Ethio Internal Medicine Speciality Clinic : ኢትዮ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ክሊኒክ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethio Internal Medicine Speciality Clinic : ኢትዮ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ክሊኒክ

Ethio Internal Medicine Speciality Clinic : ኢትዮ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ክሊኒክ Ethio Internal Medicine Speciality Clinic is giving health care service 24/7. Also have Laboratory and Ultrasound Services.

Specialists: Nephrologist, Internist, Gynecologist, Psychiatrist, Dermatologist, General Surgeon, Neurosurgeon and Pediatrician.

Giving free first aid service near the 'ሰሚት ታቦት ማደርያ'መልካም በዓል!!ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 0993928748 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉ  ...
18/01/2026

Giving free first aid service near the 'ሰሚት ታቦት ማደርያ'
መልካም በዓል!!

ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 0993928748 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉ

15/01/2026

የሪህ ህክምና በእግር ስፔሻሊስት ሀኪም

📍ከሰሚት ታቦት ማደርያ ፊት ለ ፊት ከሚገኙት የ ጋራ መኖርያ ቤቶች ጀርባ

ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 0993928748 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉ

#ሪህ

20/12/2025

ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ የሚያስከተሉ ነገሮች

08/12/2025

ጤናማ ያለሆነ የማህፀን ፈሳሽ

08/12/2025

በግንኙነት ወቀት የወንድ ብልት በደንብ አለመቆም

🩺 የጉበት ቫይረስ ምንድን ነው?ሄፓታይተስ ብዙውን ጊዜ በቫይረስ ኢንፌክሽን (ሄፓታይተስ ኤ, ቢ, ሲ, ዲ እና ኢ) የሚከሰት የጉበት ችግር ሲሆን ፣ ሥር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ወደ ጉ...
03/12/2025

🩺 የጉበት ቫይረስ ምንድን ነው?

ሄፓታይተስ ብዙውን ጊዜ በቫይረስ ኢንፌክሽን (ሄፓታይተስ ኤ, ቢ, ሲ, ዲ እና ኢ) የሚከሰት የጉበት ችግር ሲሆን ፣ ሥር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ወደ ጉበት ጉዳት ፣ ካንሰር አልፎ ተርፎም ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ—ነገር ግን መከላከል እና መታከም የሚችሉ ናቸው!

🚨 ለምን ስለጉበት ቫይረስ ማወቅ ያስፈልጋል?

✅ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ። አብዛኞቹ ሰዎች ደሞ እንዳለባቸው አያውቁም።
✅ በጉበት ቫይረስ በሽታ በየአመቱ 1.1 ሚሊዮን ሰዎች ለህልፈተ ህይወት ይደረጋሉ። ነገር ግን
✅ በምርመራ፣ በክትባት እና በህክምና ሄፓታይተስን መከላከል እና ማከም ይቻላል።

✅ ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል ? :

🔹 መመርመር - በተለይ የተወለዱት ከ1945-1965 ዓ.ም ከሆነ ወይም የደም ንክኪ ከነበረ።
🔹 መከተብ - ደህንነቱ የተጠበቀ ክትባቶች ለሄፐታይተስ ኤ እና ቢ ማግኘት።
🔹 መንስኤዎቹን ማወቅ - ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ የጋራ መርፌዎች ወይም ንጽህናውን ያልጠበቀ ንቅሳት መንስኤዎቹ ናቸው።
🔹 ህክምና ማግኘት - ሄፓታይተስ ሲ አሁን በዘመናዊ ህክምና ይድናል!

💛 ወደ ክሊኒካችን በመምጣት ተገቢውን የሄፒታይተስ ህክምና እና ምርመራ ያግኙ።

📞ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ0993928749 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉልን !

📍አድራሻችን ፡ ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ፊት ለፊት ፣ ዋሺንግተን ሰፈር መግቢያ ጋር ያገኙናል

28/11/2025

መካንነት የምንለው መቼ ነው ?
ይህ ችግር ካለብዎት በስፔሻሊቲ ክሊኒካችን በመምጣት አስፈላጊውን ህክምና እና ምርመራ ማግኘት ይችላሉ።

📞ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ0993928749 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉልን !

📍አድራሻችን ፡ ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ፊት ለፊት ፣ ዋሺንግተን ሰፈር መግቢያ ጋር ያገኙናል

🦶💥ሪሂ (Gouty Arthritis) ምንድን ነው?💥🦶ሪሂ የመገጣጠምያ ህመም ሲሆን በደም ውስጥ ከመጠን በላይ የዩሪክ አሲድ መከማቸት ምክንያት ይመጣል። ዩሪክ አሲድ ሲከማች መስታወት የሚመስሉ...
28/11/2025

🦶💥ሪሂ (Gouty Arthritis) ምንድን ነው?💥🦶

ሪሂ የመገጣጠምያ ህመም ሲሆን በደም ውስጥ ከመጠን በላይ የዩሪክ አሲድ መከማቸት ምክንያት ይመጣል። ዩሪክ አሲድ ሲከማች መስታወት የሚመስሉ የሚወጉ ድንጋዮችን በመገጣጠሚያ ይፈጠራል። ሪህ በብዛት የእግር አውራጣትን ይጎዳል።

🔹 የሪህ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

✅ድንገተኛ ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም ( በብዛት ማታ ማታ )
✅የመገጣጠሚያ እብጠት, መቅላት እና ማተኮስ
✅በህመም ምክንያት የእንቅስቃሴ መገታት እና
✅በአንድ መገጣጠሚያ (በብዛት የእግር አውራጣት፣ ጉልበት ወይም ቁርጭምጭሚት) የሚጀምር ህመም ሊያሳይ ይችላል።

🔹ሪህ በምን ሊቀሰቀስ ይችላል?

🍖 ቀይ ስጋ ወይም የባህር ምግቦች
🍺 አልኮል በተለይ ቢራ
🥤 ስኳራማ መጠጦች እና
💊 በጣም የሚያሸኑ መድኃኒቶችን መጠቀም ሪህን ሊቀሰቅሰው ይችላል

🔹 ሪህን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

✅የታዘዘውን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ
✅ውሃ በደንብ መጠጣት
✅የሚቀሰቅሱ ምግቦችን አለመውሰድ
✅አልኮል እና ስኳራማ መጠጦችን አለመውሰድ እና
✅ክብደትን መቆጣጠር ሪህን ለመቆጣጠር ይረዳል።

📌 የተጠቀሱትን ምልክቶች ካዩ ወደ ክሊኒካችን በመምጣት ተገቢውን ምርመራ እና ህክምና በስመጥር ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ያግኙ።

👣 እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ቶሎ ወደ ክሊኒካችን በመምጣት በውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ይታዩ።

📞ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ0993928749 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉልን !

📍አድራሻችን ፡ ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ፊት ለፊት ፣ ዋሺንግተን ሰፈር መግቢያ ጋር ያገኙናል

World AMR Awareness week : November 18-24 የጸረ ትህዋሲያን መድሃኒት መላመድ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ይህ ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለባክቴሪያ፣ ለቫይረስ ፣ ...
20/11/2025

World AMR Awareness week : November 18-24
የጸረ ትህዋሲያን መድሃኒት መላመድ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት

ይህ ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለባክቴሪያ፣ ለቫይረስ ፣ ፈንገስ እና ፓራሳይት በምንሰጣቸው መድሃኒቶች ላይ ያሉ ለውጦች እና መድሃኒት የመላመድ ሂደቶች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የዘንድሮው መሪ ቃል "ዛሬውኑ እርምጃ በመውሰድ ዛሬያችንን እና ነጋችንን እንጠብቅ" የሚል ሲሆን ክሊኒካችን ኢትዮ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክም ህብረተሰባችን በሃኪም ያልታዘዙ መድሃኒቶችን ያለ አግባብ በመውሰድ ከሚመጣበት ከፍተኛ ጉዳት እራሱን እንዲጠብቅ መለዕክት ለማስተላለፍ ይወዳል።

ለማንኛውም የጤና እክል ወደ ክሊኒካችን ሲመጡ ተገቢውን ህክምና እና እንክብካቤ በስመጥር ሃኪሞቻችን ያገኛሉ።

📞ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ0993928749 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉልን !

📍አድራሻችን ፡ ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ፊት ለፊት ፣ ዋሺንግተን ሰፈር መግቢያ ጋር ያገኙናል

የሰሞኑ ወረርሽኝ !የ ማርበርግ በሽታ (hemorrhagic fever) በቫይረስ የሚመጣ በከፍተኛ ሁኔታ ለህይወት አስጊ የሆን በሽታ ሲሆን ከታች የተዘርዘሩት ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወድ ጤና ...
17/11/2025

የሰሞኑ ወረርሽኝ !

የ ማርበርግ በሽታ (hemorrhagic fever) በቫይረስ የሚመጣ በከፍተኛ ሁኔታ ለህይወት አስጊ የሆን በሽታ ሲሆን ከታች የተዘርዘሩት ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወድ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

እንደ አለምጤና ድርጅት እና ኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር የሄሞራጂክ ትኩሳት በሽታ መስፈርት
- እስከ 3 ሳምንት የቆየ ትኩሳት እና
- በፅኑ የታመመ ሰው እና
- ከሚከተሉት ሁለቱ የሚታዩበት
1. ደም የቋጠረ የሚያሳክክ ሽፍታ
2. ነስር (ከአፍንጫ ደም መፍሰስ)
3. ደም የቀላቀለ ትውከት
4. ደም የቀላቀለ አክታ
5. ደም የቀላቀለ ሰገራ

💙የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች በማድረግ እራስዎን ይጠብቁ ። ለማንኛውም የጤና እክል ወደ ክሊኒካችን ሲመጡ ተገቢውን ህክምና እና እንክብካቤ በስመጥር ስፔሻሊስት ሃኪሞቻችን ያገኛሉ።

📞ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በ0993928749 ወይም 0115526928 ላይ ይደውሉልን !

📍አድራሻችን ፡ ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ፊት ለፊት ፣ ዋሺንግተን ሰፈር መግቢያ ጋር ያገኙናል ።

13/11/2025

የህመም ማስታገሻዎች ኩላሊት ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ
ዶ/ር ተስፋዬ ይልማ (የኪላሊት ህክምና ስፔሻሊስት )

07/11/2025

Address

2V32+67H
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Internal Medicine Speciality Clinic : ኢትዮ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share