10/04/2026
እንኳን ለስቅለተ ዓርብ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!
የዎባ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነዋይ ማትዮስ ለጌታችና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሳኤ በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ሚያዝያ 2/2018 ዓ.ም (ከዎአወጤጽ/ቤት)
ከዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አቶ ነዋይ ማትዮስ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለተ ዓርብ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል
በሀገራችን ብሎም በመላው ዓለም የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ አክብሮት የሚታሰበው የስቅለት በዓል፤ የፍቅር፣ የትህትና እና የራስን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት ታላቅ ተምሳሌት ነው።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በፈቃዱ የተቀበለው መከራና የከፈለው መስዋዕትነት ለሁላችንም ይቅርታን፣ ሰላምንና መተሳሰብን የሚያስተምር ነው።
የጌታ ስቅለት የፍቅር ሁሉ ጥግ እና ለሌሎች የመኖር ጥበብ የታየበት ዕለት ነው። ይህ የሕመም፣ የጸሎትና የይቅርታ ዕለት ለሀገራችን እና ለዓለም ሰላምን፣ ለልባችን ቅንነትን የሚያድል ይሁን።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የበዓል ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መልካም በዓል!
ዳንኤል ገበየሁ ከዎባ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት