
21/12/2024
ላይ ሰለሚወጡ ስጋ መሰል ነገሮች #ክፍል 2
👉 ሰላም ውድ የአይኬር ቪዥን ቤተሰቦች በtiktok ገፃችን ላይ በተደጋጋሚ ካስተዋልነው ግብረመልስ በመነሳት ዛሬ በሁለት ክፍል ካሰናዳናቸው ፣በተለይም አይናችን ላይ ስለሚወጡ ስጋ መሰል ነገሮች የሁለተኛውን አይነት የሚያብራራ እንዲሁም እውቀት የሚያስጨብጥ አጭር ቪድዮ ለቀንላችዋል።
👉 አይናችንን በመስታወት ስናይ አይናችን ላይ ስጋ መሰል ነገር ልናስተውል እንችላለን። ከነዚህ ችግሮች ውስጥ አንዱ ቴሪጅዬም (Pterygium) ይባላል። ይህ አይነቱ የስጋ መሰል ነገር በብዛት ከአፍንጫ በኩል የሚጀምር እና እድገት ያለው ነዉ።
👉 ፈጣን እድገት የሚስተዋል ከሆነ እና ወደ አይናችን መሃከለኛው /ጥቁሩ ክፍል የሚደረስ ከሆነ እየታን ሊጋርድ ስለሚችል ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ተገቢውን መፍትሄ ማከናወን ያስፈለጋል።
👉 የዚህ ችግር ዋነኛ መንስኤዎች የምንላቸው ፣ ለተለያዩ ጨረሮች መጋለጥ፣ ለፀሃይ ብርሃን ረዝም ላለ ጊዜ መጋለጥ ፣ አዋራ በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በተለይም ሞቃት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ላይ ይህ በብዛት ይስተዋላል.
👉 ይህንን ለመከላከል በተቻለ መጠን ከሃኪምዎ ጋር በመማከር ፣ የጨረር እንዲሁም የአዋራ መከላከያ መነፅሮችን መልበስ ፍቱን መከላከያ መንገድ ነው።
👉 እጀግ የከፋ ደረጃ ላይ ከደረሰ ብቻ በሰርጀሪ ሊነሳም ይችላል። ነገር ግን ይህ ችግር ከሰርጀሪ በኃላም ቢሆንም እንክዋን ተደጋግሞ ስለሚከሰት መከላከያ መነፅሮችን መልበስ, እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን መንሣዔዎች በመከላከል አይናችንን እንጠብቅ.
👉 ሙሉ ቪድዮ በቲክቶክ ገፃችን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZGdhum91F/
👉👉👉አይኬር ቪዥን መካከለኛ የአይን ክሊኒክ
''የሰውነት መበራት አይን ናት!!!''
አድራሻ፥ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ - ክርስቲያን
ወደ 6ኪሎ ታክሲ መያዣ ራመት ኦዳ ሞል 4ተኛ ፎቅ
ስልክ 📞📱0911278339
0967373737
☎️ 0111266449