Dr Robel ዶ/ር ሮቤል

Dr Robel ዶ/ር ሮቤል ዶ/ር ሮቤል አሳምነው፤
የህፃናት አና ታዳጊ ልጆች እስፔሻሊስት ሀኪምና በወሎ ዩኒቨርሲቲ ህፃናት ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር

19/03/2026

#የጨቅላ ሕፃናት መታፈን ምንድነው?
#አንዴትስ ይታከማል?
#መከላከል ይቻላልዎይ?
የጨቅላ ሕፃናት መታፈን (Perinatal Asphyxia) ማለት አንድ ሕፃን ከመወለዱ በፊት፣ በመውለድ ሂደት ላይ ወይም ከተወለደ በኋላ ባሉት ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በቂ የሆነ ኦክስጅን ባለማግኘቱ ምክንያት የሚከሰት የጤና እክል ነው. ይህ ሁኔታ በሕፃኑ አካል ውስጥ ያለውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን እንዲጨምርና የደም አሲድነትን (acidosis) እንዲጨምር ያደርጋል.

#መንስኤዎች
የእንብርት ገመድ መተብተብ ወይም መታጠፍ.
የምጥ ጊዜ መርዘም ወይም መቸገር.
የእንግዴ ልጅ (Placenta) ያለጊዜው መላቀቅ.
ሕፃኑ ገና ሳይወለድ በሆድ ውስጥ ሳለ የቆሸሸ ፈሳሽ (meconium) መዋጥ.
በጥቅሉ በቂ ያልሆነ አና ጊዜዉን ያልጠበቀ የጤና ባለሙያ ክትትል አና ዉሳኔ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል
#ምልክቶች
- ሕፃኑ ሲወለድ ወዲያውኑ አለማልቀስ ወይም የመተንፈስ ችግር.
- የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊነት ወይም ወደ ነጭነት መቀየር.
- የጡንቻዎች መላላት (floppy muscle tone).
- የልብ ምት ዝቅተኛ መሆን.
- ንቃት መቀነስ
#ሕክምና
ሕፃኑ ከተወለደ በኋላ መታፈን ካጋጠመው ፈጣን የሆነ የሕክምና እርዳታ ያስፈልገዋል፦ ይህም መሰረታዊ አርዳታ በ አንድ ደቂቃ ዉስጥ መሰጠት ይኖርበታል::

* የመተንፈሻ ቱቦን ማጽዳት፦ ሕፃኑ የዋጠውን ፈሳሽ
በማስወገድ አየር እንዲገባ ማድረግ.
* ኦክስጅን መስጠት፦ በጭንብል (mask) ወይም
በመተንፈሻ መሣሪያ አማካኝነት ኦክስጅን እንዲያገኝ
ማድረግ.
* የሰውነት ሙቀትን ማስተካከል፦ ሕፃኑን በማሞቅ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ የሰውነት ሙቀትን በመቀነስ (Therapeutic Hypothermia) የአንጎል ጉዳትን መቀነስ.
* መድኃኒቶች፦ የደም ዉስጥ ንጥረነገሮችን, የደም ግፊትንና የልብ ምትን ለማስተካከል የሚረዱ መድኃኒቶችን መስጠት.

#መከላከል
አብዛኛውን ጊዜ መታፈንን ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል፦ ችግሩ ደርሶ ከማከም ይልቅ ቀድሞ መከላከል የማይተካ ሚና አለው::
• የእርግዝና ክትትል፦ አንዲት እናት በእርግዝናዋ ወቅት የጤና ክትትል በማድረግ የሕፃኑን የጤና ሁኔታ ማወቅ.
በጤና ተቋም መውለድ፦ በባለሙያ ታግዞ መውለድ ችግሮች ሲፈጠሩ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል.
• የተመጣጠነ ምግብ፦ እናቶች በእርግዝና ወቅት ጤናማ አመጋገብ መከተል ይኖርባቸዋል.
የመታፈን ደረጃው ከፍ ካለ, ወይም ቶሎ አና ፕሮፌሽናል አርዳታ ካላገኘ,÷
_ ራሱን መቻል መቸገር : ራስን ችሎታ በወቅቱ አለመቀመጥ: አለመሄድ: ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነ የሰዉነት ማንዘፍዘፍ: ግትር ማለት: አንዲሁም አስቀመጨረሻው ሲያድጉ በራስ መመገብ (ጡት መጥባት አለመቻል): መናገር አና መሄድ አለመጀመርም ሊከሰት ይችላል::

ማሳሰቢያ፦ "መታፈን" የሚለው ቃል የጨቅላ ሕፃናትን የአፍንጫ መታፈን (Nasal Congestion) ለማመልከት አይደለም። ይህ ከሆነ ግን መፍትሄው አፍንጫን በጨው ውሃ (Saline drops) ማጽዳትና ንፅህናን መጠበቅ ነው.
ስለ እርግዝና ክትትል አስፈላጊነት ወይም ስለ አራስ ሕፃናት እንክብካቤ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይፈልጋሉ?
አንግድያዉስ ማብራሪያ የምትፈልጉበትን ጉዳይ ይጥቀሱ
ማብራሪያ ይቀርብሎታል::

 #ስለ ቶንሲል እድገት፣ የቀዶ ጥገና አስፈላጊነት እና ከልብ ሕመም ጋር ስላለው ቁርኝት እነሆ፦1.  #ቶንስል አስከ 5 ዓመትና ከዚያ በህዋላ ቶንሲል የሰውነት በሽታ መከላከል ሥርዓት አካል ...
17/03/2026

#ስለ ቶንሲል እድገት፣ የቀዶ ጥገና አስፈላጊነት እና ከልብ ሕመም ጋር ስላለው ቁርኝት እነሆ፦

1. #ቶንስል አስከ 5 ዓመትና ከዚያ በህዋላ

ቶንሲል የሰውነት በሽታ መከላከል ሥርዓት አካል ሲሆን፣ በተለይ እስከ 5 እና 6 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ በጣም ንቁ እና መጠናቸው ትልቅ ይሆናል።
ከ5 ዓመት በኋላ፦ የልጁ በሽታ የመከላከል አቅም እየዳበረ ሲሄድ የቶንሲል አስፈላጊነትና መጠኑም እየቀነሰ ይመጣል።

#መቀነስ፦ በአብዛኛው ከጉርምስና (Puberty) በኋላ ቶንሲሎች መጠናቸው እየቀነሰ እና እየተኮማተሩ (Atrophy) ይሄዳሉ። ስለዚህ ብዙ ሕፃናት በዕድሜ እየጨመሩ ሲሄዱ የቶንሲል ኢንፌክሽን መደጋገም ይቀንስላቸዋል።

2. #አስቸኳይ የቀዶ ጥገና ሁኔታዎች

ቶንሲልን በቀዶ ጥገና ለማውጣት (Tonsillectomy) ውሳኔ የሚሰጠው ቶንስል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሲያመዝን ብቻ ነው። ዋና ዋናዎቹ ሁኔታዎች፡-
ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን፦ በአንድ ዓመት ውስጥ 7 ጊዜ፣ ወይም በሁለት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 5 ጊዜ፣ ወይም በሦስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 3 ጊዜ እና ከዚያ በላይ የቶንሲል ሕመም ከተከሰተ።
የመተንፈስ ችግር (Sleep Apnea)፦ ቶንሲሉ በጣም ከማበጡ የተነሳ በእንቅልፍ ወቅት የመተንፈስ መቆራረጥ ወይም ከባድ ማንኮራፋት ካመጣ።
የመዋጥ ችግር፦ ምግቦችን ለመዋጥ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ የልጁን ዕድገት የሚጎዳ ከሆነ።
መግል መቋጠር (Peritonsillar Abscess)፦ በቶንሲል ዙሪያ መግል ተከማችቶ በባክቴሪያ መድኃኒት ካልዳነ።

3. #ከልብ ሕመም ጋር ያለው ቁርኝት
ይህ በጣም ወሳኝ ነጥብ ነው። የቶንሲል ኢንፌክሽን በቀጥታ የልብ ሕመም አይደለም፤ ነገር ግን ካልታከመ ወደ ልብ ሕመም ሊያመራ ይችላል፦ ለዚህ ደግሞ ዋና የሚባለው ዉሳኔ የሕፃናት ሀኪም አንድያየው ማድረግ ነው::

#የመንስኤው ባክቴሪያ፦ ቶንሲልን የሚያጠቃው "Group A Streptococcus" የተባለ ባክቴሪያ በአግባቡ በባክቴሪያ መድኃኒት (Antibiotics) ካልታከመ፣ የሰውነት መከላከል ሥርዓት ባክቴሪያውን ለመምታት ሲሞክር በስህተት የልብ ቫልቮችን ሊያጠቃ ይችላል። ይህም በጣም ጥቂቶች ላይ ሊከሰት ይችላል::
ነገር ግን የቶንስል እንፌክሽን ምክንታቱ ባክተርያ ብቻ አይደለም
* ቫይረስ.... ከፍተኛ ድርሻ አለው
* አለርጂ
* አንዳንዴም ሌላ አብጠት ሊሆን ስለሚቺል ቀዶ ጥገና አንዴ ብቻኛ አማራጭ ማየት ተገቢ አይደለም
#ሩማቲክ ፊቨር (Rheumatic Fever)፦ ይህ የልብ መገጣጠሚያዎችን እና ቫልቮችን የሚጎዳ ሕመም ነው። የቶንሲል ኢንፌክሽን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ካልታከመ ወደዚህ ከባድ የልብ ሕመም ሊቀየር ይችላል። ለዚህ ዋና የሚባለው ሕክምና ደግሞ የልጆች ሐኪሞ ጋር ክትትል ና ምክር ማግኘት ነው::
#ጥንቃቄ፦ ቶንሲል ባለበት ወቅት የሚታዘዝን አንቲባዮቲክ መድኃኒት አቋርጦ አለመተው ለዚህ ነው የሚመከረው።
#ቶንስል በቀዶ ጥገና ከተወገደ በህዋላ የቶንስል እንፌክሽን
ሊይዘን ይችላሎይ??..............
በአርግጥ ቀዶ ጥገና (tonsillectomy) ለሚያስፈልጋቸው ልጆች ትልቅ ጠቀሜታ አለው::

ነገር ግን የሚከተሉትን ነጥቦች ማወቅ አስፈላጊ ነው፦
የጉሮሮ መቁሰል (Pharyngitis)፦ ቶንሲል ቢወገድም የጉሮሮዎ ግድግዳ በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ሊቆጣ ይችላል። ይህ ከቶንሲል ሕመም ጋር ተመሳሳይ ስሜት ቢኖረውም "የጉሮሮ መቁሰል" እንጂ የቶንሲል በሽታ አይደለም።
ስትሬፕ ስሮት (Strep Throat)፦ ቶንሲል የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በስትሬፕቶኮከስ ባክቴሪያ የሚመጣ የጉሮሮ ኢንፌክሽን ሊይዛቸው ይችላል።
የቶንሲል ቁርጥራጭ መተረፍ (Tonsil Regrowth)፦ አልፎ አልፎ በቀዶ ጥገና ወቅት ትንሽ የቶንሲል ክፍል ተርፎ ከሆነ፣ ያ የተረፈው ክፍል አድጎ ኢንፌክሽን ሊያስተናግድ ይችላል። ነገር ግን ይህ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው።
ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚከሰት ኢንፌክሽን፦ ቀዶ ጥገናው እንደተደረገ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት የቁስሉ ቦታ በባክቴሪያ ሊጠቃ ይችላል። ይህ በቶሎ በሕክምና መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው።
ባጠቃላይ፦ ሰርጄሪው የሚደረገው ተደጋጋሚ የቶንሲል ኢንፌክሽንን ለማስቀረት ስለሆነ፣ ከቀዶ ጥገና በኋላ የሕመሙ መደጋገም በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል: ሜዲካል ኬሩን ግን ሊተካ አይችልም ::
ሪስክ ኦፍ እንፌክሽኑም ቀዶ ጥገና ከተሰራ ከሁለት ዓመት በሁዋላ አንደህዝብ ( General populiation) አኩል ነው::

27/12/2025

# #የልጆችን አድገት ከሚጉዱ አና ለተለያዩ በሽታዎች በር ከሚከፍቱ የንጥረ-ነገሮች: አጥረት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ዉስጥ አንዱ ነው , , ,
ቫይታሚን ዲ ( Vitamin D)
በተለየ መልኩ ለእነማን ያስፈልጋል?
(ታርጌት ግሩፕስ)
1. ያለግዝያቸው የተወለዱ ሕፃናት: premature babies
2. በአግባቡ የፀሐይ ብርሃን(ጨረር ) ያላገኙ ሕፃናት
3. በዓለማቺን በ ሰሜኑ ንፍቀክበብ የሚኖሩ ሕፃናት
4. በ ሀኪም ምርመራ የተለዩ ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት
5. አድምያቸው የገፋ አናቶች (ሜኖፖሰ)

ቫይታሚን ዲ ጤናማ አጥንትን ለመገንባት እና ለመጠበቅ ሰውነታችን የሚያስፈልገው ንጥረ ነገር ነው። ምክንያቱም ሰውነትዎ ካልሲየም የሚባለውን የአጥንት ዋና አካል ቫይታሚን ዲ ሲገኝ ብቻ ነው የሚይዘው።
ይህ ካልስየም የተባለው ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም ለመመጠጥ ቫይታሚን D ያስፈልጋል::

ቫይታሚን ዲ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉ ሌሎች ብዙ ሴሉላር ተግባራትን ይቆጣጠራል። ፀረ-ብግነት ፣አንቲኦክሲደንትስ እና የነርቭ መከላከያ ባህሪያቱ የበሽታ መከላከያ ጤናን የጡንቻን ተግባር እና የአንጎል ሴሎች እንቅስቃሴን ይደግፋሉ።
ለልጆች በሽታ ለመከላከል የሚያስችል ጉልበት ይፈጥራል:: በተለይ በሳንባምች የመጠቃት አድላቸዉን ይቀንሳል:: immune modulatory effect ስላለው::

ቫይታሚን ዲ በተፈጥሮው በብዙ ምግቦች ውስጥ አይገኝም፣ ነገር ግን ፎርቲፊይድ ከሆነ ወተት፣ከእንቁላል አስኳል፣ ከተመረተ እህል እና ከሰባ ዓሳ ለምሳሌ ሳልሞን፣ ማኬሬል እና ሰርዲን ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ቀጥተኛ የፀሐይ ብርሃን በቆዳዎ ውስጥ ያለውን ኬሚካል ወደ ንቁ የቫይታሚን (ካልሲፌሮል) ቅርፅ ሲቀይር ሰውነትዎ ቫይታሚን ዲ ይሠራል።

ቆዳዎ የሚያመርተው የቫይታሚን ዲ መጠን በብዙ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፡ ይህም የቀን ሰአት፣ ወቅት፣ ኬክሮስ እና የቆዳ ቀለምዎን ጨምሮ። በሚኖሩበት ቦታ እና በአኗኗርዎ ላይ በመመስረት የቫይታሚን ዲ ምርት በክረምት ወራት ሊቀንስ ወይም ሙሉ በሙሉ ሊቀር ይችላል። የፀሐይ መከላከያ የቆዳ ካንሰርን ለመከላከል ጠቃሚ ቢሆንም የቫይታሚን ዲ ምርትንም ይቀንሳል።
መልቲ ቫይታሚን ከቫይታሚን ዲ ጋር መውሰድ የአጥንትን ጤንነት ለማሻሻል ይረዳል። የሚመከረው ዕለታዊ የቫይታሚን ዲ መጠን እስከ 12 ወር ለሆኑ ህጻናት 400 ኢንተርናሽናል ዩኒት (IU)፣ ከ1 አመት በላይ ሕፃናት 800 IU ነው።
ይህ መጠን vit D አጥረት አንዳለባቸው ለታወቁት አይደለም::

የቫይታሚን ዲ እጥረት ምልክቶች

አብዛኛዎቹ የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው ሰዎች ምንም ምልክቶች አያሳዩም ሌሎች ደግሞ የማንኛውንም ህመም ምልክቶች ሊሆኑ የሚችሉ ግልጽ ያልሆኑ ምልክቶችን ሊያስተውሉ ይችላሉ። ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: ለተደጋጋሚ የሳንባ ምች መጋለጥ
• የጡንቻ ሕመም
• የአጥንት ህመም
• ለህመም ስሜት መጨመር
• በእጆቹ ወይም በእግሮቹ ላይ "የሚዋጋ መርፌ" ስሜት
• በሰውነት ክፍሎች እንደ የላይኛው ክንዶች ወይም ጭኖች ያሉ የጡንቻዎች ድክመት
• በእግር ውስጥ ጡንቻዎች ድክመት በእግር በሚጓዙበት ጊዜ መንቀጥቀጥ ምክንያት
• የአጥንት ስብራት ታሪክ
• የጡንቻ መንቀጥቀጥ ወይም መንቀጥቀጥ
• የጡንቻ መወዛወዝ
• የታጠፉ እግሮች (ብራኬት እግሮች) በጣም ከፍተኛ የሆነ እጥረት ሲኖር

የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዴት ይመረመራል?
ብዙውን ጊዜ ምንም ምልክቶች ስለሌሉ የቫይታሚን ዲ እጥረትን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። የቫይታሚን ዲ መጠንን የሚመረምር የደም ምርመራ ለምርመራ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።ለሁሉም ታካሚዎች በመደበኛነት አይታዘዝም። አንድ በሽተኛ እንደ አጥንት ወይም የጡንቻ ህመም ያሉ ምልክቶችን ሪፖርት ካደረገ ወይም ሌሎች የቫይታሚን ዲ እጥረትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ የጤና እክሎች ካሉት ዶክተሮች ይህንን ምርመራ ያዛሉ።

ጥናቶች ምን ይላሉ
ለተወሰኑ ሁኔታዎች የቫይታሚን ዲ አጠቃቀም ላይ የተደረገ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፡-
• የማገናዘብ (ኮግኒቲቭ) ጤና ይጠብቃል - ጥናቶች እንደሚያሳዩት በደም ውስጥ ያለው የቫይታሚን ዲ ዝቅተኛ መጠን ከግንዛቤ መቀነስ ጋር የተያያዘ ነው።
• በዘር የሚተላለፍ የአጥንት በሽታዎች ለማከም ይረዳል - የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ቫይታሚን ዲ ለመምጠጥ ወይም ለማቀነባበር ባለመቻሉ ያሉ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማከም ያገለግላሉ።
• መልቲፕል ስክለሮሲስ የተባለውን የነርቭ ህመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል - መልቲፕል ስክለሮሲስ በማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሥር የሰደደ በሽታ ሲሆን ይህም የአንጎልንና የአከርካሪ አጥንትን ያጠቃል።ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የረጅም ጊዜ ቫይታሚን ዲ መውሰድ ይመልቲፕል ስክለሮሲስ ተጋላጭነትን ይቀንሳል።
• ኦስቲኦማላሲያ- ቫይታሚን ዲ ላይ ከባድ በቫይታሚን ዲ እጥረት ምክንያት የአጥንት ማዕድናት ይዘት፣የአጥንት ህመም፣ የጡንቻ ድክመት እና ለስላሳ አጥንት (osteomalacia) ለማከም ያገለግላሉ
• ኦስቲዮፖሮሲስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቂ ቪታሚን ዲ እና ካልሲየም በአመጋገባቸው ውስጥ የሚያገኙ ሰዎች የአጥንትን ማዕድን መቀነስን፣ ኦስቲዮፖሮሲስን ለመከላከል እና የአጥንት ስብራትን ለመቀነስ ይረዳሉ።
• ሶሪያሲስ(Psoriasis) - ቫይታሚን ዲ ወይም ካልሲፖትሪን የተባለውን የቫይታሚን ዲ ውህድ ቆዳው ላይ መቀባት በአንዳንድ ሰዎች ላይ የፕሌክ ዓይነት ሶሪያሲስን ማከም ይችላል።
• ሪኬትስ ይህ ሁኔታ የቫይታሚን ዲ እጥረት ባለባቸው ልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን ቫይታሚን ዲ በመስጠት ችግሩን መከላከል እና ማከም ይቻላል።

በተገቢው መጠን ሲወሰድ ቫይታሚን ዲ በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይቆጠራል
ይሁን እንጂ ከመጠን በላይ የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን ወይም ሲረፕ መዉሰድ ሊያስከትላቸው የሚቺሉ ችግሮች አሉ::
የፀሐይ ብርሃንን አንዴት አንጠቀማለን?
መቼ አና ምን ያህል ለስንት ጊዜ የሚለዉን
በቀጣይ ፅሁፍ አስቀምንገናኝ ወንድም አህቶቻችን ይጠቀሙበት ዘንድ ሼር አድርጉላቸው::

 # #መቼም ቢሆን  # #ልጆችን  # #ለማሳደግ ማስታወስ ያለባችሁ ነጥብ.....🙅🙅
21/11/2025

# #መቼም ቢሆን # #ልጆችን # #ለማሳደግ ማስታወስ ያለባችሁ ነጥብ.....🙅🙅

We have to appreciate and acknowledge such incredible works!! Abebech Gobena Hospital በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶት የእናትን ጭ...
20/11/2025

We have to appreciate and acknowledge such incredible works!! Abebech Gobena Hospital በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶት የእናትን ጭንቀት ወደ ደስታ የቀየረው የተሳካ ሕክምና
********

በአፍሪካ ለመጀመሪያ በዓለም ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ግሩም የሕክምና ጥበብ የተስተዋለበት ሥራ የተከናወነው በኢትዮጵያ ነው።

በእናቱ ሆድ ውስጥ ብዙ ጊዜ ደም እየተለገሰው የነበረው ሕጻን በትናትናው እለት ወደዚህች ምድር በጤንነት ተቀላቅሏል፡፡

ወይዘሮ ሰናይት ታምራት ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናዋ በተፈጠረባት የሾተላይ ችግር ምክንያት ልጇን አጥታለች፡፡

በጤና ጣቢያ ክትትሏን ታደርግ የነበረችው የ28 ዓመቷ ታካሚ፣ ቀደም ሲል በተፈጠረባት ችግር ምክንያት 'ዳግም ልጄን አጣው ይሆን' የሚል ከፍተኛ ጭንቀት ገብቷታል፡፡

ይህች እናት 21 ሳምንት ሲሆናት ክትትል ከምታደርግበት ጤና ጣቢያ በተፃፈላት ሪፈር መሰረት ወደ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ማዕከል ታመራለች፡፡

የአበበች ጎበና የእናቶች እና የህፃናት ሕክምና ማዕከል ባደረገው ምርመራ ፅንሱ በሾተላይ ምክንያት የደም ማነስ እንዳጋጠመው ደረሰበት፡፡

ቀደም ሲል በሾተላይ ምክንያት ልጇን ላጣች እና አሁን በሆድዋ ለተሸከመችው ልጅ በጭንቀት ውስጥ ላለች እናት መፍትሔ ፍለጋ የተቋሙ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ማድረግ ስለሚችሉት ነገር ምክክር ጀመሩ፡፡

ፅንሱ ገና የ21 ሳምንት መሆኑ የታሰበውን ሕክምና ከባድ አድርጎታል፡፡

በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ የደም ማነስ ችግር ላጋጠመው የ21 ሳምንት ብቻ ዕድሜ ላለው ፅንስ የደም ስሮቹ ደም ለመስጠት የሚያስቸግሩ ቀጫጭን ቢሆኑም፣ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም የመስጠት ሕክምና ማድረግ ለፅንሱ ህልውና አማራጭ የሌለው መፍትሔ እንደሆነ ለታካሚዋ ተነገራት፡፡

የመጀመሪያው ደም የመለገስ ሕክምናም እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ተከናወነ። ታካሚዋ የመጀመሪያዎቹን ወራቶች በሳምት ሁለት ቀን ለክትትል ወደ ሕክምና ተቋሙ በማምራት አስፈላጊውን ክትትል ስታደርግ ቆየች፡፡

ፅንሱ ሕክምናውን እያገኘ መፋፋት እና እድገት ማሳየት ሲጀምር በሳምት አንዴ በመምጣት ክትትሉ ቀጠለ፡፡

ለእናት እና ለልጅ ጥብቅ የሆነ ክትትል በማድረግ ደም የመለገስ ሂደቱ እስከ 10 ጊዜ ቀጥሎ ፅንሱ የመወለጃው ጊዜ ሲደርስ በቀዶ ሕክምና 3.5 ኪ.ግ የሚመዝን ልጅ በሰላም ተገላግላ እናት ልጇን ማቀፍ ችላለች፡፡

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ሕክምና ማዕከል የተፈጠረው ይህ ታሪክ፣ በሕክምናው ታሪክ በዓለም በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም ተለግሶ ስኬታማ የሕክምና ክትትል በማድረግ ወደዚህ ዓለም የተቀላቀለ ሁለተኛው ልጅ ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ፅንስ በእናቱ ሆድ እያለ 10 ጊዜ ደም ተሰጥቶት የተሳካ የሕክምና ሂደት አልፎ የተወለደው በብራዚል ሲሆን፣ በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመሪያው የ21 ሳምንት ፅንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ 10 ጊዜ ደም በመሰጠት ስኬታማ የሕክምና ሒደት አልፎ በስኬት የተወለደ መሆኑ ልዩ አድርጎታል፡፡

ሕክምናው በኢትዮጵያ ውስጥ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በየካቲት 12 የአበበች ጎበና የእናቶች እና ህፃናት ሕክምና ማዕከል የሚሰጥ ሲሆን 30 ሳምንት እና ከዛ በላይ የሆነ እድሜ ያለው ፅንስ የእናት ሆድ ውስጥ እንዳለ የመወለጃው ቀን እስኪቃረብ ድረስ ደም የመስጠት ሒደት የተለመደ ነው፡፡

በአሁን ሰዓት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶች እና ህፃናት ህክምና ማዕከል እናት እና ልጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

20/11/2025

አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ከተለያዩ መፀሃፍት አና መደብር ሳይቆራረጥ ለማድረስ የተከፈተ ድኅረ ገፅ ቢሆንም የተለያዩ ወቅታዊ አና ስሜትን የሚጎዱ ሃገራዊ ሁኔታዎች ሙያዊ ስራን በነፃነት ለመስራት አንቅፋት መሆናቸው ግልፅ ነው:: የተለያዩ ወንድም አህቶችን ስሜት መጠበቅም አስፈላጊ በመሆኑ ለአመታት በሚፈለገው መልኩ ሞያዊ አገዛ አላደረገም:: ይሁን አንጂ አልፎ አልፎም ቢሆን አንዳንድ ሙያው ምክረ ሃሳቦችን አስተላልፌያለሁ አሁንም ማካፈል አወዳለሁ:: መልካም ቀን ይሁንላቺሁ!!

# # ቅርበት
:::::::::::::::

ልጆች ከመብላት እና መጠጣት ባለፈ ከወላጆቻቸው(ከአሳዳጊያቸው) መቀራረብን ይሻሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወላጅ ልጅ ትስስር በተጠናከረ ቁጥር የልጆች የአእምሮ፣ የጤና፣ የስሜት፣ እና የመስተጋብር ክህሎታቸው ያድጋል፤ይበለፅጋል፡፡

በ Duke's University ለ30 አመታት የዘለቀ ተከታታይ ጥናት በልጅነታቸው በወላጅና ልጅ መካከል ጥብቅ የስሜት ትስስር ኖሯቸው ያደጉ ልጆች ከሌሎች ልጆች የተሻለ በራስ መተማመን ፣ ደስተኛ፣ በት/ቤት የተሻለ ውጤት ማግኘትና ችግር ቢገጥማቸው የመፍትሄ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል።

ምንም እንኳን ሁላችንም በተፈጥሮ የመቀራረብ አቅም (Potential intimacy) የተሰጠን ቢሆንም እንደ ችግኝ በመኮትኮት ማሳደግ የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው፡፡

✅ በወላጅ እና በልጅ መካከል ያለውን ቅርርብ ለማሳደግ

1. አብሮ መጫወት
2. በጋራ መብላት
3. ልጆችን መስማት
4. ፍቅርን ማሳየት
5. ጤናማ እና ሚዛኑንን የጠበቀ ገደብ ማድረግ
6. በቤተሰብ የጋራ ጊዜ የማሳለፍ ልማድ ማዳበር!

Be careful!! ይህንን መረጃ ተረጋግታችሁ አንብቡት:: Ministry of Health
18/11/2025

Be careful!! ይህንን መረጃ ተረጋግታችሁ አንብቡት::
Ministry of Health

We are waiting for you!!
31/03/2025

We are waiting for you!!

የዘመቻ ሕክምና ሰላም አንደምን አላችሁ? ጥብቅ መልአክት ይዤ መጥቻለሁ: ላልሰማ አሰሙ በጣም ጠቃሚ ነው:: የብዙዎችን ችግር ይፈታል::ከየካቲት 25 አስከ የካቲት 29/2017 ዓ. ም በደሴ ...
23/02/2025

የዘመቻ ሕክምና
ሰላም አንደምን አላችሁ? ጥብቅ መልአክት ይዤ መጥቻለሁ: ላልሰማ አሰሙ በጣም ጠቃሚ ነው:: የብዙዎችን ችግር ይፈታል::
ከየካቲት 25 አስከ የካቲት 29/2017 ዓ. ም በደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል እግራቸው የተቆለመመ (የዞረ ) ልጆች ና አዋቂዎች በዘመቻ ስለሚካሄድ በተባለው ጊዜ በመገኘት ሕክምናዉን አንድያገኙ ሲል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል:: ደብዳቤዉን ከስር አያይዜዋለሁ::

Dear CMHS Team,  and leadersI would like to take a moment to express my deepest gratitude to CMHS, Wollo University for ...
22/02/2025

Dear CMHS Team, and leaders

I would like to take a moment to express my deepest gratitude to CMHS, Wollo University for the invaluable support, guidance, and opportunities you have provided. As a cornerstone of growth and development, your institution has played a pivotal role in shaping not only my career but also my personal growth.

The foundation and values instilled by CMHS, Wollo University continue to inspire and guide me in all my endeavors. Your commitment to excellence, innovation, and community has left an indelible mark, and I am truly honored to be associated with such a prestigious institution.

Thank you for being a beacon of knowledge and a source of unwavering support. I look forward to continuing this meaningful relationship and contributing to the legacy of Wollo university, CMHS in any way I can.

With sincere appreciation,

Thank you very much Wollo university PCH energetic, responsible and dedicated staff, WU and DCSH admin and staff, my mom...
21/02/2025

Thank you very much Wollo university PCH energetic, responsible and dedicated staff, WU and DCSH admin and staff, my mom and wife, EMA board members, and those who are with me at large!! 🙏🙏

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913252415

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Robel ዶ/ር ሮቤል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Robel ዶ/ር ሮቤል:

Share