06/05/2023
የጥርስ ጤና አጠባበቅ
___________
👉ጤናማ ጥርስ እና ድድ እንዲኖረን ማድረግ ያሉብን ነገሮች
1) በቀን ሁለት ጊዜ ጥርሳችንን መቦረሽ
👉 ጠዋት ቁርስ ከበላን በኋላ እና ማታ ደሞ እራት ከተመገብን በኋላ ወይም ከመተኛታችን በፊት ማፅዳት አለብን ስንቦርሽ ጥርሳችንን ቢበዛ ከ 3 ደቂቃ መብለጥ የለበትም።
2) ጥርሳችንን በቀን አንድ ጊዜ ፍሎስ ማድረግ
👉 ክር መሳይ ገመድ (dental floss) በመጠቀም በጥርሶቻችን መካከል የሚገኙ ትናንሽ ምግቦችንም ሆነ ቆሻሻዎችን የጥርስ ብሩሻችን ሊያፀዳው ወይም ሊደርስበት ስለማይችል በፍሎሱ ማፅዳት እና ጥርሳችን በጊዜ ሂደት እንዳይቦረቦር መከላከል እንችላለን።
3) የጥርስ ብሩሻችንን ከ 3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ መቀየር ይኖርብናል ።
👉 ብሩሻችን ከላይ ከተጠቀሰው ጊዜ በላይ የምንጠቀምበት ከሆነ የመሰባበር እና በፊት የነበረውን ቅርፅ ይዞ ስለማይቀጥል ጥርሳችንን በስርዓት አያፀዳልንም በዛም ላይ ድዳችንን በመጉዳት እንዲደማ ያደርገዋል።
4) በ 6 ወር አንድ ጊዜ የጥርስ ሀኪም ጋር መታየት
👉 በእኛ ሀገር ብዙ ጊዜ ካልታመምን ወደ ሀኪም ቤት የመሄድ ልምዱ ባይኖረንም ግን በጣም አስፈላጊ እና መለመድ ያለበት ነገር ቢኖር ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።
👉አፋችን ውስጥ በቀላሉ ለእኛ ያልታዩን ወይም ቀላል ነው ብለን ያሰብናቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።
ለምሳሌ
#የጥርስ መቦርቦር ,
#መጥፎ የአፍ ጠረን ,
#የድድ መድማት እና የመሳሰሉት...
እነዚህ ነገሮች በጊዜ መፍትሄ ማግኘት እየቻሉ ሀኪም ቤት ሂደን ባለመታየታችን እና ሀኪም ባለማማከራችን ጥርሳችንን እስከማጣት እና ቀላል የነበሩትን የጥርስ ሕመሞች ወደ ከባድ ችግር ያደርሳቸዋል።
👉ስለሆነም በየስድስት ወሩ ወደ ጥርስ የህክምና ማእከላት በመሄድ ቅድመ ምርመራ በማድረግ ጤናማ ጥርስ እንዲኖረን እናድርግ።
5) የአመጋገብ ስርዓታችንን ማስተካከል
👉 # በጥርስ ላይ የሚጣበቁ እና ጣፋጭነት ያላቸውን ምግቦች መቀነስ በተለይ ህፃናትን ከእነዚህ ምግቦች ማራቅ ካልሆነም በልተው እንደጨረሱ እንዲቦርሹ ማድረግ ይጠበቅብናል።
የሚጣበቁ ወይም ጣፋጭ ምግቦች ውስጥ
#ከረሜላ ,
#የለውዝ ቅቤ ,
#ቸኮሌት ,
#ማርማራታ
#ጣፋጭ መጠጦች.... የመሳሰሉት ይገኙበታል።
👉 # በተቃራኒው ደሞ የካልሺየም ይዞታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን ስንጠቀም ጥርሳችን ጠንካራ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳናል።
ከነዚህ ምግቦች መካከል
#ጎመን ,
#የወተት ተዋፅኦ ,
#ሰላጣ እና .... የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
#ጤና ሚኒስቴር