Love kasu

Love kasu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Love kasu, AIDS Resource Center, Ethiopia, Addis Ababa.

29/01/2024
29/01/2024

ከኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የተላለፈ መልዕክት

አገራችን “ኢትዮጵያ ከአባቶቻችንን የተረከብናት ብቻ ሳትሆን ከመጪው ትውልድ የተዋስናት ጭምር እንደሆነች” እንገነዘባለን፡፡ ከዚህ አመክንዮ በመነሳት ሁሉም ዜጋ ያለ አድልዎ ፈጣን እና ፍትሀዊ የሆነ የመንግስት አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለውም ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ለዚህም የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር በመሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች፣ በግንባታ ፍቃድ፣ በንግድ፣ በሲቪል ነዋሪዎች ምዝገባ እና በሌሎች ወሳኝ በሆኑ ሴክተሮች ላይ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማዘመን እና ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በመመደብ ለሁሉም ነዋሪዎች ቀልጣፋ እና ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡

በጀመርናቸው የሪፎርም ስራዎች ፋይሎችን በመስረቅ፣ፎርጂድ ፋይሎችን ከነባር ፋይሎች ጋራ በመቀላቀል፣ ፋይሎችን በመሰወር እና በሌሎች መንገዶች ይፈፀሙ የነበሩ የመሬት ምዝበራዎችን ከማስቀረት ጀምሮ ሌሎች በርካታ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለናል፡፡ አስተዳደሩ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከሚያከናውናቸው ተግባራት ባሻገር ህብረተሰባችንን እየፈተነ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ችግር ለመቀነስ የእሁድ ገበያዎችን ከማስፋት ጀምሮ በክ/ከተማችን ትልቅ የገበያ ማዕከል ተገንብቶ አገልግሎት ለመሰጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል ፡፡ እንደ ክ/ከተማ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሠው ተኮር ተግባራት እየተከናወኑም ይገኛሉ፡፡

መንግስት ለውጥ ለማምጣት በቁርጠኝነት እየሠራ ቢሆንም የህብረተሰቡ የነቃ እና የተደራጀ ተሳትፎ ካልታከለበት የእኛ ጥረት ብቻውን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ በመሆኑም የክ/ከተማችን ነዋሪዎች መንግስት ዘመናዊ አሰራሮችን በመዘርጋት ፈጣን እና ፍትሀዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ የሚታዩ ችግሮችን ከማረም ጀምሮ ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን እና ሌብነትን በመታገል ረገድ የበኩለቹህን ሚና እንድትወጡ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡

በአገር ጉዳይ ሁሉም ይመለከተዋል፤ ሁሉም አሻራውን የማስቀመጥ ሀላፊነትም አለበት!!

Address

Ethiopia
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Love kasu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram