Dr. Emebet Eshetu

Dr. Emebet Eshetu የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሃኪም ለህክምና ቀጠሮ ለመያዝ | www.dremebet.et

እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ! ዛሬ ቀጠሮ ለሚይዙ፣ ለመጀመሪያ 15 ተጠቃሚዎች በመረጡት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሃኪም፣ የቪዲዮ ህክምናና ማማከር ላይ የ 99% ቅናሽ አድርገናል።ዘሬ ...
11/05/2025

እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ!
ዛሬ ቀጠሮ ለሚይዙ፣ ለመጀመሪያ 15 ተጠቃሚዎች በመረጡት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሃኪም፣ የቪዲዮ ህክምናና ማማከር ላይ የ 99% ቅናሽ አድርገናል።

ዘሬ ቀጠሮ ይዘው፣ ሀኪሞችን ከዛሬ ጀምሮ፣ በሳምንት ውስጥ በሚመችዎት ቀን መርጠው ያማክሩ።

👉🏼 ቀጠሮ ሲይዙ፣ ሃኪሞችን ከመረጡ በኋላ Appl Promocode የሚለውን በመጫን የ99% ቅናሽኑ ይተግብሩ።

የቴሌሜድስን መተግበሪያውን ያውርዱ።

👇For Android
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.tenadoc

👇For iPhone, iOS
https://apps.apple.com/us/app/tenadoc/id6743532775

ጤናዶክ ዲጂታል ሄልዝኬር
👩🏻‍⚕️👨🏽‍⚕️

💟

Tenadoc - ጤናዶክ@followers

እርግዝና ስታስቢ፡ ማወቅ ያለብሽ የቅድመ እርግዝና ዝግጅቶች​በአደጉ አገሮች ጭምር እስከ 50% ያልታቀደ እርግዝና ይፈጥራል። እርግዝና እንዲፈጠር ስታቅጅ፣ ጤናማ የሆነ ጽንስ እንዲፈጠር፣ የሚ...
03/05/2025

እርግዝና ስታስቢ፡ ማወቅ ያለብሽ የቅድመ እርግዝና ዝግጅቶች​

በአደጉ አገሮች ጭምር እስከ 50% ያልታቀደ እርግዝና ይፈጥራል።

እርግዝና እንዲፈጠር ስታቅጅ፣ ጤናማ የሆነ ጽንስ እንዲፈጠር፣ የሚያስፈልጉሽ የቅድመ እርግዝና ዝግጅቶች፤

👉🏼 ቢያንስ እርግዝና ከመሞከርሽ ከሁለት ወር በፊት ( 0.4mg እስከ 0.8mg ) ፎሊክ አሲድ በየቀኑ መወሰድ፣ በጽንሱ አፈጣጠር ላይ ችግር እንዳይኖር ይረዳል።
👉🏼 ጤናማ ምግቦችን መመገብ
👉🏼 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
👉🏼 የጥርስ ንጽህናን መጠበቅ
👉🏼 መጠነኛ የሆን የሰውነት ክብደት ላይ መሆን ይኖርብሻል (ከበቂ ክብደት በታችም ወይም ከበቂ ክብደት በላይ መሆን የለብሽም)
👉🏼 አንችንና ጽንሱን ከሚጎዱ ነገሮች መራቅ፡ እንደ ( ሲጋራና ሽሻ ማጨስ፡ ከልኮል መጠጣት፡ አደንዛዥ እጽ መጠቀም እና ሌሎች አነቃቂ መድሃኒቶች መውሰድ )
👉🏼 በሃኪም ያልታዘዙ መድሃኒቶችን ከመውሰድ በፊት ሃኪምሽን ማማከር
👉🏼 በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎችን ኤች አይ ቪን ጨምሮ ምርመራ ማድረግ እንዱሁም የሄፒታይተስ B እና C ምርመራ ምድረግ
የደም አይንት መርመራ ማድረግ
👉🏼 ከዚህ በፊት የሚታወቁ በሽታዎችን ለሃኪምሽ ማሳውቅ፡ እንደ ( የአስም፡ የስኳር ፡ የልብና የታይሮይድ በሽታውችን )
👉🏼 ከዚህ በፊት እርግዛና ላይ ያጋጠሙሽ ችግር ካሉ ለሃኪምሽ ማማከር፡ እንደ (የአፈጣጠር ችግር፡ ቀኑ ሳይደርስ መውለድ፡ በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የደም ግፊት፡ ስኳር፡ በወሊድ ጊዜ የሚያጋጥም የደም መፍሰስ፡ በእርግዝና ጊዜ የደም መርጋት )

እርግዝና ስታስቢ በትንሹ ከ ሶስት ወር ቀደም ብለሽ ከሃኪምሽ ጋር የቅድመ እርግዝና ምርመራዎችና ምክር አገልግሎት መውሰድ፡ ጤናማ ልጅ እንዲኖሽ ይረዳል፡፡

💟

የቴሌሜድስን መተግበሪያውን ያውርዱ።

👇For Android
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.tenadoc

👇For iPhone, iOS
https://apps.apple.com/us/app/tenadoc/id6743532775

ስለ ማህፀንና ፅንስ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማንበብ ከታች ባለው ሊንክ ይጠቀሙ።
06/01/2024

ስለ ማህፀንና ፅንስ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማንበብ ከታች ባለው ሊንክ ይጠቀሙ።

ጡት ማጥባት፡ ለአንችና ለልጅሽ ያሉት ጠቀሜታዎች የእናት ጡት ወተት ለጨቅላ ልጅሽ የተሟለ ምግብ የያዘ ሴሆን በተጨማሪ የተለመዱ የህጻናት በሽታወችን፡ ለመከላከል የሚረዱ አንቲቦዲስ .....

ከማህፀን ውጪ እርግዝናከማህጸን ውጪ እርግዝና፣  በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ከፍተኛ ለሆነ ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥል ለሚችል የደም መፍሰስ ይዳርጋል።    ከማህጸን ውጪ እርግዝና በመጀመ...
19/12/2023

ከማህፀን ውጪ እርግዝና

ከማህጸን ውጪ እርግዝና፣ በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ከፍተኛ ለሆነ ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥል ለሚችል የደም መፍሰስ ይዳርጋል።

ከማህጸን ውጪ እርግዝና በመጀመሪያ ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል ወይም ከመሃፀን ውስጥ ካለ እርግዝና ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።

እነዚህም የወር አበባ መቅረት፣ የጡት ህመም እንዲሁም ማቅለሽለሽና የእርግዝና ምርመራ ላይ እርግዝና ማሳየት ናቸው።

ከማህፀን ውጪ እርግዝና ምልክቶች
የሆድ ህመምና ከማህፀን ደም መፍሰስ ናቸው።

እነዚህ ምልክቶች ካጋጠሙ ከማህፀን ውጪ እርግዝና መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ የደም ምርመራዎችንና የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
👇

Check out Dr. Emebet Eshetu 🩺's video.

ከዚህ በፊት ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያጋጠማት ሴት፣ ማድረግ ያለባት ጥንቃቄ
18/12/2023

ከዚህ በፊት ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያጋጠማት ሴት፣ ማድረግ ያለባት ጥንቃቄ

Check out Dr. Emebet Eshetu 🩺's video.

እርግዝና እየሞከሩ ባሉ ጥንዶች፣ እርግዝና የመፈጠር እድሉ በ አማካኝ...
28/11/2023

እርግዝና እየሞከሩ ባሉ ጥንዶች፣ እርግዝና የመፈጠር እድሉ በ አማካኝ...

41 likes, 2 comments. “እርግዝና እየሞከሩ ያሉ ጥንዶች፣ ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙና፡ በቂ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት እያደረጉ እርግዝና የመፈጠር እድሉ በአማካኝ፡ በ 1 ወር ው...

የመካንነት ምርመራ መች መጀመር አለብሽ?
18/11/2023

የመካንነት ምርመራ መች መጀመር አለብሽ?

2608 likes, 69 comments. “የመካንነት ምርመራ መች መጀመር አለብሽ? . Emebet Eshetu”

የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራዎች፣የጡት ካንሰር  ቀደም ብሎ ከታወቀ በሕክምና የመዳን  ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ ቅድመ ምርመራ  ማድረግ   የጡት ካንሰር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንዳለ ሳይስፋ...
28/10/2023

የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራዎች፣

የጡት ካንሰር ቀደም ብሎ ከታወቀ በሕክምና የመዳን ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡

ስለዚህ ቅድመ ምርመራ ማድረግ የጡት ካንሰር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንዳለ ሳይስፋፋ ለማወቅና አስፈላጊውን የሕክምና ለማድረግ ይረዳል።

ከ 20 ዓመት በላይ የሆነች ማንኛውም ሴት፣ በየወሩ ጡቶቿን፣ በቤት ውስጥ፣ በመስታዎት በማየት እና በመነካካት መፈተሽ ይኖርባታል።

እድሜያቸው ከ20 - 39 አመት የሆኑ ሴቶች፣ ቢያንስ በየ ሁለት ዓመቱ እና እድሜያቸው ከ40 እስከ 50 የሆኑ ሴቶች በየዓመቱ ህክምና ቦታ በመሄድ በጤና ባለሙያ የሚደረግ የጡት ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

እንዲሁም እድሜያቸው ከ50 እስከ 74 የሆኑ ሴቶች፣ በየ 2 ዓመቱ ማሞግራም እንዲነሱ ይመከራል።

Check out Dr. Emebet Eshetu | OB/GYN's video.

ሰላም፣ትምህርታዊና እንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች ሲለቀቅ፣ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ስልካችሁን ካታች ባለው ሊንክ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ።
27/10/2023

ሰላም፣
ትምህርታዊና እንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች ሲለቀቅ፣ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ስልካችሁን ካታች ባለው ሊንክ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ።

Register your mobile number to receive free SMS notification about women's healthcare post & Dr. Emebet Eshetu's work schedule updates

ማወቅ ያለብሽ የጡት ካንሰር ምልክቶችየጡንት ካንሰር በአለም ላይ በስፋት የሚከሰት የካንሰር አይነት ሲሆን፡ ባደጉ አገሮች ከ8 ሴት አንዷ በጡት ካንሰር ትጠቃለች፡የጡር ካንሰር ምልክቶች፡📌 በ...
16/10/2023

ማወቅ ያለብሽ የጡት ካንሰር ምልክቶች

የጡንት ካንሰር በአለም ላይ በስፋት የሚከሰት የካንሰር አይነት ሲሆን፡ ባደጉ አገሮች ከ8 ሴት አንዷ በጡት ካንሰር ትጠቃለች፡

የጡር ካንሰር ምልክቶች፡

📌 በጡት እና በብብት ላይ የሚወጣ ዕባጭ
📌 በጡትና በጡት ጫፍ ላይ የሚከሰት ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ህመም
📌 ጡት ውስት በዳሰሳ የሚገኝ የጡት ህዋሶች መወፈር
📌 የጡት ቆዳ መቅላት ወይም የቆዳ ቀለም መቀየር
📌 የጡት ቆዳ መሰርጎድ ወይም መወፈር
📌 የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት
📌 በጡት ጫፍ የሚዎጣ ለየት ያለ ፈሳሽ ወይም ደም
📌 ሁለቱ ጡቶች ሲነፃፀር የጡት ቅርፅ እና መጠን መለወጥ

እነዚ ምልክቶችን ካየሽ ወደ አቅራቢያሽ ሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርብሻል፡፡

ቪዲዮውን፣ ቲክቶክ ላይ ከታች ባለው ሊንክ ያገኙታል።

Check out Dr. Emebet Eshetu | OB/GYN's video.

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251944457777

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Emebet Eshetu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr. Emebet Eshetu:

Share