መልካምነትThe power of positive

መልካምነትThe power of positive በመልካምነት ጀምረን በመልካምነት ለመጨረስ መሀል ላይ የሚገ?
(3)

25/05/2024
25/05/2024

Samrawit Fikru

03/05/2024

ዕይታችን
የግልም ይሁን የማህበረሰባዊ ግንኙነቶቻችን በብዙ ድልድዮች(ማህበረሰባዊ እና ግላዊ እሴቶች) የተያያዙ ናቸው። አንድ ግለሰብ ከተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ድልድዮች ሊተሳሰር ይችላል ምሳሌ - በትዳር፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በእድር፣ በብአላት ፣ እቁብ፣ በደቦ፣ በጨዋታ፣ በትምህርት ፣ በስራ፣ በስደት ወዘተ እነዚህ ሰዋች ከሰዋች የሚገናኙበት ማህበረሰባዊ ድልድዮች ናቸው። አንድ ሰው ብዙ ድልድይ ይኖረዋል ስንል ከአንዳንዶቹ ጋር በትዳር ተቀራርቧል ከሌሎቹ ጋር ደግሞ በእድር ከሌሎቹ ጋር ደግሞ ተመሳሳይ ቋንቋ በመናገር ከሌሎቹ ጋር ደግሞ በኳስ የጤና ቡድን ... ስለዚህ አንድ ሰው ብዙ ማንነት ካላቸው ሰዎች ጋር የግንኙነት ድልድይ ሊገነባ ይችላል እንደ ግለሰቡ ግንኙነት የመገንባት አቅም።
ታድያ አንዳንድ ሰዎች ስትቀርቧቸው ፊት ይነሷችሁእና ስትርቁ ምንም እንዳልተፈጠረ ምነው ጠፋሽ/ህ ይሏችሆል። ማህበረሰባዊ ትስስራችንም ውስጥም ብዙ የሚያስተሳስሩን የፍቅር ድልድዮች አሉን በግለሰቦች የጥላቻ መርዝ ስብከት ድልድዩን ይሰብሩትና ምንም እንዳላጠፉ ተመልሰው እንሸምግላችሁ እናስታርቃችሁ ይሉናል። ልክ በልጅነታችን ወሬ እንደምታመላልሰዋ ልጅ ወሬ ከዚህ እዚያ እያመላለሰች ታጣላንና መጨረሻ ላይ እያለቀሰች ልታስታርቀን ትሞክራለች። መጀመሪያ ነበር እንጅ የፍቅር ድልድዩ ይበልጥ እንዲጠነክር መስራት። እዚህ ጋር መጨመር የምፈልገው በማህበረሰባዊም ይሁን በግል ግንኙነታችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ንቃተ ህሊና ሊኖረን ይገባል ወሬኛም እንበለው ፕሮፖጋዲስት በቀላሉ ሊሸረሽረን ለማይገቡ የትስስር እሴቶች/values እና ለመልካም ግንኙነታችን ትልቁን ስእል እንመልከት። የማህበረሰብ ግንኙነት ሲጠነክር የማህበረሰብም ይሁን የሀገር እንዲሁም የግል ችግሮች ይቀረፋሉ። የሚያገናኙንን ድልድዮች እናጠንክራቸው እንጅ ስህተትን እየፈለግን አናድክማቸው።
ዕይታ/SM

26/04/2024

ኤደን ትባላለች የጤና ባለሙያ ስትሆን ከእኛ ጋር ለመስራት ማለትም ከህክምናዉ ጎን ለጎን ጤና ነክ ጉዳዮችን ለእናንት በዩቲዩብ እና ፌስቡክ ለማቅረብ ተስማምተናል! ብዙ ነገር እንደምታሳዉቃችሁ ባለ ሙሉ እምነት ነን!

20/04/2024

ዕይታችን

በህይወታችን ሶስት አይነት ሰዎች ይኖራሉ!
1ኛ ቅጠል የምንላቸው/The leaf people
እነዚህ ሰዎች ወደ ህይወታችን የሚመጡት ወቅት ጠብቀው ነው። ወላዋይ ወይም አቋም የሌላቸው ሰዎችን መጠቀሚያ ማድረግ የሚፈልጉ። የሚፈልጉን የሚደውሉልን ሲፈልጉን ብቻ ሲሆን እኛ ባስፈለጉን ጊዜ busy ናቸው። እነዚህ ሰዎችን እንዳትደገፏቸው ምክንያቱም ደካማ ስለሆኑ። ወደ እኛ የሚመጡት የፈለጉት ነገር ስላለ ነው። በአጋጣሚ ንፋስ ከመጣ ይወስዳቸዋልና በጥንቃቄ ቅረቦቸው የሚወዱን ነገሮች ሁሉ ጥሩ ስለሆኑልን ብቻ ስለሆነ። ንፋስ/ ችግር ካጋጠመን ካጠገባችን በንፋስ ፍጥነት ስለሚጠፉ አደገኛ ናቸው።

2ኛ ቅርንጫፍ የምንላቸው/ Branch people
ጠንካራ የሚባሉ ሲሆኑ ነገሮች እየከበዱ ሲመጡ ግን መቆረጣቸው/ ተንው ዘወር ማለታቸው አይቀርምና እነዚህም ጥንቃቄ ይፈልጋሉ። እስከተወሰን መንገድ አብረውን ሊጓዙ ይችላሉ ነገሮች ሲጠነክሩ ዘወር ሊሉ የሚችሉ ናቸው።

3ኛ መሰረት የጣሉ/Root people
እነዚህ ሰዎች በህይወታችን በጣም ጠቃሚ/ significant የምንላቸው ሲሆኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚቀርቡን በችግር ጊዜም አብረውን እስከመጨረሻው የሚዘልቁ ናቸው። ወቅት ቢቀያየር ስልጣን ቢሄድ ገንዘብ ና ሀብት ቢጠፋ ... እነዚህ ሰዎች አጠገባችን አሉ። እንደ አዲስ ህይወት እንዲለመልም ህይወታችንን ውሀ የሚጠጡልን ሰዎች ናቸውና እና ክብራቸው እንውደዳቸው እኛም ከጎናቸው እንሁን።
እስኪ በችግራችሁ ከጎናችሁ የነበሩ ጓደኞቻችሁን/ቤተሰብ አስትያየት መስጫው ላይ ሜንሽን አድርጓቸውና አመስግኗቸው።
መልካም ቀን
እይታ/SM

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መልካምነትThe power of positive posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to መልካምነትThe power of positive:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram