
25/09/2023
የደም ግፊት ማለት አንድ ሰው በተደጋጋሚ የላይኛው መጠን ከ140 በላይ እና ወይም የታችኛው ከ90 በላይ ከሆነ የደም ግፊት ይባላል።
ምንም እንኳ መድኋኒት መውሰድ ግድ የሚሆንባቸው ሰዎች ቢኖሩም ለሁሉም ሰው ግን መድኃኒት መጀመር ላያስፈልግ ይችላል። ይህ ከሐኪሞ ጋር በመወያየት የሚወሰን ሲሆን ያለ መድሀኒት የደም ግፊት ለመቀነስ እንደሚረዱ በሳይንስ የተደገፉ ዘዴዎች እንዳሉ ማወቅና መተግበር ጠቃሚ ነው። በመሆኑም የሚከተሉትን ዘዴዎች ተጠቅመው የደም ግፊቶትን ይቀንሱ ስል እመክራለሁ ። ልብ ይበሉ ፦ በተለይ የኩላሊት ድክመት ፣ የልብ ድካምና ስኳር ካለቦት መድሀኒት ሊያስፈልጎት ስለሚችል እባክዎት ከሐኪሞ ጋር ይመካከሩ።
1ኛ፦ የአተነፋፈስ ዘዴ፡ በየቀኑ አየር ወደ ሳንባች በደንብ ሳብ አርገን ለ 4 ሰኮንድ ያህል በመያዝ ቀስ አርገን ወደ ውጭ መተንፈስ ። ይህን ለአስር ደቂቃ ያህል በየቀኑ መደጋገም ። ዮጋ ኒድራ/Yoga nidra ቪዲዮ ከዩቲዩብ በመመልከት አሰራሩን ማወቅ ይቻላል። ይህ መላ ሰውነታችንን ዘና/relax በማድረግ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል ።
2ኛ፦የጨው መጠንን መቀነስ ፡ በአሁን ሰዓት ብዙ ነገሮች ጨው በብዛት ይይዛሉ፦ ዳቦ ጨው አለው፤ ካች ኣፕ ብዙ ጨው አለው....ወዘተ። ይህም ሳናውቀው የጨው አወሳሰዳችንን ከፍ ያደርገዋል ። ጨው የደም ግፊትን በብዛት ከፍ ከሚያደርጉ ነገሮች ዋንኛው ነው። በመሆኑም በቀን ከሚያስፈልገን 1.5 ግራም አብዝተን ባንጠቀም ይመከራል። ምግቦችን ስናዘጋጅም ሆነ ስንመገብ የጨው መጠናቸውን መመልከት ይኖርብናል ።
3ኛ፦ የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ ምግቦችን ማዘውተር ፡ እንደ ነጭ ሽንኩርት ፣ ሙዝ፣ ቀይ ሽንኩርት ፣ ስትሮበሪ፣ ሰናፍጭ(spinach) የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መጠቀም የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል ።
4ኛ፦የአልኮል መጠጥ መተው /በጣም መቀነስ
5ኛ፦ የኣሳ ዘይትን መጠቀም፡ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፈ ነው። ከ70 በላይ የሆኑ ጥናቶች የኣሳ ዘይት የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚረዳ አሳይተዋል ።
6ኛ፦ጭንቀትን መቀነስ፦ ጭንቀት ኮርቲሶልና አድሬናሊን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በመጨመር የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋል ።በመሆኑም የጭንቀት መጠንን የሚቀንሱ እንደ ፀሎት ፣ ዮጋ፣ ሜዲቴሽን የመሳሳሉ ዘዴዎችን በመጠቀም የደም ግፊት እንዳይጨምር ማድረግ ይቻላል ። በተለይ የረጅም ጊዜ ጭንቀት ካለቦት መነሻውን ለይተው መፍታት አለቦት።
7ኛ፦ ሰፖረት መስራና ውፍረትን መቀነስ፦ የህን ማድረግ በርካታ የጤና ጥቅሞች የሉት ሲሆን የደም ግፊትን መከላከልና መቀነስ ከዋነኞቹ ነው።
8ኛ፦ በቂ እንቅልፍ መውሰድ ፦ ከ7-8 ሰዓት መደበኛ እንቅልፍ መውሰድ የደም ግፊትን ለመቀነስ ሲረዳ የእንቅልፍ እጦት በተቃራኒው የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል።