
27/02/2020
ለመስጠት መሰጠት ያስፈልጋል
*
በአመት 10.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኘው የሊቨርፑሉ የፊት አጥቂ ሰይዶ ማኔ የተሰነጣጠቀና የተጫጫረ አይፎን ይዞ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፤ ስለሁኔታው የተጠየቀው ማኔ የሰጠው መልስ ግን አስደናቂ ነበር
*
"10 ፌራሪ፣ 20 የዳይመንድ ሠአት እና 2 ጄት ፕሌንስ ምን ይሠሩልኛል? ለአለምስ ትርፋቸው ምንድነው? ተርቤ አቃለሁ፣ በባዶ እግሬም እጫወትም ነበር፣ ወደ ት/ቤትም አልገባሁም፡፡ አሁን ግን ሰዎችን መርዳት ችያለሁ፤ የኔ ምርጫ ት/ቤቶችን መገንባት እና የተቸገሩትን ማልበስና መመገብ ነው፡፡ ቅንጡ ቤት፣ መኪና እና ፕሌን አያስደስቱኝም፤ ለህዝቤ ህይወት ከሠጠቺኝ ማካፈሉ ነው የኔ ደስታ፡፡