Dr. Seid Arage

Dr. Seid Arage Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Seid Arage, Medical and health, Ethiopia, Addis Ababa.

Maternal Fetal Medicine sub specialist
( በእናቶችና ጽንስ ህክምና አደጋ ላይ ወይም ውስብስብ ችግሮች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ህክምና )
ረዳት ፕሮፌሰር
አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በረካ የእናቶችና ህጻናት ማእከል
+ 251910161920

Today I received the attached recognition on behalf of the department Head of Obstetrics and Gynecology ,CHS, Addis Abab...
07/08/2025

Today I received the attached recognition on behalf of the department Head of Obstetrics and Gynecology ,CHS, Addis Ababa University ,
From Bole sub city.
This is a recognition received for the Cervical cancer screening and counseling done for three days by our Residents and other CHS volunteers.
We would like to thank all who are involved in the task.
ዘወትር ስንሰራ በነበረው ስራችን ስላመሰገናችሁን
ለቦሌ ክፍለ ከተማም የላቀ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
subcity information technology team
Ababa university
of health sciences Addis ababa University

05/07/2025

941 likes, 37 comments. “postmenopausal bleeding needs urgent evaluation”

17/04/2025

የስራ ሰአትና ቦታ ለጠየቃችሁኝ።

https://www.facebook.com/share/p/16UuQj6iT8/
15/04/2025

https://www.facebook.com/share/p/16UuQj6iT8/

የደም ማነስ ለገጠመው ፅንስ ደም መስጠት …

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የእናቶችና ፅንስ ህክምና ክፍል የደም ማነስ ያጋጠመው የአራት ወር ፅንስ ደም እንዲሰጠው በማድረግ የጽንሱን ህይወቱ ማትረፍ መቻሉን በሆስፒታሉ የእናቶችና ጽንስ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ሰዒድ አራጌ ገልጸዋል።

ህፃናት በማህፀን እያሉ እንደማንኛውም ሰው የደም ማነስን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎች ሊያጋጥማቸው እንደሚችልም ተናግረዋል።
የጤና እክል ገጥሟት ወደ ሆስፒታሉ የመጣች አንዲት ነፍሰ-ጡር እናት በተደረገላት ምርመራ ሽሉ የደም ማነስ ችግር እንደገጠመው የተደረሰበት በመሆኑ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።

እናትየው ወደ ሆስፒታሉ ስትመጣ የዘገየች ቢሆንም በተደረገላት ክትትል የጽንሱን ህይወት በመታደግ ውጤታማና አስደሳች ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል።

ሾተላይ ወይም አር ኤች ፋክተር በመባል የሚታወቀው ህመም መኖሩ ከታወቀ ህፃናት በማህፀን ሳሉ በሚደረግላቸው የህክምና ክትትል በተሳካ ሁኔታ ማዳን እንደሚቻል መታየቱን አብራርተዋል።

በመሆኑም የህክምና ባለሙያዎች እንዲህ አይነት ችግር ያለበት ፅንስ ካጋጠማቸው ለተጨማሪ ህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መላክ የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩን አስገንዝበዋል።

ይህንን የህክምና ሂደት በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ማስተማር እንደሚያስፈልግ የገለጹት ዶ/ር ሰዒድ፤ እናቶች ከመጀመሪያ ፅንስ ሁለተኛውና ሶስተኛው ከባድ ሊሆን እንደሚችል ተረድተው በአፋጣኝ ክትትል በማድረግ ወደተቋሙ እንዲመጡ አመላክተዋል።

ዶ/ር ሳምሶን ከሃሊ በበኩላቸው፤ በዘመናዊ አልትራሳውንድ በመታገዝ ህክምናው መስጠት መጀመሩን ጠቅሰው፤ በማህፀን እያሉ የደም ማነስ ችግር የሚገጥማቸውን ህፃናት ህይወት መታደግ ተችሏል ብለዋል።

እናቶች በእርግዝና ክትትል ወቅት የደም አይነታቸውን በመለየት መድሀኒት በ28ኛው ሳምንት በመውሰድ የችግሩን የመከሰት ዕድል ከ16 በመቶ ወደ 0 ነጥብ 3 በመቶ ገደማ መቀነስ እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ፅንስ የሾተላይ ችግር ያለበት መሆኑ ከተረጋገጠ በማህፀን ውስጥ እያለ ለራሱ በተዘጋጀ መርፌ አማካኝነት ደም የመስጠት ስራ እንደሚከናወንም አብራርተዋል።

በእየሩስ ወርቁ

09/04/2025
05/03/2025

ነብሰ ጡር እናት ወይም አጥቢ እናት መጾም ትችላለች?
እንደሚታወቀው አንዲት እናት በእርግዝናዋ ጊዜ ወይም ጡት በምታጠባበት ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻሉ እና በዛ ያሉ ምግቦችን መመገብ እና ፈሳሾችን ማብዛት ይጠበቅባታል። ከሌላው የእድሜ ክፍል በተለየ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ የሰፈልጋታል ። ነፍሰ ጡር እናት ከሆነች ደሞ በተለየ ሁኔታ የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ላይ በተደጋጋሚ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ስለሚያጋጥሟት በአንጻሩ ደግሞ በመጨረሻዎቹ ወራት ቶሎ የመጥገብ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ስለሚከሰትባት በ24 ሰአት ዉስጥ ከ 5 ጊዜያት በላይ መመገብ ሊያስፈልጋት ይችላል።
ይህም በመሆኑ አንዲት ነብሰ ጡር ወይም አጥቢ እናት ለመጾም ከመነሳቷ በፊት ቀጥሎ ያሉትን ህክምናዊ ጉዳዮችን ማወቅና አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባት ለማስታወስ እንወዳለን ፦
በመጀመሪያዎቹ 3 ወራት የእርግዝና ጊዜ የሚገጥሙ ማስመለስ እና ማቅለሽለሽ ካለ በጾም እንደሚባባስ ማወቅ ያስፈልጋል
አንዲት ነብሰ ጡር ወይም አጥቢ እናት የስኳር በሽታ ካለባት ለእርሱም መድሃኒት የምትወስድ ከሆነ ጾም ላይ መጠንቀቅ ይገባታል
የደም ማነስ ፣ ተቅማጥ ፣ ደም ግፊት አንዲሁም ሌሎች ከእርግዝና ጋር ወይም ከ ማጥባት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተጨማሪ ህመሞች አለመኖራቸውን ማወቅ ይኖርባታል
በጾም ምታሳልፈው የቀኑ እርዝመት ከ 12 ሰአት እንዳይበልጥ ይመከራል
የአካባቢው የአየር ሁኔታ በጣም ሞቃታማ ከሆነ አለመጾሙ ይመከራል
ሱሁር መመገብ ፣ ጨው የበዛበትን መግብ መቀነስ ፣ በአንጻሩ ደሞ በተለይ ስሁር ላይ ፕሮቲን ፣ ፋይበር ነክ የሆኑ ጥሩ ምግቦችን መመገብና ፈሳሽ ነገሮችን በብዛት መውሰድ ይመከራል
ለመጾም ሲወስኑ ሃኪሞን ሳያማክሩ በአርግዝና ወቅት የሚሰጡ መድሀኒቶችን ማቁአረጥ እንደማይገባ ማወቅ ግድ ይላል
መንታ ወይም ከዚያም በላይ ጽንስ ካለ ከአምስት ወር በኀላ አለመጾሙ ይመከራል
አሁን ላይ የምጥ ሰሜቱ ካለም መጾም አይመከርም

ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድም ጥንቃቄዎችን ያረገች እናት ረመዳኑአን በየትኛውም የእርግዝና እድሜ ላይ ብትጾም ፅንሱ ላይ ችግር እንደሌለው በርካታ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ከዘጠኝ ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ወር መፆም ጉዳት እንደሚያስከትል የሚአትት የጥናት ውጤት እንደሌለም ይታወቃል ። ሆኖም ግን እርግዝና ላይ ያለች እናት ከሚያስፈልጋት ጉልበት አኳያ ፆሙን ጀምራ ካልቻለች ወይም የድካም ስሜት ከተሰማት ቀጥሎም ራስ ምታት ከተሰማት በጾሙ መቀጠል አይገባትም። የመፆም ፍላጎቷ ካየለ ግን አንድ ቀን እየፆመችና አንድ ቀን እያፈጠረች አቅሟን እንድታይ ትመከራለች።
ፆመኛ የሆነች ነብሰ ጡር ወይም አጥቢ እናት እንዳትወስዳቸው የምትመከራቸው የምግብ አይነቶች
ጨው የበዛበት ምግብ ፣ ቅባትና ጮማ፣ ስኳር የበዛበት ምግብ
እንደማንኛውም ጊዜ ከሱስ ሁሉ መጠንቀቅ
ፆመኛ የሆነች ነብሰ ጡር ወይም አጥቢ እናት ( በተለይ ስሑር ላይ ) እንድተወስድ ምትመከራቸው የምግብ አይነቶች
በፕሮቲን የበለጸጉ የምግብ አይነቶችን ( ለምሳሌ ለውዝ ፣ ምስር፣ አተር ወይም የባቄላ ፉል
በፋይበር የበለጸጉ የምግብ አይነቶችን ( ለምሳሌ ተምር )
ፍራፍሬዎችን ( ለምሳሌ የማንጎ ፣ የአቮካዶ ፣ የፓፓዬ ፣ ወዘተ ጭማቂዎችን
ሆልግረይን ምግቦችን( ለምሳሌ የቂንጬ ሾርባ ፣ ውሃ በወተት )
በፆመ ላይ የሆነች ነብሰ ጡር ወይም አጥቢ እናት የሚከተሉትን ምልክቶች ካየች ሀኪሟን እንድታማክር ትጠየቃለች
የምጥ ምልክት
ረዘም ላለ ሰአት የልጅ እንቅስቃሴ መቀነስ
ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት ማጋጠም
ከፍተኛ የሆነ ድካም ፣ የውሃ ጥም ፣ ረሃብና ማዞር መከሰት
በጥቅሉ በጾሙ ምክንያት የሚመጣ ምልክቶችን መገምገም
በዶ/ር ሰይድ አራጌ
( የማህጸንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ፣ ማተርናል ፌታል ሜድስን ሰብ ስፔሻሊስት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል MFM unit እና በረካ የእናቶችና ህጻናት ህክምና ማዕከል )

አዲስ አበባ

08/01/2025

በረካ የህክምና አገልግሎት

ከዚህ በታች ለተመለከተው ክፍት የሥራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ ሠራተኛ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
1. የሥራ መደቡ መጠሪያ፦
Nurse
※ የትምህርት ደረጃ፦ ቢ.ኤስ.ሲ. ዲግሪ
※ የሥራ ልምድ፦ ከ0 አመት ጀምሮ
※ ብዛት፦ 4
※ ፆታ፦ አይለይም

※ ደመወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሠረት

ማሳሰቢያ፡ አመልካቾች የትምህርት፣ የሙያ ፈቃድና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን ዋናውንና ኮፒውን ከማመልከቻ ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ5 (አምስት) የሥራ ቀናት የህክምና ተቋሙን
ሰው ሀብት አስተዳደር በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር በቴሌግራም የተሟላ ማስረጃ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

አድራሻ፡- ከ ቤተል ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ጥቁር አባይ
መስቀለኛው ጋር
ሞባይል፡ 0910161920

Huge congratulations for all involved!!!Our own  managed  cases got published .this is a case series with an atypical pr...
07/01/2025

Huge congratulations for all involved!!!
Our own managed cases got published .
this is a case series with an atypical presentation of hypokalemia(neurologic manifestation). hypokalemia is a common finding following Hyper emesis gravidarum after days or weeks of severe vomiting .
I hope it will be important for health care professionals involving in the the management of Hypokalemia particularly hyperemesis gravidarum.
anyone who had ever encounter this kind of presentation?

Severe Life-Threatening Hypokalemia Primarily Presented With Isolated Paralysis: Case Series From Ethiopia
Getasew Kassaw Alemu, Seid Arage Asfaw, Lisanne Seifu Asres, Beniam Yohannes Kassa
First published: 06 January 2025
https://doi.org/10.1002/ccr3.70062
https://lnkd.in/dCuSp2Wm

Severe hypokalemia can primarily present as a weakness of the limbs, without any other clinical manifestation. A life-threatening level of decreased serum potassium level can be unusually present wit...

https://youtu.be/rlutWv4CEVM
01/11/2024

https://youtu.be/rlutWv4CEVM

አዲስ ሕይወት ሰፋ ያሉ የጤና ጉዳዮችን የሚዳስስ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሲሆን በሕክምና ሁኔታ ላይ ትኩረቱን አድረጎ . የህክምና እና የታካሚዎች ስጋት እንዲሁም ሌሎች የጤና ጉዳዮችን ከሰ.....

Address

Ethiopia
Addis Ababa
7080

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Seid Arage posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram