16/03/2026
የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) መድኃኒቶች!
የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማከም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የ PDE5 inhibitors በመባል የሚታወቁ መድኃኒቶች ናቸው።
እነዚህ መድኃኒቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
Sildenafil (Vi**ra)
Tadalafil (Cialis)
Vardenafil (Levitra)
Avanafil (Stendra)
እንዴት ነው የሚሰሩት?
እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት በብልት ውስጥ ያሉ የደም ስሮች እንዲከፈቱ እና የደም ዝውውር እንዲጨምር በማድረግ ነው።
ይህ የሚሆነው PDE5 የሚባለውን ኢንዛይም (enzyme) በመከላከል ነው። የ PDE5 ኢንዛይም የብልት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል። ስለዚህ እነዚህ መድሃኒቶች የ PDE5 ኢንዛይምን ሲገቱት የብልት ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ ደም በቀላሉ ወደ ብልቱ እንዲፈስ ያደርጋሉ፣ ይህም ለግንኙነት የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ብልት እንዲቆም ይረዳል።
ማን መውሰድ የለበትም?
እነዚህን መድሃኒቶች ከመውሰድዎ በፊት የጤና ሁኔታዎን ለሀኪምዎ መንገር በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይም የሚከተሉት የጤና ህመሞች ካሉዎት እነዚህን መድሃኒቶች መውሰድ የለብዎትም:
የልብ ህመም ካለብዎት: ለልብ ህመም ናይትሬት (nitrate) የያዙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ። እነዚህን መድሃኒቶች ከናይትሬት ጋር አብሮ መውሰድ ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከባድ የደም ግፊት መቀነስ ሊያስከትል ይችላል።
የደም ግፊት ችግር ካለብዎት: ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎ።
የጉበት ወይም የኩላሊት በሽታ ካለብዎት: የመድሃኒቱ ተጽእኖ በሰውነትዎ ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ሊራዘም ስለሚችል የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያባብስ ይችላል።
ከሀኪም ወይም ከሳይኮሎጂስት ጋር መነጋገር: የስንፈተ ወሲብ መንስኤ የአእምሮ ጭንቀት ወይም ስነልቦናዊ ከሆነ ከሙያተኛ ጋር መነጋገር ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
እነዚህ ምክሮች ከመድኃኒቱ ጋር ተዳምረው የበለጠ ውጤታማነት እንዲያገኙ ይረዳዎታል።
አዲሱን የYoutube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_