Fews medium clinic ፈውስ መካከለኛ ክሊኒክ

Fews medium clinic ፈውስ መካከለኛ ክሊኒክ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fews medium clinic ፈውስ መካከለኛ ክሊኒክ, Medical and health, አለም ገና/ኬንቴሪ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ, Addis Ababa.

25/05/2022
06/07/2021

ጤና ይስጥልኝ ውድ የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮቻችን ለዛሬ ስለ ደም ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?
አብረን እንከታተል
ABO blood Group System

የደም ዓይነት በቀይ የደም ሴሎች ሽፋን(ገጽ) ላይ የሚገኝ በውርስ የወሰድነውን አንቲጅን(Antigen) መሠረት ያደረገ የደም ክፍፍል ነው፡፡
አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ እነሱም ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ናቸው፡፡
የደም ዓይነት ከእናትና አባት በወረስነው ዘረመል(ጂን) ይወሰናል፡፡
ሰውነታችን በአማካይ ከአራት እስከ ስድስት ሊትር ደም ይይዛል፡፡
ደም ከቀይ የደም ሴል፣ ነጭ የደም ሴል እና ፕሌትሌትስ (በፈሳሽ መሰል ፕላዝማ) የተሰራ ወይም የተገነባ ነው፡፡
የፕላዝማ(Plasma) 90% ውሃ ሲሆን በተጨማሪ ፕሮቲን፣ ሆርሞንና ውጋጅ ቆሻሻዎችን ይዟል፡፡
የደማችን 60% የሚሆነው ፕላዝማ ሲሆን 40% የሚሆነው ደግሞ የደም ሴሎች ናቸው፡፡
የደም ሴሎቻችን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ተግባር አላቸው ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ያደርሳሉ ካርበን ዳይኦክሳይድ እና ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ያስወግዳሉ፤ ደም ቀይ ቀለም እንዲኖረው አድርገውታል፡፡
ነጭ የደም ሴሎች ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት አንዱ ክፍል ሲሆን ኢንፌክሽንን በመዋጋት ይረዳናል፡፡
ፕሌትሌትስ ደም እንዲረጋ በማድረግ የደም መፍሰስን ይከላከላሉ፡፡
የደም ዓይነታችን የሚለየው/የሚታወቀው በደም ውስጥ በሚገኙ አንቲጅን(Antigen) እና አንቲበዲ(Antibody) አማካይነት ነው፡፡
አንቲበዲ(Antibody) ሰውነታችን ከውጪ ለሚገቡ ጀርሞችን ለመከላከል የሚጠቀምበት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት ክፍል ነው፡፡
አንቲጅን በቀይ የደም ሴሎች ገጽ ላይ የሚገኙ ፕሮቲኖች ናቸው አንቲበዲዎች በፕላዝማ ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ከውጭ ወደሰውነታችን የገቡ ማንኛውንም ነገሮች በመለየት እንዲወገዱ ለበሽታ የመከላከል ስርዓት ጥቆማ ያደርጋል፡፡
የኤ.ቢ.ኦ የደም ሥርዓት ክፍፍል ምን ይመስላል?
አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ፡፡
• ኤ(A)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ቢ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
• ቢ(B)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ቢ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ኤ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
• ኤቢ(AB)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ እና ቢ አንቲጅን ይገኛሉ (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ምንም ዓይነት አንቲበዲ አይገኝም)
• ኦ(O)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ምንም ዓይነት አንቲጅን አይገኝም (በፕላዝማ ውስጥ ሁለቱም ኤ እና ቢ አንቲበዲ ይገኛሉ)፡፡
የትኛው የደም ዓይነት ለየትኛው የደም ዓይነት መስጠት ይችላል?
✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ለማንኛውም ሰው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ያለው ሰው ቢ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤቢ የደም ዓይነት ላለው ሰው ብቻ ደም መለገስ ይችላል፡፡
ከየትኛው የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ?
✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኤ(A) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ቢ(B) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ከማንኛውም የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ፡፡
ከኤ(A) እና ቢ(B) አንቲጅን በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ አንቲጅን አለ እሱም አር.ኤች ፋክተር(Rh factor) ይባላል፡፡

በደም ውስጥ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል በደም ውስጥ ሲገኝ ፖዘቲቭ

20/06/2021

ፈውስ መካከለኛ ክሊኒክ ስራ ጀመረ!!

ቦታ:-አለም ገና/ ኬንቴሪ ሪፍት ቫሊ
ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ዳሊቲ መውጫ

የሚሰጡ አገልግሎቶች:-

*የአዋቂና የህፃናት ጠቅላላ ምርመራ ና ህክምና

*መለስተኛ ቀዶ ጥገና ግርዛትን ጨምሮ

*የደም ግፊት፣የስኳር፣የአስም ምርመራ ና ክትትል

*የአባለዘር በሽታ ፣የውሃ ሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ፣ የቲቢ፣የፈንገስ፣የወባ በሽታ ፣የአንጀት ቁስለትና የጨጓራ ባክቴሪያ ምርመራ ና ህክምና

*የጉበት፣የኩላሊት፣የልብ፣የሳንባ ጤንነት ምርመራ

*የአይን፣የጆሮ፣የአፍ በሽታዎች ምርመራ

*የእርግዝና ልየታና ምክር፣የማዋለድ አገልግሎት

*የስነ-ተዋልዶ አገልግሎት

*የአልትራ ሳውንድ፣የራጅ፣የሲቲ ስካን፣የኤም አር አይና ሌሎችንም ምርመራ እንደአስፈላጊነቱ በማዘዝ ህክምናና የሪፈር አግልግሎት እንሰጣለን።

"አላማችን የእርሶ ጤና መሆን ነዉ

Address

አለም ገና/ኬንቴሪ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fews medium clinic ፈውስ መካከለኛ ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram