
02/10/2023
የጡት ካንሰር እና እርግዝና
👉 ጡት ካንሰር ከ 3000 እርግዝና ውስጥ በ አንዱ እንደሚከሰት ጥናቶች ያሳያሉ።
👉 የሚከሰተውም በ ጡት ላይ ያሉ ህዋሳት ወደ ካንሰርነት ሲቀየሩ ነው ።
ምልክቶች
❗️በጡት እና ብብት አከባቢ እብጠት መኖር
❗️ የጡት መጠን ለውጥ መኖር
❗️የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሰርጎድ
❗️ ከወተት ውጪ ሌላ ፈሳሽ ማፍሰስ
❗️የጡት ቆዳ መቅላት፣ ማበጥ
❗️ልክ የብርቱኳን ሽፋን ዓይነት መልክ መያዝ እና ሌሎችም
አጋላጭ ሁኔታዎች
👉 ፆታ ሴት መሆን
👉 ከቤተሰብ ( እናት፣ እህት ወይም ልጅ)
👉 ማጨስ
👉 ውፍረት
👉 ለጨረር መጋለጥ
👉 አልኮል እና ሌሎችም
❓ በሆርሞን ለውጥ ምክንያት በእርግዝና ወቅት የጡት መጠን ይጨምራል። ይህ መሆኑ ደግሞ የጡት ካንሰርን በእርግዝና ወቅት በምርመራ ማረጋገጥ አዳጋች ያደርገዋል።
ስለዚህ የጡት ምርመራ በእርግዝና ክትትል ወቅት አንዱ መደረግ ያለበት ነገር ነው።
🚨 ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ካዩ ወይም ጥርጣሬ ካሎት ወደ ህክምና ማዕከል በመሄድ ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል ።
ከተረጋገጠ በኋላ የበሽታው ስፋት:-
👉 በካንሰር ዓይነት
👉 በእድሜ
👉 የእርግዝናው ቆይታ
👉 በስርጭቱ እና ወዘተ ይወሰናል።
ህክምናው
👉በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ካንሠር ቢረጋገጥ ምን ማድረግ አለባቸው?
👉እርጉዝ ካልሆኑ ሴቶች በተለየ መልኩ ፅንሡ በማይጎዳበት መልኩ ይከናወናል።
👉 የጨረር
👉 የኬሞቴራፒ እና
👉 የቀዶ ህክምና ዋናዎቹ ናቸው።
ለበለጠ መረጃ
099114444/0114711914
ሎተስ የእናቶች እና ህፃናት ህክምና ማዕከል