
25/07/2024
የጨጓራ ህመም(Dyspepsia) ምንድነው?
በአለም ላይ በአማካይ እስከ 20 ፐርሰንት የሚሆኑ ሰዎች የጨጓራ ህመም ይሰማቸዋል፡፡የጨጓራ ህመም በዋናነት በ ሁለት ይከፈላል፡፡እነዚህም፡-
1.በተለያዩ የታወቁ ምክንያቶች(Organic causes) የሚከሰት የጨጓራ ህመም
ለምሳሌ ኤች ፓይሎሪ በሚባል ባክቴሪያ ፣ በመድኃኒቶች (ibuprofen,diclofenac፣ potasium chloride tablets,ferous sulphate እና ሌሎችም መድኃኒቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡
2.የታወቀ መንስኤ የሌለው(functional dyspepsia)
ከ70 እስከ 80 ፐርሰንት የሚሆነው የጨጓራ ምልክት ይሄኛው ነው፡፡
የጨጓራ ህመም ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
የጨጓራ ህመም የተለያዩ ምልክቶች ሲኖሩት ዋና ዋናዎቹ፡-ምግብ ሲበሉ ቶሎ መጥገብ፣ከእምብርት ከፍ ብሎ ያለ የሆድ ክፍል ህመም እና ማቃጠል፣ማስታወክ ወይም ማቅለሽለሽ፣ሆድ መንፋት እና ምግብ ያለመፈጨት ስሜት ናቸው፡፡
የጨጓራ ህመም አሳሳቢ ነገሮችን በቀጣይ እናቀርባለን።
ዶ/ር ቀረብህ ሞላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት)
ሕክምናውን በጌራ የቤት ለቤት ሕክምና ወይም በጌራ የሐኪሞች ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ:- ፒያሳ እሪበከንቱ ከኢትዮሴራሚክስ አጠገብ EMA ታወር 3ኛ ፎቅ
ስልክ:- +251988151617
Telegram ፦ t.me/gerahealthcare
Facebook ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=61554889813307
Whatsapp፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaDlkkDKwqSXvVNfxR3
Website ፦ www.gerahealthcare.com