26/07/2025
❇❇‼ #በህይወት ሰልፍ ውስጥ ሳለህ ልብ ልትላቸው የሚገቡ እነኚህን 19 ነጥቦች በአጽንኦት አንብቧቸው!
✅✅ #ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!
👉 ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣
👉 ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፣
👉 ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።
✅✅ #የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም!
👉 ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣
👉 መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣
👉 ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።
✅✅ #መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል!
👉 ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ?
👉 እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።
✅✅ #ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!
👉 በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
👉 ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
👉 በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
👉 ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
👉 ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣
👉 ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።
👉 ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።
✅✅ #በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!
👉 ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም።
👉 አንተንም ጊዜውይ ቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፣
👉 በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።
✅✅ #መክሊትህን ፈልግ!
👉 ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ?
👉 ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ?
👉 አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና።
👉 አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው።
👉 በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት።
👉 አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው።
👉 ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው?
👉 ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው?፣
👉 የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው?
👉 ምንድነው ???
👉 እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣
👉 ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ።
👉 በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
✅✅ #መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!"
👉 ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው።
👉 ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል።
👉 መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፣
👉 መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፣
👉 ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።
✅✅ " የሚለውን አባባል አስታውስ፣
👉 የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣
👉 መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል።
👉 ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ።
👉 ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፣ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
✅✅ #ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!
👉ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም።
👉ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
✅✅ #በማንም ላይ አትፍረድ!
👉የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም።
👉ፍ