07/11/2025
"ሰላም ዶ/ር ልጄ 3 ወሩ ነው። እምብርቱ ላይ ያበጠ ነገር አለው! አንዳንዴ ይቀንሳል፣ የሆነ ጊዜ ደግሞ በጣም ይጠነክራል። የሰፈር ሰዎች ብዙ ነገር ይሉኛል (ሳንቱም አድርጊበት፣ በፕላስተር እሰሪው ...ወዘተ)። እባክህ ያንተን ምክር እፈልጋለሁ።"
(የወላጅ ጥያቄ)
👉ሰላም ጠያቂያችን ስለጥያቄው በጣም እናመሰግናለን።
👉እንደርሶ አገላለጽ ከሆነ ይህ ችግር Umbilical Hernia ይባላል!
👉ይህ ችግር በጣም የተለመደ እና በብዙ ህጻናት ላይ የሚከሰት ችግር ስለሆነ ለብዙ ወላጆች ይጠቅማል ብለን ስላሰብን ለማብራራት እንሞክራለን!
✍ጥያቄ- 1፡ የእምብርት ሄርኒያ(umbilical Hernia) ምንድን ነው?
🌡የእምብርት ሄርኒያ ማለት የሆድ እቃ ግድግዳ እምብርት ላይ የጡንቻ ክፍተት ሲኖረው የሚፈጠር ችግር ነው።
🌡በዚህ ክፍተት ማንኛውም የሆድ እቃ አካላት በተለይ ስብ እና አንጀት በክፍተቱ ሊወጣ ይችላል
🌡በዚህም ምክንያቱ እንደ እብጠት ሆኖ ይታያል።
🌡ይህ ችግር umbilical Hernia ይባላል!
✍ጥያቄ-2 : ይህ ችግር ምን ያህል የተለመደ ነው?
💊በሕፃናት ላይ በጣም የተለመደ ችግር ነው።
💊 100 አዲስ ከሚወለዱ ህጻናት ከ10-20 የሚሆኑት ሕፃናት በተለይም ያለጊዜአቸው የተወለዱ ወይም ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ይህ ችግር ይኖራቸዋል።
✍ጥያቄ-3: መንስኤው ምንድን ነው?
🌡በሆድ እቃ ግድግዳ አፈጣጠር ከአራቱም አቅጣጫ በማደግ እምብርት ላይ ይገናኛል።
🌡 ስለዚህ እድገቱን ካልጨረሰ እምብርት አካባቢ ትንሽ ቀዳዳ ወይም ክፍተት ይቀራል!
🌡ስለሆነም ህጻናት ከተወለዱ በኋላ እምብርት ላይ ሙሉ በሙሉ መዝጋት መዘጋት ካልቻለ ይህ ችግር ይከሰታል።
✍ጥያቄ- 4፡ ይህ ችግር በብዛት የሚከሰተው የትኞቹ ላይ ነው?
💊ይህ ችግር በማንኛውም ህጻናት ላይ የመከሰት እድል አለው!
💊በብዛት የሚከሰተው ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተያያዥ ችግሮች ያሉባቸው ህጻናት ላይ ነው!
🌡🌡ያለጊዜአቸው የተወለዱ ሕፃናት
🌡🌡ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሕፃናት
🌡🌡አንዳንድ ተያያዥ የአፈጣጠር ችግር ያሏቸው ሕፃናት
✍ጥያቄ-5: ይህ ችግር ያለባቸው ህጻናት ምን አይነት ምልክት ያሳያሉ?
🌡እምብርት ላይ በቆዳ የተሸፈነ ለስለስ ያለ እብጠት
🌡 ሲያለቅሱ፣ ሲያስሉ ወይም ሲወጣጠሩ የበለጠ የሚታይ ከሆነ
🌡ብዙውን ጊዜ ህመም አይሰማቸውም
🌡ብዙውን ጊዜ ዘና በሚሉበት ጊዜ እብጠቱ ተመልሶ ይቀንሳል።
✍ጥያቄ-6: ምን አይነት ችግር ሊያስከትል ይችላል?
📍አብዛኛውን ጊዜ ምንም አይነት ጉዳት የለውም።
📍 ነገር ግን አልፎ አልፎ ሄርኒያ ሊታሰር ይችላል (አንጀት ክፍተቱ ውስጥ በመግባት ሊታሰር ይችላል)።
💊ይህ ችግር መከሰቱን የሚያመላክት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች፡-
💉💉ጠንከር ያለ ህመም ያለው እብጠት
💉💉እብጠቱ ላይ ያለው ቆዳ መቅላት ወይም መጥቆር
💉💉ማስታወክ ካለው ወይም መጥባት ወይም ምግብ መውሰድ ካቆሙ
➡ ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ቢያንስ አንዱን ካሳዩ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ህክምና የሚስፈልገው ችግር ስለሆነ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል መሄድ አለባቸው!
✍ጥያቄ-7: እንዴት ይታከማል?
🌡አብዛኛውን ጊዜ እስከ 2 አመት እድሜ ድረስ በራሱ የሚዘጋ ችግር ነው።
🌡ቀበቶ ማድረግ ፣ ሳንቲም ወይም የቤት ውስጥ መድሃኒቶችን ማድረግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው
💉💉ይህን ማድረግ ቁስለት በመፍጠር ልጅዎን ሊጎዱ የሚችሉ ተግባራት ናቸው።
🌡ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች እስከሌላቸው ድረስ ተፈጥሮ በራሱ ክፍተቱ እንዲዘጋ ያደርጋል።
✍ጥያቄ-8: ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው መቼ ነው?
🌡ችግሩ ከ3-4 ዓመታት በኋላ ከቀጠለ
🌡ክፍተቱ በጣም ትልቅ ከሆነ እና በክትትል የሚቀንስ ካልሆነ
🌡ድንገተኛ ችግር ካስከተለ
🩺ስለዚህ ለቀዶ ህክምና የሚያስችል ምክንያት ከሌለው በክትትል መታየት ይቻላል!
✍ጥያቄ-9: በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን?
🌡ቦታውን ንጹህ እና ደረቅ ማድረግ
🌡በላዩ ላይ ሳንቲም ወይም ሌላ ነገር አለማድረግ
🌡ማሰር ወይም በማንኛውም ነገር መጫን አንጀት እንዲጎዳ እና እንዲቆስል አልፎ ተርፎም እንዲበሳ ስለሚያደርግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው!
👁 በዚህ ጉዳይ ወይም በሌሎች ጉዳዬች በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
👇👇👇👇👇👇
📲+251911441651
💻ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የtelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ:
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/DrSaleamlakT
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!
እናመሰግናለን
አዘጋጅ: ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Consultant Pediatric Surgeon, FCS-ECSA