09/04/2024
🧠የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በእርግዝና ወቅት (Heptitis B in pregnancy)
👉 የሄፕታይተስ B ቫይረስ ምንድነው ?
ሄፕታይተስ B ቫይረስ ጉበትን ሊያጠቃ የሚችል የሄፕታይተስ ቫይረስ አይነት ሲሆን፤ ብዙውን ጊዜ ሰዎች እንደያዙት ሳያውቁት ቆይተው በመጨረሻም በሽታው እራሱን መግለፅ ሲጀምር የሚያወቁት ሲሆን፤ ህመሙም
⁃ ቀላል አይነት - ለብዙ ዘመን በሰውነት ውስጥ ምልክት ሳያሳይ የሚቆይ አይነት ወይንም ደግሞ
⁃ ከባድ ከሆነ - አይን እና ቆዳ ቢጫ ማድረግ፣ ሽንት መጥቆር እና ሰገራ ነጣ ማለት፣ የሆድ መጠን መጨመር፣ ኪሎ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ በቀላሉ ከተለያዩ ቦታዎች መድማት፣ መገጣጠሚያዎች መድከም፣ ማቅለሽለሽ ተውከት ፣ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊከሰቱ ይችላሉ።
⁃ ቫይረሱ በደም ውስጥ እንዳለ አወቆ ካልታከሙት ወይም በየጊዜው ካልተከታተሉት ወደ ጉበት ቁስለት ፣ ለጉበት ካንሰር እንዲሁም ለሞት ሊዳርግ ይችላል
👉 HBV እንዴት ሊተላለፍ ይችላል ?
በደም፣ በዘር ፈሳሽ ፣ ወይንም በሌሎች የሰውነት ፈሳሾች ንክኪ ፣ እንዲሁም ከእናት ወደ ልጅ በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜ እና ከወሊድ በውሀላ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
👉 ሄፕታይተስ B ቫይረስ እና እርግዝና
በእርግዝና ጊዜ ሄፕታይተስ B ቫይረስ በመጀመሪያዎቹ ወራት ወደፅንሱ የመተላለፍ አቅሙ እስከ 10% ሲሆን ወደመጨረሻ ወራት ደግሞ እስከ 60% ሊደረስ ይችላል።
👉 Hepatitis B ቫይረስ በሽታን እንዴት እንከላከል ?
⁃ ህፃኑ ከተወለደ በ12 ሰዓት ውስጥ ክትባት(HBV vaccine) እና አንድ ተጨማሪ መድሀኒት(hepatitis b Immunoglobulin) መውሰድ ያስፈልገዋል።
⁃ የእናቲቱ የቤተሰብ አካላት እና ቤቷ የሚኖሩ በሙላ በተለይ ከዚህ በፊት ቫይረሱ በሰውነታቸው ይኑር አይኑር የማያውቁ በጤና ተቋም ሄደው እራሳቸውን ተመርምረው ካወቁ በውሀላ ነፃ ከሆኑ ክትባቱን መውሰድ ይኖርባቸዋል።
👉 የክትባት አሰጣጥ
⁃በጠቅላላ 3ት ክትባት መወሰድ ይኖርበታል
⁃1ኛው ክትባት - በደሞ ውስጥ ቫይረሱ እንደሌለ ሲረጋገጥ
⁃2ኛው ደግሞ - 1ኛውን ከወሰዱ ከ 1 ወር በውሀላ
⁃3ኛው ክትባት - ከ 2ኛው ከ 5ወር በውሀላ
በአለም የጤና ድርጅት(WHO) መሰረት ሙሉውን ክትባት መውሰድ ቫይረሱን ከ 98-100% መከላከል እንድንችል ያደርገናል።
አንዲት እናት እርግዝና ላይ ሆና ወይም ከወለደች በውሀላ እያጠባች ሳለች ክትባቱን መውሰድ ትችላለች ምንም ችግር የለውም።
HBV በደሟ ውስጥ ያለች እናት መድሀኒቱን የምትጀምረው በደሟ ውስጥ ያለው የሄኘታይተስ b መጠን ከተለካ በውሀላ እና መድሀኒት መጀመር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው። በተጨማሪም የጉበት መድከም ወይንም ስራ ማቆም (hepatic failure) እና በሽታው ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ከሆነ ነው።
👉 ጡት ማጥባት
ህፃኑ 1ኛውን ክትባት (HBV Vaccine 1st does ) እና ሄፕታይተስ b ኢሚኖግሎቡሊን (HB Immunoglobulin) ከወሰደ እናትየው ተገቢውን ጡት ማጥባት ልትቀጥል ትችላለች።
በኛ ሀገር የክትባት ህግ መሰረት ከ1ኛው ክትባት ቀጥሎ ለህፃኑ የሚሰጡት የHBV(hepatitis b) ክትባቶች ከሌሎች 4 ክትባቶች (diphtheria, pertussis, Tetanus, H.influenza type b) ጋር pentavalent በመሆን ይሰጣል። በዚህም መሰረት ቀጣዮቹ ክትባቶች፡-
💥 2ኛው ክትባት - በ6 ሳምንት ላይ
💥 3ኛው ክትባት - በ10 ሳምንት ላይ
💥 4ኛው ክትባት - በ14 ሳምንት ላይ ይሰጣል ።