Habesha Motivational place

Habesha Motivational place full Medical therapy ��
(12)

የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ቅጠል የጤና ጠቀሜታዎች :-✧ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቀንሳል ✧ የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል✧ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት መጠን ያስተካክላል✧ አስ...
26/09/2025

የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ቅጠል የጤና ጠቀሜታዎች :-

✧ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቀንሳል

✧ የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል

✧ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት መጠን ያስተካክላል

✧ አስም እንዳይባባስ ያደርጋል

✧ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሰዎች የሰውነት ክብደት መጠን ያስተካክላል ነገር ግን የመከላከል አቅምን አያስተካክልም

✧ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ላለባቸው ጠቃሚ ነው

✧ በማረጥ ምክንያት የሚመጡ ድንገተኛ የሙቀት ስሜት እና እንቅልፍ የማጣት ችግርን ጤናማ ያደርጋል

✧ የደም ማነስ ላለባቸው ተመራጭ ነው

✧ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች

ነፍሰ ጡር ሴት እና የሚያጠቡ እናቶች ባይጠቀሙት ይመከራል

🏋️🏋️‍♀️🏋️‍♂️ በአጭር ጊዜ  ክብደት መጨመር እና ቅርፆን ማስተካከል ይፈልጋሉ❓ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ ከ 5 -10 ኪግ ክብደት መጨመር የሚያስችል🔴ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳ...
24/09/2025

🏋️🏋️‍♀️🏋️‍♂️ በአጭር ጊዜ ክብደት መጨመር እና ቅርፆን ማስተካከል ይፈልጋሉ❓
ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ ከ 5 -10 ኪግ ክብደት መጨመር የሚያስችል
🔴ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤ ለቀጭን ሰዎች የሚመከር
🔴ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን
🤙 ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ያሉበት እናደርሳለን
🤙 ክፉለሀገር ላላችሁ በፈጣን እንልካለን

ለብ ያለ ውሃ በባዶ ሆድ መጠጣት ጥቅሞቹ```````````````````````````````````````"ሙቅ ውሃ በተፈጥሮ የተዘጋጀ የቤት ውስጥ ህክምና መስጫ ነው ይሉታል"ጃፓናውያን ማለዳ እ...
24/09/2025

ለብ ያለ ውሃ በባዶ ሆድ መጠጣት ጥቅሞቹ
```````````````````````````````````````
"ሙቅ ውሃ በተፈጥሮ የተዘጋጀ የቤት ውስጥ ህክምና መስጫ ነው ይሉታል"
ጃፓናውያን ማለዳ እንደተነሱ ለብ ያለ ውሃን የመጠጣት ልምድ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን፥ ይህም እጅግ በርካታ ህመሞችን ለማዳን እና ለመከላከል እንደሚያስችልም ነው በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ማረጋገጥ የተቻለው።

ለብ ያለ ውሃን መጠጣት ለረዥም ጊዜ ታዋቂ የሆኑ በሽታዎችንና ዘመን አመጣሽ በሽታዎችን ሳይቀር ለማዳንም ሆነ ለመከላከል ያስችላል ተብሏል በጥናቱ። ለአብነትም ፣ ለጨጓራ ህመም፣ ለብሮንካይትስ፣ ለኩላሊት ለስኳር ህመም፣ ለአስም፣ ለሳምባ ነቀርሳ፣ ለወር አበባ መዛባት ለምግብ አለመስማማት፣ ለደም ግፊት፣ ለቁርጠት፣ ለካንሰር፣ ለራስ ምታት፣ ፈጣን የልብ ምትን ለማስተካከል፣ ለድርቀት ፣ ማጅራት ገትር በሽታን ለመከላከል፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ ለጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ህመሞች እና ለሌሎችም ፍቱን ነው።

አወሳሰድ፦
• ግማሸ ሊትር ለብ ያለ ውሃን ከመኝታችን ከተነሳነ በኋላ መውሰድ ፤ ከዚያም ለ45 ደቂቃ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ።
• ቁርስ ከተመገብን በኋላም ለቀጣይ ሁለት ሰዓታት ሌላ ተጨማሪ ምግብ አለመውሰድ ።
• በዕድሜ የገፉ ሰዎች የቻሉትን ያህል ውሃ እንዲጠጡ ሲመከር፥ ሌሎች ግን እስከ አራት ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃን እንዲጠጡ ነው የሚመከረው።
• የተሻለ ውጤት ለማግኘትም ይህንኑ በየቀኑ ከ20 ቀናት እስከ አንድ ወር ድረስ ማድረግ ይገባል።
• በተመሳሳይ ቀዝቃዛ ውሃን ከምግብ በኋላ ከመውሰድ ይልቅ ለብ ያለ ውሃን መጠቀሙ ተመራጭ ነው።
• ቀዝቃዛ ውሃ ከምግብ በኋላ በሚወሰደበት ወቅት ቅዝቃዜው የወሰድነው ምግብ ቅባት ያለው ከሆነ እንዲረጋ ያደርጋል።
• ይህ የረጋ ምግብ በሰውነት ከሚመነጩ አሲዶች እና ኢንዛይሞች ጋር ሲገናኝም ካንሰርን ሊያስከትል ሁሉ ይችላል።
• በመሆኑም ከምግብ በኋላ ለብ ያለ ውሃ ፣እንደ ሻይ ያሉ ትኩስ መጠጦች አልያም ሾርባ መውሰድ ይመረጣል።
• ለብ ያለ ውሃ መጠጣት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለውም ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል። ሊሰመርበት የሚገባው ግን መረጃውን ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ

15 የሙዝ የጤና ጥቅሞች ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንዱ ሲሆን በውስጡም በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም፣ ፓታሲየም፣ አይረን፣ ዚንክ፣ አይወዲን እና ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ...
22/09/2025

15 የሙዝ የጤና ጥቅሞች

ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንዱ ሲሆን በውስጡም በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም፣ ፓታሲየም፣ አይረን፣ ዚንክ፣ አይወዲን እና ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ኢ፣ ኤፍን ይዟል። ሙዝ ለምግብነት በጣም ተመራጭ ነገር ሲሆን ሙዝን ከመብላት በተጨማሪ በጣም በርከት ያሉ ሌሎች ጥቅሞች እናገኛለን።

እነሱም እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

1. ጥርስን ያነጣል!!

ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል።

2.በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!!

ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል።

3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!!

ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው።

4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!!

ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው።

5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!!

ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ።

6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!!

የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው።

7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!!

በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ።

8. ክንታሮትን ያድናል!!

ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው።ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል።

9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!!

ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል።

10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!!

ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ።

11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!!

የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት።

12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!!

ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ።

13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!!

በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል።

14. ውሀን ያጣራል!!

የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው።

15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል።

በቀጣይ እንድናቀርብ የሚፈልጉትን የጤና መረጃ በአስተያየት መስጫ ላይ ያስቀምጡልን !!

ቀይ ሽንኩርት ለቤት ውስጥ ሕክምና ወደር ያልተገኘለት መድኃኒት☞14 ነጥቦች 1. ከጉንፋን ለመላቀቅ፡-  ግማሽ ፍንካች በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ላይ በመሃል በመሀሉ አስነተኛ ስኳር ነስንሰው...
21/09/2025

ቀይ ሽንኩርት ለቤት ውስጥ ሕክምና ወደር ያልተገኘለት መድኃኒት☞14 ነጥቦች

1. ከጉንፋን ለመላቀቅ፡- ግማሽ ፍንካች በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ላይ በመሃል በመሀሉ አስነተኛ ስኳር ነስንሰው በመሸፈን ለሰዓት ያህል ሸፍኖ በማስቀመጥ በቀን ሁለቴ ቢመገቡ ጉንፋንን በቶሎ ይሰናበታሉ፡፡

2. የፀጉር መነቀልን ለመከላከል፡- የተወሰነ ሽንኩርት ውሃ ውስጥ ጨምረው ያፍሉትና ከሻምፖ በፊት ደጋግመው ይታጠቡበት ውጤቱን በፍጥነት ያዩታል፡፡

3. የሕፃን ሆድ ቁርጥ ለማስታገስ፡- ህፃናት በሆድ ቁርጠት ሲቸገሩ አንድ ፍንካች ሽንኩር በውሃ አፍልታችሁ በየሰዓቱ በትሰጧቸው ከስቃያቸው ፋታ ያገኛሉ፡፡

4. የነፍሳት ንክሻ ሕመምንና እብጠትን ለመቀነስ፡- በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ሕመም በሚሰማውና በአበጠው ቦታ ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ሸፍኖ መያዝ፡፡

5. ለጆሮ ኢንፌክሽን፡- በስሱ የተሸነሸነ ሽንኩርት በአነስተኛ ጨርቅ ተቋጥሮ ሕመሙ እስኪጠፋ ድረስ በታመመው ጆሮ ላይ መወተፍ ትልቅ መፍትሔ ይሆናል፡፡

6. ደም ለማቆም፡- ድንገት ጣቶን የሆነ ነገር ቢቆርጦት ወይም ቢወጋዎት የሽንኩርት ልጣጭ ቢጠመጥሙበት ወይም በስሱ የተከተፈ ሽንኩርት ቢይዙበት በፍጥነት ደሞ ከመፍሰስ እንዲቆም ያደርጋል፡፡

7. የአካባቢዎን አየር ያጸዳል፡- ተልጦ የተከተፈ ሽንኩርት በቤት ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ቢያስቀምጡ ባክቴሪያና ቫይረሶችን በመምጠጥ ቤቶን ያፀዳል፡፡

8. በፀሐይ ወይም በእሳት የተቃጠለን ቆዳን ያክማል፡-በአነስተኛ የተላጠ ሽንኩርት በፀሐይ ወይም በእሳት የተቃጠለን ቆዳ ቢያሹት ከኢንፌክሽን ይጠብቆታል፡፡ ይህም ቆዳዎ እንዲያገግም ከማድረጉ ባሻገር እንዳይቀላ ያደርገዋል፡፡

9. ትኩሳትን ያስወግዳል፡፡ የተላጠና በቀጭኑ የተከተፈ ሽንኩርት ከኮኮናት ዘይት ጋር አድርገው የውስጠኛው እግሮን ካሹት በኃላ ሽንኩርቱን እዚያው በመተው በላስቲክ ጠቅልለው ካልሲ አድርገው ቢተኙ ትኩሳቱ ለሊቱን ጠፍቶ ያድራል፡፡

10. ከአፍንጫ የሚወጣ ደምን ለማቆም፡- የሚደማ አፍንጫን ለማቆም የተከተፈ ሽንኩርት በሚደማው አፍንጫ ውስጥ ለተወሰነ ደቂቃ ቢያስገቡ ደሙ ይቆማል፡፡

11. የእንቅልፍ ማጣት ችግርን ያቃልላል፡- ከመተኛትዎ በፊት በትላልቁ የተከተፈ ሽንኩርት በጨርቅ አስረው ወይም እንዲሁ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሽታውን ቢምጉት ከዚያን እንቅልፎን በቀላሉ ያመጣዋል፡፡

12. የወባ ትንኝን ከቤቶ ያባርራል፡- የተላጠውን ሽንኩርት በሚተኙበት ቦታ ላይ በሳህን አድርገው ያኑሩት ወይም የተከተፈ ሽንኩረቱን የሚጋለጠውን የሰውነቶን ክፍል ይሹበት የወባ ትንኟ ከቤቶ ወጥታ ትሄዳለች፡፡

13. የጉሮሮ ሕመምን ያስውግዳል፡፡ የተፈጨ ሽንኩርት ውሃውን አነስተኛ ማር ጨምረውበት በተደጋጋሚ ቢወስዱ የጉሮሮ ቁስልን ይፈውሳል፡፡

14. በቆዳዎ ላይ የሚገኝ ጥቁር ነጥቦችን ያስወግዳል፡- ከዕድሜ መግፋትና በሌሎች ምክንያት በቆዳዎ ላይ የሚወጡ ጥቁር ነጥቦችን በቀን ሁለት ጊዜ በተከተፈ ሽንኩርት ያለማሳለስ ቢያሹት ውጤቱን በፍጥነት ያገኙታል።

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ይተባበሩ!

በነጭ ሽንኩርት ሊታከሙ የሚችሉ 30 ህመሞች❶ እንቅልፍ ማጣት ፣ ማይግሬንበየቀኑ ጥቂት ነጭ ሽንኩርት መመገብ ከእነዚህ በሽታዎች ሁሉ ይጠብቅዎታል። ደምን በማጥራት ከብዙ መርዞች ያጸዳል። ይህ...
20/09/2025

በነጭ ሽንኩርት ሊታከሙ የሚችሉ 30 ህመሞች

❶ እንቅልፍ ማጣት ፣ ማይግሬን
በየቀኑ ጥቂት ነጭ ሽንኩርት መመገብ ከእነዚህ በሽታዎች ሁሉ ይጠብቅዎታል። ደምን በማጥራት ከብዙ መርዞች ያጸዳል። ይህንን ይሞክሩ እና ውጤቱ አያሳዝዎትም፤ ምክንያቱም ያለ መድሃኒት የዕለት ተዕለት ጤና ነው።

❷ አስካሪስ (የሆድ ትል)
ሁለት የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት በ6 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ውስጥ ይጨምሩ። ለ12 ሰዓታት ያህል ይዘፍዝፉት። ከዚያም አጥልለው ይጠጡ።

❸ አስቴኒያ (ድካም)

በአከርካሪ አጥንት ላይ የሚደረግ ማሳጅ ውጤታማ ህክምና ነው። ግማሽ ጠርሙስ በነጭ ሽንኩርት እና በኮኮናት ጭማቂ ሞልተው ለሁለት ቀናት ያቆዩት። በቀን ሁለት ጊዜ ትንሽ ብርጭቆ ይጠጡ።

የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ + የሎሚ ጭማቂ + የኮኮናት ጭማቂ ቅልቅል ይጠጡ።

❹ ቃጠሎ
አንድ የሾርባ ማንኪያ የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት ወይም የሺአ ቅቤ ጋር ይቀላቅሉ። ውህዱን በደንብ ይምቱት። የተጎዳውን ቦታ በቀስታ በመንካት ይተግብሩ።

በየቀኑ ቡና ሲጠጡ በሰውነትዎ ላይ ምን ይከሰታል? ☕ጠዋት ቡና ሳይጠጡ መንቀሳቀስ ይከብድዎታል? ብቻዎን አይደሉም! ቡና ከጣዕሙ ባሻገር ለሰውነትዎ የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉ፦✅ ዋና ጥቅሞች:የበ...
19/09/2025

በየቀኑ ቡና ሲጠጡ በሰውነትዎ ላይ ምን ይከሰታል? ☕

ጠዋት ቡና ሳይጠጡ መንቀሳቀስ ይከብድዎታል? ብቻዎን አይደሉም! ቡና ከጣዕሙ ባሻገር ለሰውነትዎ የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉ፦

✅ ዋና ጥቅሞች:

የበለጠ ጉልበት – ካፌይን የአዕምሮን ንቃት ይጨምራል። 💪

የሆድ ዕቃ እንቅስቃሴ – የአንጀት እንቅስቃሴን ያነቃቃል። 🚽

ስሜት ማሻሻል – ዶፓሚን በመጨመር ደስታን ይፈጥራል። 😊

የአልዛይመር በሽታ ስጋት መቀነስ – የአዕምሮ ጤናን ሊደግፍ ይችላል። 🧠

የልብ ጤና – የልብና የደም ዝውውር ስጋትን ሊቀንስ ይችላል። ❤️

⚠️ ጥንቃቄ ያስፈልጋል!

ከመጠን በላይ መጠጣት ጭንቀት፣ የእንቅልፍ ችግር ወይም ጥገኝነት/ሱሰኝነትን

እርስዎ የቡና አፍቃሪ ነዎት? ምን አይነት ቡና ነው የሚመገቡት? ኮሜንት ላይ ያጋሩን! 👇

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habesha Motivational place posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Habesha Motivational place:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram