08/05/2025
Caution ⚠️ ⚠️ ⚠️
በአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ የሚመረቱ አትክልቶች የተመረዙ ናቸው ተባለ
በአዲስ አበባ ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ አትክልቶች ከወንዝ ዳርቻና ከፋብሪካ በሚወጡ መርዛማ ኬሚካሎች (ፅዳጆች) የተመረዙ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ይህንን ያስታወቀው ማክሰኞ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የቅንጅት ሥራዎችን ዕቅድ አፈጻጸም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት ወቅት ነው፡፡
ከ16 ተቋማት ጋር ላለፉት ዘጠኝ ወራት የተሠሩ ሥራዎችና የታዩ ክፍተቶችን የሚያሳይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
የአየር ብክለት በከተማዋ ከፍተኛ ሥጋት መደቀኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡
አቶ አሰግደው እንደተናገሩት በአዲስ አበባ በወንዞች ዳርቻ የሚበቅሉ አትክልቶች በሙሉ የተመረዙ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
(ሪፖርተር)