና
ስሜቱን እንዲገልፅ ማገዝ ነው። ስለ ሰዎች ማንነት የምንረዳው
በአብዛኛው የሚያወሩትን ሰምተን ነው። ስለራሳችን ለመረዳትም
ስለራሳችን የምናወራውን መስማት አለብን። የስነ ልቦና ህክምና
ላይ ስለአጋጠመን ነገሮች፣ ስለ አስተዳደጋችን፣ ስለፍቅር
ግንኙነታችን በጥሞና ለሚያዳምጥ ሰው ስለምናወራ ስለራሳችን
ማንነት የተሻለ እንረዳለን።
3) አማራጭ መንገድ፦ ታካሚው የጭንቀትና ሌሎች አሉታዊ
ስሜት ትክክለኛ ምክኒያት ከተረዳ "የሁኔታዎች ውጤት ነኝ!"
ከማለት ወጥቶ "የውሳኔዬ ውጤት ነኝ!" ማለት ሲችል ጭንቀት
የሚቀንሱ አማራጭ መንገዶች ማሰብ ይጀምራል። የተወሰኑትን
በተግባር ለውጦ ይሞክራል። ከዛ ውጤት ካገኘበት ይበልጥ
እያሻሻለው ይሄዳል።
አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች በንግግር የስነ ልቦና ህክምና ብቻ
መታከም ይችላሉ። ለአንዳንዶቹ ደግሞ ከመድሀኒት ጎንለጎን
ይሰጣል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/04/2024

Intern (የህክምና ትምህርት የመጨረሻ አመት ተማሪ)ነኝ።
ግቢ የገባሁት 2004ዓም ነው። እስከአሁን እንዴት
አልጨረስክም ልትሉኝ ትችላላችሁ። እኔ ግን እስከአሁን
ያልጨረስኩት በጤና መታወክ ነው። ከPc-1 ወደ Pc-2 አልፌ
ትንሽ እንደተማርኩ Bipolar disorder diagnosed ተደረኩ።
Exam ላይ ስለነበርኩ ለጤናዬ ትኩረት አልሰጠውም። ነገር
ግን ከጤናዬ ሳልሆን ፈተናውንም በትክክል ሳልፈተን ቀረሁ።
ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ እኔና Forced withdrawal
ተግባብተን መኖር የጀመርነው። Intern እስክሆን ብዙ
challenge የሚያደርጉ ጊዜዎችን አሳልፌያለሁ። Sodium
valproate ለ 8 አመት ወስጃለሁ፤ ግን በመሀል ብዙ ጊዜ
አቋርጫለሁ። "ምክንያቱም ብዙ መድሀኒቶች Public
pharmacy ሳይኖሩ ያሉት Private pharmacy ላይ ነው"
private ደግሞ ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።
የሚመለከተው ባለ ድርሻ አካል ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠን
እጠይቃለሁ።
"ያለ አእምሮ ጤና ጤና የለም "
Dr.Israel W/yohannes(Intern)

03/04/2024

የራስን ስነ ልቦና መመርመር
==================
የስነ ልቦና አባት በመባል የሚታወቀው ቪልኸልም ቩንት
(Wilhelm Wundt) ካበረከታቸው ነገሮች ሀሳብንና ስሜትን
በመመርመር ስነ ልቦናን የመረዳት መንገድ (Interospection
) ዋነኛው ነው።
ይህንን ዘዴ በንግግር የስነ ልቦና ህክምናም በብዛት
እንጠቀምበታለን። ሰዎች ስለ ስሜቶቻቸው፣ ሀሳቦቻቸውና
ድርጊቶቻቸው ግንዛቤ እንዲኖራቸውና አዳዲስ ስነ ልቦናዊ
ሙከራዎችን (Experimental self-observation)
እንዲያደርጉ ለማስቻል። ሁሉም ሰው ልዩ ነው። ያለበት ሁኔታ፤
የሚያጋጥመው ችግርም እንደዛው። ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው
ሊሰራ የሚችለውን ዘዴ ሊያውቅ የሚችለው ግለሰቡ ራሱ ነው።
የንግግር ህክምና አላማም ሰዎች የሚሰራላቸውን ዘዴ
እንዲያመጡ ማገዝ ነው።
የራስን ስነልቦና መመርመር መብሰልሰል ማለት አይደለም።
መብሰልሰል ስለ አንድ ነገር እየደጋገሙ ማሰብ ሲሆን በአሉታዊ
ስሜቶች የተሞላ ስለሆነ ጉዳት ያስከትላል።የራስን ስነ ልቦና
መመርመር ግን ነጻና ከፍረጃ ውጭ ትውስታን፣ ስሜትን፣ ፀባይን
በመመርመር ራስን ወደ መገንዘብ የሚደረግ ጉዞ ነው። ለብዙ
ጥያቄዎቻችን መልሱ ያለው ውስጣችን ነው።
አንድ ቡድሂስት መነኩሴ አሜሪካ ይሄዳል። የ7 ዶላር በርገር
ገዝቶ ለበርገር ሻጩ 10 ዶላር ሰጥቶ መልስ ቢጠብቅ ዝም
አለው። ቢጠብቅ ዝም አለው። በመጨረሻ " መንድም መልስ
ስጠኝ!" ሲለው በርገር ሻጩ " ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልስ
የምታገኘው ከውስጥህ ነው።" ብሎ መለሰለት።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/04/2024

"ጭራሽ መልስ ትመልስልኛለህ?!"
=====================
ገነነ ህፃን እያለ ጥፋት ሲያጠፋ አባቱ እየገረፈው ለምን
እንዳጠፋ ይጠይቀዋል። ገነነ እንባውን እያዘራ ዝም ብሎ
ይቆማል። አባቱ "ምን ይዘጋሀል?" እያለ ግርፊያውን ይቀጥላል።
ገነነ ቢጨንቀው ያጠፋበትን ምክኒያት መናገር ሲጀምር አባቱ
"ጭራሽ መልስ ትመልስልኛለህ?!" ብሎ የግርፊያውን ሀይል
ይጨምራል። ግርፊያው ካለቀ በኋላ እራት ይቀርባል። ገነነ
እያለቀሰ ነው። ወላጆቹ "ዋጣት እና አርፈህ እራትህን ብላ"
ብለው ይቆጡታል።
ገነነ አሁን ትልቅ ሰው ሆኖ የሆነ መስሪያ ቤት ውስጥ ኤክስፐርት
ሆኖ ይሰራል። አለቃው ስራ ሰጥቶት ሰርቶ ሲያስረክብ "እንደዚህ
አልነበረም መስራት የነበረብህ!" ብሎ ሲቆጣው በትክክል
እንደሰራ ቢያውቅም "እሺ" ብሎ ይወጣል። ነገር ግን "በትክክል
እኮ ነው የሰራሁት" ብሎ ባለማስረዳቱ ይናደዳል። እንደተናደደና
በምን እንደተናደደ ሳያውቅ ጭንቀት ውስጥ ይገባል።
በባህላችን አሉታዊ ስሜቶችን ማለትም ሀዘን፣ ንዴት ...ወዘተ
መግለፅ አይበረታታም። በዚህ ምክኒያት ስሜት የምንገልፅባቸው
ቃላት ውስን ናቸው። ስሜትን መግለፅ የሚያበረታቱ ቋንቋዎች
ውስጥ ለንዴት እንደየደረጃው ብዙ ቃላት አላቸው። ለምሳሌ
በእንግሊዘኛ ከትንሽ ንዴት እስከ ትልቅ ንዴት Annoyed,
frustrated, irtitated, exasperated, mad, outraged,
furious, livid ሊባል ይችላል።
ንዴት፣ ሀዘን የመሳሰሉት አሉታዊ ስሜቶች በቃላት የሚገለፁበት
መንገድ ካልተመቻቸ በአካላዊ ምልክቶች እንዲገለፁ
እንገፋቸዋለን። "ጭንቅላቴ ተቃጠለ፤ ፀጓራዬ ተላጠ" የሚባሉት
ምልክቶች አንዳንዴ ስነ ልቦናዊ የጭንቀት መገለጫዎች ሊሆኑ
ይችላሉ። ብዙ ሰዎች ንዴታቸውን መግለፅ ስለሚከብዳቸው
ለራሳቸው ይዘውት ይጨነቃሉ። የስነ ልቦና ህክምና ስሰጥ ብዙ
ሰዎች የሚያሳዝን የህይወት ገጠመኛቸውን እየነገሩኝ ያለቅሱና
"ይቅርታ ረበሽኩህ" ይላሉ። የስነ ልቦና ህክምና ላይ ሰዎች
ንዴታቸውን፣ ሀዘናቸውን ሲነግሩን ለመስማት ዝግጁ ነን።
እንደውም እናበረታታቸዋለን።
እንደ ገነነ ወላጆች አይነት ሲፋጅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ
የልጅ አስተዳደግ (Double-bind parenting) የልጆች ስነ
ልቦና ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳድራል። በመጨረሻ በከፍተኛ ንዴት
የሚሰማቸው ሰዎች የስነ ልቦና ባለሞያ ወይም የአእምሮ ሀኪም
ቢያማክሩ ሞያዊ እገዛ ማግኘት ይችላሉ። ወላጆች ደግሞ
ልጆቻቸው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ስሜትን እንዲገልፁ
ማበረታታት እንዲሁም ስሜታቸውን የሚገልፁበት ቃላት
ማስተማር ወሳኝ ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/04/2024

"የአማኑኤል ካርድ አለኝ፤ የፈለግኩትን ባደርግህ አልጠየቅም!!"
=============================
ጥል ወይም አለመግባባት ሲፈጠር "የአማኑኤል ካርድ ስላለኝ፤
በህግ አልጠየቅም፤ በኋላ እንዳይቆጭህ!" የሚሉ ሰዎች እንዳሉ
ሰምቻለሁ። ወንጀልና የአእምሮ ህመም ያላቸውን ግንኙነት
እንዲሁም "የአእምሮ ህመም ስላለብኝ ነው ወንጀሉን
የፈፀምኩት" የሚሉ ሰዎች አማኑኤል ሆስፒታል እንዴት
እንደሚስተናገዱ እንሆ፦
ከአእምሮ ህመም ጋር የተያያዙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያጠናው
የአእምሮ ህክምና ዘርፍ Foriensic psychiatry ይባላል።
በዚህ የአእምሮ ህክምና ዘርፍ ሁለት አንኳር ጉዳዮች ይታያሉ።
የመጀሪያው የፍርድ ሂደትን መከታተል መቻል አለመቻል።
Ability to stand trial. ምክኒያቱም አንድ ግለሰብ በአእምሮ
ህመሙ ምክኒያት ፍርድ ቤት በተገቢው ሁኔታ መናገር ካልቻለ
ወይም ያልተገባ ፀባይ ካሳየ ፍ/ቤት በመድፈር (Contempt of
court) ቅጣት ይበየንበታል። ስለዚህ ተከሳሽ ፀባዩ
የሚያጠራጥር ሲሆን ይላክና የፍርድ ሂደቱን መከታተል ይችላል
ወይም አይችልም የሚለው ተወስኖ መልስ ይሰጣል።
ሁለተኛው የወንጀል ሀላፊነት(Criminal responsibility)
ነው። አንድ ሰው የአማኑኤል ካርድ ስላለው ከወንጀል ሀላፊነት
እንዲያመልጥ አይደረግም። መጀመሪያ ህመም እንዳለበትና
እንደሌለበት ይጣራል። በመቀጠል ያለበት ህመም ከባድ ነው
ወይስ ቀላል የሚለው ይለያል። ከባድም ቢሆን ከተጠያቂነት
ለማምለጥ በቂ አይደለም። በመጨረሻም ወንጀሉ በተፈፀመበት
ወቅት የነበረበት የአእምሮ ሁኔታ መስቀለኛ መረጃዎች
በመውሰድ ይገነባል። ይሄ ሲሰራ አጭበርብረው የአእምሮ
ህመም እንዳለባቸው የሚያስመስሉ ሰዎችን ለመለየት የተለያዩ
ዘዴዎችን እንጠቀማለን።
እነዚህን ሁሉ ካሟላ ለፍ/ቤት ሞያዊ አስተያየት
(Professional opinion) ይላካል። ሆኖም አስተያየቱን
ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር አስተያይቶ የሚወስነው ፍ/ቤት ነው።
በሀገራችን ያለው የወንጀል አእምሮ ምርመራ ወረፋ ረጅም
ነው። አመት ሁለት አመት ሊፈጅ ይችላል። "የአእምሮ ህመም
ስላለብኝ ነው" ብሎ ለማምለጥ የሚያስብ ሰው አማኑኤል ወረፋ
እስኪደርሰው ታስሮ ነው የሚጠብቀው። ቢታሰር ቅጣቱን ጨርሶ
በ6ወር መውጣት እየቻለ "የአእምሮ ህመም ስላለብኝ ነው።"
ብሎ አመት ከ6ወር የታሰረ ሰው አጋጥሞኛል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

05/06/2022
አስቸጋሪ ጊዜያት እና ቀልዶች (ኮሮና የመጣ ጊዜ የተቀለዱ)=====================================በአስቸጋሪ ጊዜያት ቀልዶች እንደ ስነ ልቦናዊ የህመም ማስታገሻያገለግላሉ።...
13/04/2022

አስቸጋሪ ጊዜያት እና ቀልዶች (ኮሮና የመጣ ጊዜ የተቀለዱ)
=====================================
በአስቸጋሪ ጊዜያት ቀልዶች እንደ ስነ ልቦናዊ የህመም ማስታገሻ
ያገለግላሉ። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይሁዳውያን
ብዙ ቀልዶች እየፈጠሩ አስጨናቂውን ጊዜ ቀለል እንዲል
ለማድረግ ይሞክሩ ነበር። አንዷን እነሆ፦
አንድ አይሁድ 'አዋቂ' ጋር ይሄድና ጀርመኖች መቼ እንደሚሸነፉ
ይጠይቃል። 'አዋቂውም' በአንድ የአይሁድ አመት በአል እንደሆነ
ይነግረዋል። አይሁዱም "የትኛው አመት በአል?" ብሎ ሌላ
ጥያቄ ያሰከትላል። አዋቂውም "መቼም ቀን ጀርመኖች ይሸነፉ፤
ያን ቀን ለአይሁዶች አመት በአል ነው።" ብሎ መለሰለት።
ሲግመን ፍሮይድ Jokes and their Relations to the
Unconscious በሚለው መፅሀፉ ላይ አስቸጋሪ ነገሮች ላይ
ስንቀልድ ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮችን በትንሹም ቢሆን
የመቆጣጠር ስሜት እንዲሰማን ያደርጉናል ብሏል። "...it is
striking back or taking control. It is a poor
substitute but it may be all that is available...
ለማንኛውም ጥቂት የኮሮና ቀልዶች፦
1)ሰዎች በፊት ጉንፋን ሲይዛቸው "አሞኛል፤ ከቤት መውጣት
አልፈልግም። ጥቅል...ል ብዬ ተኝቼ ነው የምውለው።"
ኮሮና የያዛቸው ሰዎች "አሞኛል ግን ቤት መዋል ስለሚደብር
ሀይገር ተሳፍሬ፣ ስታዲየም ገብቼ ኳስ አይቼ፣ ዕድር ደረስ ብዬ፣
እግረ መንገዴን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳትፌ ብመጣ ደስ
ይለኛል።
2) አሜሪካ ኮሮና ሲመጣ ብዙ ሶፍት ገዝተው ሶፍት ከገበያ ላይ
እንዲጠፋ ያደረጉት ሰዎች መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ይነዱ የነበሩ
ሰዎች እንደሆኑ በጥናት ተረጋግጧል።
3) ጭንቀት በተሰማኝ ቁጥር ጭንቀቱን ለመቀነስ ጥቂት
ኪሎሜትሮች ሮጣለሁ። አሁን አርበጉና ደርሻለሁ። ወደ ቤቴ
እንዳልመለስ 'ትራንስፖርት' የለም።
4) ቤት ለመቀመጥ ተቸግረዋል? እንግዲያውስ ቅንድብዎን
ይላጩ።
5) አሁን ሁሉም ሰው እጁን እየታጠበ ስለሆነ መንገድ ላይ
የሚሸጠው ቆሎ ጣእሙ ጠፍቷል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

በቫያግራ ምክኒያት በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች ሞተዋል!!!!=============================ለስንፈተ ወሲብ የሚወሰደው በተለምዶ ቫያግራ የሚባለውመድሀኒት ምክኒያት በአለማችን በሺህ ...
13/04/2022

በቫያግራ ምክኒያት በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች ሞተዋል!!!!
=============================
ለስንፈተ ወሲብ የሚወሰደው በተለምዶ ቫያግራ የሚባለው
መድሀኒት ምክኒያት በአለማችን በሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች
ሞተዋል። ሆኖም የመድሀኒት ሸያጩ በሀገራችን ተጧጡፏል።
"ያሉበት ድረስ እናመጣለን።" የሚሉ ማስታወቂያዎች
በማህበራዊ ሚዲያ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም።
ቫያግራ (Sildenafil citrate) ሲጀመር የልብ መድሀኒት ነበር።
የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች ደግሞ ለስንፈተ ወሲብ
የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ይላል። ሲልዴናፊል ብልት እንዲቆም
የሚያደርገው የደም ዝውውርን በመለወጥ ወደ ብልት ብዙ ደም
እንዲገባ የገባው ደግሞ እንዳይወጣ በማድረግ ነው። ይህ
ለውጥ ደግሞ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይም ተፅእኖ
ያመጣል።
ቫያግራ የሚጠቀሙ ሰዎች ራስ ምታት፣ የጨጓራ ህመም፣
የጀርባ ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ከሁሉም የሚያስፈራው
ግን ድንገት የደም ግፊት ዝቅ ብሎ የልብ ምት መቋረጥ ነው።
በአለማችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ምክኒያት
ህይወታቸውን አጥተዋል።
ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲኖሩ በዘፈቀደ ቫያግራ
ከመግዛት በተገቢው ሁኔታ ተመርምሮ ትክክለኛውን ህክምና
ማድረግ የተሻለ ነው። ማስታወስ የሚያስፈልገው ወሳኙ ጉዳይ
አብዛኞቹ ከወሲብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ስነ ልቦናዊ መንስኤ
እንዳላቸው ማወቅ ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ዩዴሞኒያ 15 - ካንሰር የለወጠው ጀግና አሊ በናት===============================አውስትራሊያዊው አሊ በናት የህይወት ዘዬው እጅግ ቅንጡ የሆነወጣት ሚሊየነር ነበር። የሚነዳ...
09/04/2022

ዩዴሞኒያ 15 - ካንሰር የለወጠው ጀግና አሊ በናት
===============================
አውስትራሊያዊው አሊ በናት የህይወት ዘዬው እጅግ ቅንጡ የሆነ
ወጣት ሚሊየነር ነበር። የሚነዳቸው መኪናዎች እያንዳንዳቸው
ከሀያ ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያወጣሉ። ጫማዎቹን ሀያና ሰላሳ
ሺዎች አውጥቶ ነው የሚገዛው። ይታመምና ካንሰር እንዳለበት
ይነገረዋል። ካንሰሩ ደግሞ ወደ ሰውነቱ ተሰራጭቷል....አሊ
በናት ስለህይወት ያለው አተያይ ተለወጠ።
ዱኒያ ምንም ቢያምር ዱኒያ እንደሆነ ተገነዘበ። ወድ መኪናዎቹ
ትርጉም የለሽ እንደሆኑ ቅንጡ ጌጣጌጦቹም ረብ እንደሌላቸው
ተረዳ። ያለውን እያንዳንዷን ገንዘብና የቀረውን እያንዳንዷን
ሰኮንድ ለሰዎች መልካም በማድረግ ለማሳለፍ ወሰነ።
ንብረቶቹን ሸጦ ለደሀ አፍሪካውያን ትምህርት ቤት መስራት
ጀመረ። አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለ ህመሙ ሲጠየቅ
"አልሀምዱሊላህ አላህ ካንሰር የተባለ ስጦታ ሰጥቶኛል። ትልቅ
ስጦታ ነው። በዱኒያ ተጋርዶ የነበረው አይኔ አሁን ተከፍቷል።"
ብሏል። አሊ በናት ያለውን ንብረት በመለገስ ብቻ አላበቃም።
ሌሎችም የእሱን ፈለግ እንዲከተሉ በማስተባበር ብዙ ት/ቤት
እንዲሰሩ አድርጓል። አሊ "አንድ የተቸገረ ልጅ ፈገግ እንዲል
ከማገዝ በላይ ምን ደስታ አለ?" ይላል።
አሊ ከመሞቱ በፊት የቪዲዮ መልእክት ቀርፆ አስቀምጦ ነበር።
መልእክቱ ላይ "እመኑኝ ታማችሁ በዚህ ምድር ላይ ጥቂት ጊዜ
እንደቀራችሁ ስትረዱ በጭራሽ ገንዘብን አታሳድዱም። በህይወት
ውስጥ የእውነት አስፈላጊዎቹ ነገሮች ግልፅ ይሆንላችኋል።
ብንችል እያንዳንዱን ቀን በዚያ መረዳት መኖር ብንችል
መልካም ነው።" ብሏል
አሊ በናት በ2018 አልፏል። ነገር ግን የሚታወሰው ቅንጡ
ሚሊየነር ተብሎ ሳይሆን "መልካሙ፣ ለሰዎች አሳቢው አሊ"
ተብሎ ነው። እሱ የዘራው የመልካም ስራ ዘር በሌሎች ሰዎች
ውስጥ ፍሬ እያፈራ የብዙዎችን ህይወት እየለወጠ ነው።
ዩዴሞኒያ ለሁላችን!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ሱስ መጀመሪያ ላይ ደስ ይላል===================አብዛኞቹ ደስታ የሚፈጥሩ ነገሮች (ኳስ ማየት፣ መሳሳም፣ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ሱስ...ወዘተ) አእምሯችን ውስጥ VentralTegmental ...
06/04/2022

ሱስ መጀመሪያ ላይ ደስ ይላል
===================
አብዛኞቹ ደስታ የሚፈጥሩ ነገሮች (ኳስ ማየት፣ መሳሳም፣
ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ሱስ...ወዘተ) አእምሯችን ውስጥ Ventral
Tegmental Area የሚባለው ክፍል ውስጥ ዶፓሚን የሚባል
ንጥረ ነገር ሲለቀቅ የሚሰሙን ስሜቶች ናቸው። ብዙ ሰዎች
ለሙከራ፣ ለሙድ፣ ለጥናት፣ ለመዝናናት ....ወዘተ ብለው
ይጀምራሉ። ከዛ ግን አንዳንድ ሰዎች አእምሮ ውስጥ ለውጦች
ሲፈጠሩ ሱስ ህመም ይሆናል።
ቀስበቀስ ሱሱ ከማህበራዊ ህይወት፣ ከስራ፣ ከዝንባሌዎች፣
ከፍቅር ግንኙነት እየበለጠ ሌሎቹን እያስረሳ ይመጣል። በዚህ
ጊዜ ከቀላል ህመም ወደ ከባድ እየተሸጋገረ ነው። አሁን ሰዎቹ
ለመውጣት እያሰቡ መንገዱ ግን ይቸግራቸዋል። ማታ "ከአሁን
በኋላ አቆማለሁ" ይሉና ሰአቷ ስትደርስ እየተጣደፉ ወደ ሱስ
ይሄዳሉ። ሰአቷ ስትደርስ የምታንቀለቅለውና የምታጣድፈው
Anterior Cingulate Cortex የምትባለው የአእምሮ ክፍል
ናት። ይህቺ ክፍል ስለታመመች ኳስ፣ ሴክስ፣ እድር፣ እቁብ፣
ለቅሶ ...ወዘተ የመሳሰሉትን ታስረሳና ሱሱን ታጎላለች። እናም
ታጣድፋለች። የሱስ ሰአት የደረሰበት ሰው ብታናግሩት በሙሉ
ልብ አያዳምጥም። ነገሩን ካረዘማችሁት ሊነጫነጭ ግፋ ካለም
ሊጣላ ይችላል። ትእግስትንና ስሜትን የሚቆጣጠረው የአእምሮ
ክፍል Prefrontal cortex በሱስ ምክኒያት ስራውን ቀንሷል።
ሰዎች ሱስ ውስጥ የሚቆዩት አእምሯቸው ውስጥ በተከሰቱት
ለውጦች ምክኒያት ነው። መውጣት እየፈለጉም መውጣት
ያቅታቸዋል። ሱሱን አይፈልጉትም ግን እንዴት ይውጡ?
ወዳጆቻቸው "ሱስ ተው" ብለው ይመክሯቸዋል። ግን ለውጥ
የለም። ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚመክራቸውን ሰው እየሸሹ
ይሄዳሉ።
ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው። ህክምናው ግን ሂደት
ነው። አእምሮ ውስጥ በሱስ ምክኒያት የተከሰቱትን ለውጦች
ወደቦታቸው የመመለስ ሂደት ነው።
የሱስ ህክምና በአማኑኤል፣ ዘውዲቱ፣ ጳውሎስ፣ የካቲት
ሆስፒታሎች እንዲሁም በግል የአእምሮ ክሊኒኮች ይሰጣል።
መልእክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

የሴክስ ፍላጎት ልዩነት በፆታዎች====================በትዳር ውስጥ አለመግባባት ከሚፈጥሩ ጉዳዎች ዋናዎቹየገንዘብ አወጣጥ፣ የልጆች አስተዳደግ፣ ተነጋግሮአለመግባባት፣ የአማቶች ጣልቃ...
06/04/2022

የሴክስ ፍላጎት ልዩነት በፆታዎች
====================
በትዳር ውስጥ አለመግባባት ከሚፈጥሩ ጉዳዎች ዋናዎቹ
የገንዘብ አወጣጥ፣ የልጆች አስተዳደግ፣ ተነጋግሮ
አለመግባባት፣ የአማቶች ጣልቃ ገብነትና በሴክስ ዙሪያ
የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ምናልባትም በሴክስ
ዙሪያ የሚፈጠሩ ችግሮች ትልቅ ድርሻ ይይዛሉ።
በፆታዎች መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ችግሮች
እንዳይፈጠሩ ለማድረግ፣ ሲፈጠሩም ለመፍታት ስለሚረዳ
በKaplan & Sadock Synopsis of Psychiatry 11th
edition የተቀመጠው እንደሚከተለው ተተርጉሟል።
"የሴክስ ፍላጎት በሴቶችም በወንዶችም ላይ አለ። ስለ ሴክስ
ምን ያህል ጊዜያት ያስባሉ? ወይም ከሴክስ ጋር የሚያያዙ
ነገሮች ሲሰሙ/ሲያዩ ንቁ ይሆናሉ? የሚሉትን ከለካን በተፈጥሮ
ወንዶች ላይ ከፍ ብሎ ይታያል። በሁለቱም ፆታዎች ሴክስ
የሚያደርጉበት ምክኒያት በሴክስ ከሚገኘው ደስታ በተጨማሪ
በሌሎች ምክኒያቶች ሊሆን ይችላል። እነዚህ ተጨማሪ
ምክኒያቶች ከፍ ባለ ሁኔታ ሴቶች ላይ ይስተዋላሉ።
በሴቶች ላይ ከሚታዩት ተጨማሪ ምክኒያቶች ከአጋራቸው ጋር
ያለቸውን መቀራረብ ለማጠናከር፣ አጋራቸውን ለማስደሰት፣
አጋራቸው ወደ ሌላ እንዳይሄድ ለማድረግ ይጠቀሳሉ።
ሁለቱም ፆታዎች ላይ ለሴክስ እንዲነሳሱ የሚያደርጉ ነገሮች
ቢኖሩም አይነታቸው ልዩነት አለው። ወንዶች የተገለጠ ገላ
ሲመለከቱ ስሜታቸው የሚቀሰቀስ ሲሆን ሴቶችን 'ሮማንቲክ'
ሁኔታዎች ወይም ታሪኮች ስሜታቸውን ይቀሰቅሰዋል።"
በተጨማሪም አልጋ ላይ ያለው መግባባት ሌሎች ጉዳዮች ላይ
ያለውን መግባባት እንደሚወስነው ሁሉ በሌሎች ጉዳዮች ላይ
ያለው መግባባት እንዲሁ አልጋ ላይ ያለውን መግባባት
ይወስነዋል። በሴክስ ዙሪያ የሚፈጠሩ ችግሮች ሰዎች ላይ
ዲፕሬሽን፣ ጭንቀት እና የአእምሮ ውጥረት እንደሚያከስትሉ
ሁሉ በተገላቢጦሹም ትክክል ነው።
እነዚህ ችግሮች ለመፍታት በትዳር ውስጥ ግልፅ ውይይት
የሚያስፈልግ ሲሆን ጭንቀት የሚፈጥር ከሆነ የስነ ልቦና
ባለሞያ ወይም የአእምሮ ሀኪም በማማከር ሞያዊ እገዛ
ማግኘት ይቻላል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ሮቢን ዊሊያምስ በሰራባቸው ፊልሞች ሁሉ ላይ 10 ጎዳናተዳዳሪዎች ስራ እንዲያገኙ ያስደርግ ነበር። ከመቶ ሀምሳ በላይጎዳና ተዳዳሪዎች ከጎዳና ተነስተው ስራ እንዲያገኙ አድርጓል።ሮቢንን የአእም...
05/04/2022

ሮቢን ዊሊያምስ በሰራባቸው ፊልሞች ሁሉ ላይ 10 ጎዳና
ተዳዳሪዎች ስራ እንዲያገኙ ያስደርግ ነበር። ከመቶ ሀምሳ በላይ
ጎዳና ተዳዳሪዎች ከጎዳና ተነስተው ስራ እንዲያገኙ አድርጓል።
ሮቢንን የአእምሮ ህመም ነጠቀን እንጂ። ነፍስህ በሰላም ትረፍ
ሮቢን።

"በጭንቀት ምክኒያት ጨዋታ አምልጦኝ ያውቃል"=============================ጂያንሉዪጂ ቡፎን በስኬት ላይ ስኬት የተቀዳጀ በረኛ ነው።ህይወት ግን ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አልነበረ...
05/04/2022

"በጭንቀት ምክኒያት ጨዋታ አምልጦኝ ያውቃል"
=============================
ጂያንሉዪጂ ቡፎን በስኬት ላይ ስኬት የተቀዳጀ በረኛ ነው።
ህይወት ግን ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ታላቁ በረኛ
ድባቴና ፓኒክ አጋጥሞት ያውቃል። ሁኔታውን ሲያስታውስ
"ለመጀመሪያ ጊዜ ድባቴ (Depresssion) ያጋጠመኝ በሀያዎቹ
እድሜ እያለሁ ነው። የህይወት ትርጉም ጠፍቶብኝ ነበር።
በበረኛነቴ እንጂ በሰውነቴ ሰዎች የሚያስቡልኝ አልመስል አለኝ።
አንድ ቀን ከጨዋታ በፊት ከፍተኛ መሸበር (Panic attack)
አጋጠመኝ። አሰልጣኜን ዛሬ መጫወት አልችልም። አልኩት።
አሰልጣኞች አሪፍ በረኛ የሚሉት ምንም የማይፈራ ደፋር ሲሆን
ነው። እኔ በርግጥ ደፋር ነኝ። ነገር ግን አንዳንድ ቀን ከየት
እንደመጣ የማላውቀው ፍርሀት ይሰማኛል። ከቤት መውጣት
አልፈልግም። አልጋዬ ውስጥ ጥቅልል እንዳልኩ ውዬ ባድር
አመርጣለሁ።" ብሏል።
ቡፎን ክብር፣ ዝና፣ ገንዘብ አልጎደለውም። ነገር ግን የአእምሮ
ህመም ማንም ሰው ላይ ሊከሰት ስለሚችል እሱም
አጋጥሞታል። የድብርት ህመም መጥፎነቱ ካለህ ነገር ይልቅ
የጎደለህ ላይ እንድታተኩር ያደርግሀል። የሰራሀቸውን ጥሩ
ነገሮች አስረስቶ የተሳሳትከውን አንዲት ነገር እያስታወሰ ፀፀት
ይፈጥርብሀል።
ቡፎን የአለም ዋንጫን፣ ብዙ የጣሊያን ሴሪ አ ዋንጫዎች፣
በተደጋጋሚ የኮፓ ኢታሊያን ክብር ቢያነሳም ድባቴ ውስጥ ሲሆን
አእምሮው እነዚህን በዜሮ አባዝቶ ያላሳካውን የሻምፒዮንስ ሊግ
ዋንጫ ሊያሳየው ይችላል።
ቡፎን ተገቢውን የአእምሮ ህክምና ስላደረገ ህመሙ
አልጠናበትም እንዲሁም አልቆየበትም።
የአእምሮ ህመም ማንም ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል። ውጤታማ
ህክምና አለው። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ተነጋግረን መግባባት ለምንድነው ያቃተን?==========================አንዳንዶቹ ባለመነጋገራቸው ምክኒያት አይግባቡም። አንዳንዶቹተነጋግረውም አይግባቡም። በአእምሮ አሰራር ላይ ብዙ...
05/04/2022

ተነጋግረን መግባባት ለምንድነው ያቃተን?
==========================
አንዳንዶቹ ባለመነጋገራቸው ምክኒያት አይግባቡም። አንዳንዶቹ
ተነጋግረውም አይግባቡም። በአእምሮ አሰራር ላይ ብዙ
መፅሀፍትን ያበረከተው ደራሲ ቶኒ ቡዛን Use your Head
የሚለው መፅሀፉ ላይ ምላሽ ሰጥቶበታል። እነሆ፦
ለምሳሌ ገና "ቅጠል" የሚለውን ቃል ስናወጣ አንድ አረንጓዴ
ቀለም የሚያስደስተው ሰው በአእምሮው አረንጓዴ ቅጠል
የሞላበት ጫካ ይታየዋል። አንድ በልጅነቱ ከዛፍ ላይ የወደቀ
ሰው ንዴት ሊሰማው ይችላል። አንዳንድ ሰው አእምሮው ላይ
የሚመጣበት ደግሞ የደረቀና የረገፈ ቅጠል ነው።
ንግግር እንደ ፓስታ የረዘመ ወጥ የሆነ ነገር ነው። አእምሯችን
ውስጥ ያሉት ሀሳቦች ግን እጅግ ውስብስብ ናቸው። ስንናገር
ወጥ ነገር እንናገር እንጂ አእምሯችን ውስጥ ከብዙ ቃላቶች
መካከል መርጠን፣ አድማጭ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት
ገምግመን ነው የምንናገረው። አድማጭም በበኩሉ
የሚሰማውን እንደፓስታ ምጥጥ እያደረገ ሳይሆን
የሚያስገባው። እያንዳንዷን ቃል ከአውዷና ከምትወክለው ሀሳብ
አንፃር እየገመገመ እየመረጠ ነው የሚሰማው።
አንዳንድ ጊዜ ምንም ችግር አይፈጥርም ብላችሁ የተናገራችሁት
ቃል ሌላውን ሰው ድንገት በጣም ሊያስቆጣው ይችላል።
ምክኒያቱ ያቺ ቃል በግለሰቡ አእምሮ ውስጥ የምትወክለው፣
የተዛመደችው እና የምታቃጭለው በእኛ አእምሮ ውስጥ
ከተወከለችበት፣ ከተዛማደችበት እና ከምታቃጭለው ሀሳብ
የተለየ መሆኑ ነው።
አንድ በጣም የምወዳት የሳይኮሎጂስት ዊሊያም ጀምስ ጥቅስ
አለች "ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ በእርግጥ እየተነጋገሩ ያሉት
ስድስት ሰዎች ናቸው። እያንዳንዳቸው ራሳቸውን የሚዪበት፣
እያንዳንዳቸው ሌላውን የሚያዪበት እንዲሁም የእያንዳንዳቸው
እውነተኛው ራሳቸው ደግሞ አለ።" የሁለት ሰዎች ንግግር
እንደዚህ ከሆነ ስብሰባን እንግዲህ ሳሉት
የተለያዩ መረዳቶች እንዳሉ ማወቅ አለመግባባቶቻችንን እና
ግጭቶቻችንን በተሻለ በመገንዘብ የተሻለ ለመግባባባት
ይረዳናል
ከላይ "ቅጠል" የሚለው አንድ ቀላል ቃል ምን አይነት የተለያየ
ትርጉም የተለያዩ ሰዎች ላይ እንደሚፈጥር ስላወቅን በቀጣይ
ውይይቶቻችን ላይ "ብሄር" ወይም "ህግ ማስከበር" ወይም
"አንቀፅ 39" ....ወዘተ የሚሉት ቃላት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ
ትርጉም እንዳላቸው ከመረዳት እንጀምራለን።
ፅሁፉም የተለያየ ትርጉም እንደሚሰጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ስንፈተ ወሲብ ወንዶች ላይ================ስንፈተ ወሲብ በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የብልት አለመቆም ችግርነው። አልፎ አልፎ ብዙ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን እንደህመም የሚወሰደው በተደ...
05/04/2022

ስንፈተ ወሲብ ወንዶች ላይ
================
ስንፈተ ወሲብ በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የብልት አለመቆም ችግር
ነው። አልፎ አልፎ ብዙ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን እንደ
ህመም የሚወሰደው በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነና በግለሰቡ/
በአጋሩ ላይ ጫና የሚፈጥር ሲሆን ነው። ስንፈተ ወሲብ
በተደጋጋሚ ሲከሰት በራስ መተማመንን ሊቀንስ፣ ግንኙነትን
ሊያሻክር እንዲሁም ፍርሀትና ጭንቀትን ሊፈጥር ይችላል።
በአሜሪካን ሀገር ከ12 ሚሊዮን በላይ ወንዶች ላይ እንደሚከሰት
ጥናቶች ያሳያሉ። የመከሰት እድሉም ከእድሜ ጋር እየጨመረ
ይሄዳል። ስንፈተ ወሲብ በአካላዊ ወይም የነርቭ ህመሞች
ወይም ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶች ሊመጣ ይችላል። ከ40 አመት
እድሜ በታች ሲከሰት ዋነኛው ምክኒያት ስነ ልቦናዊ ነው።
ከአካላዊ ህመሞች ጋር ተያይዞ የሚመጣ ከሆነ ህክምናው
የሚያተኩረው አካላዊ ህመሞቹን በመቆጣጠር ላይ ነው።
የስኳር መጠንን መቆጣጠር፣ የደም ግፊትን ማስተካከል፣
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ....የመሳሰሉት። በተጨማሪም እንደ
ቫያግራ ያሉ መድሀኒቶችም ከሀኪም ጋር በመመካከር ሊታዘዙ
ይችላሉ።
ምክኒያቱ ስነ ልቦናዊ ከሆነ የንግግር የስነ ልቦና ህክምና
ከችግሩ ስር ያሉትን ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶች (ጭንቀት፣ ድባቴ)
በመለየት ለማከም ያስችላል።
ስለ ህክምናው ጥያቄ ካለ ኢንቦኮስ በማድረግ መጠየቅ
ይቻላል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Ramadan Mubarak ⭐️🌙
02/04/2022

Ramadan Mubarak ⭐️🌙

ካንሰርን ያሸነፈው ጀግና መታሰቢያ ጋር========================በ19አመትህ ካንሰር እንዳለብህ ቢነገርህ ምን ይሰማሀል?በራስህ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ደርሶ ካላየህ ላይገባህይች...
27/03/2022

ካንሰርን ያሸነፈው ጀግና መታሰቢያ ጋር
========================
በ19አመትህ ካንሰር እንዳለብህ ቢነገርህ ምን ይሰማሀል?
በራስህ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ደርሶ ካላየህ ላይገባህ
ይችላል። እመነኝ እጅግ በጣም ከባድ ነው። "እግርህ ከጉልበት
በላይ ይቆረጣል።" ብትባል ምን ይሰማሀል?
ቴሪ ፎክስ በ19 አመቱ ካንሰር እንዳለበት ተነገረውና ቀኝ እግሩ
ከጉልበቱ በላይ ተቆረጠ። አርቴፊሻል እግር ተገጠመለት።
መንቀሳቀስ ጀመረ። ቀስበቀስ በደንብ ስፖርት መስራት ጀመረ።
አንተ በሁለት እግርህ ስንት ኪሎሜትር መሮጥ ትችላለህ?
መሮጡን ተወውና በአራት አመት አንዴ ኦሎምፒክ ላይ
ኢትዮጲያውያን ማራቶን ሲሮጡ ሳትሰለች ሙሉውን አይተህ
ታውቃለህ?
ቴሪ ፎክስ ገና በልጅነቱ በካንሰር ምክኒያት እግሩ ስለተቆረጠ
አዝኖ ቤት አልተቀመጠም። የካንሰር ህክምና እንዲሻሻል
ለማድረግ ገንዘብ ለማሰባሰብና ግንዛቤ ለመፍጠር በአርቴፊሻል
እግሩ በየቀኑ ማራቶን መሮጥ ጀመረ። ማራቶን በሁለት እግር
መሮጥ ከባድ ነው። በአርቴፊሻል እግር ሲሆን አርቴፊሻሉ
የሚያርፍበት ቦታ ይቆስላል። ቴሪ ግን አመመኝ፣ ቆሰለብኝ፣
ደከመኝ ሳይል ከሰኞ እስከ እሁድ ይሮጥ ነበር።
እቅዱ ካናዳን ከጠረፍ እስከጠረፍ ለመሮጥና ስምንት ሺህ
ኪሎሜትሩን ለመጨረስ ነበር። አምስት ሺ ኪ.ሜ. ከሮጠ በኋላ
አልቻለም። ትንፋሽ አጠረው፤ ድካም የማያሸንፈው ቴሪ ተንደር
ቤይ ከተማ ላይ ተሸነፈ። ሆስፒታል ሲወሰድ ካንሰሩ በደሙ
ውስጥ ተሰራጭቷል። በ22 አመቱ ህይወቱ አለፈ። ቴሪ ግን
ካንሰርን አሸንፎ ነው ያለፈው። ከ800ሚልየን ዶላር በላይ
ለካንሰር ምርምር የሚሆን ገንዘብ አሰባስቦ ለብዙዎች መዳን
ምክኒያት ሆኗል።
ወደ ተንደር ቤይ ከተማ የቴሪን መታሰቢያ ለማየት ስሄድ የአየሩ
ፀባይ በጣም በረዷማ ነበር። መንገዱ አይመችም። የጀግናውን
መታሰቢያ በነዚህ ጥቃቅን ምክኒያቶች ሳላይ ልመለስ
አልችልም።
በየዜናው በየማህበራዊ ሚዲያው መጥፎ ዜናዎች ቢበዙም
የቴሪ መታሰቢያን ስመለከት ተስፋ እንዳለ መልካም ሰዎች
እንዳሉ አሰብኩ።
ዩዴሞኒያ ቴሪ
ዶ/ር ዮናስ ላቀው።

Address

St, Amanuel Mental Specialized Hospital
Addis Ababa

Telephone

+251919352858

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdu nasir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Abdu nasir:

Share