18/03/2026
"የልጅዎ የወደፊት ጤና መሰረት"
✅ የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት"
የአንድ ህፃን የጤና እና የአእምሮ እድገት 80% የሚወሰነው በመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት ውስጥ እንደሆነ ያውቃሉ?
⏱ይህ ጊዜ ከእርግዝና ጀምሮ ህፃኑ 2 አመት እስኪሞላው ያለውን ጊዜ ያካትታል።
1️⃣ 🤱 ለእርጉዝ እናቶች (ከፅንስ ጀምሮ)
የቅድመ ወሊድ ክትትል፦ ቢያንስ 8 ጊዜ የህክምና ክትትል በማድረግ የፅንሱን ጤንነት ያረጋግጡ።
የተመጣጠነ ምግብ፦ አይረን (Iron) እና በፎሊክ አሲድ (Folic Acid) የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለፅንሱ አእምሮ እድገት ወሳኝ ነው።
እረፍት እና የአእምሮ ሰላም፦ የእናትየው ደህንነት የልጁ ደህንነት ነው።
2️⃣ 👶 ለጨቅላ ህፃናት (ከ0 - 6 ወር)
የእናት ወተት ብቻ፦ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ውስጥ ከጡት ውጪ ምንም አይነት ውሃም ሆነ ተጨማሪ ምግብ አያስፈልግም። የእናት ወተት ሁሉንም አልሚ ምግቦችና በሽታ የመከላከል አቅምን ይይዛል።
የቆዳ ለቆዳ ንክኪ፦ ከህፃኑ ጋር የሚደረግ የቆዳ ለቆዳ ንክኪ ፍቅርን ከመጨመር ባለፈ የህፃኑን የሙቀት መጠን ያስተካክላል።
3️⃣🍲 ከ6 ወር እስከ 2 አመት
ተጨማሪ ምግቦች፦ ከ6 ወር በኋላ ከጡት ወተት ጎን ለጎን ለስላሳ እና የተፈጩ የተመጣጠኑ ምግቦችን (አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እህል) ይጀምሩ።
ክትባቶችን ማጠናቀቅ፦ ልጅዎን ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ ወቅታዊ ክትባቶችን በሰዓቱ ይስጡ።
⚠️"ዛሬ የምናደርገው ጥንቃቄ፣ የነገውን ጤናማ ትውልድ ይፈጥራል!"
📍 አድራሻችን፦ [22 ብርሃን ዛሬ ት/ቤት ፊት ለፊት]
📞 ለበለጠ መረጃ፦ [09 11 666770]
📱 ቴሌግራም፦
[https://t.me/semah22mchcenter]
📱 Google map
https://maps.app.goo.gl/jJ9XXBpLq2LTK5FU9