
15/05/2025
ከ 1 አመት በታች ላለ ልጅ ማር አይሰጥም!!
ለምን ማር አይፈቀድም?
ብዙ ባህሎች ላይ ማር ለሕጻናት "ጤናማ" ተብሎ ይታሰባል፣ ነገር ግን ሳይንሳዊ ምርመራዎች ከአንድ ዓመት በታች እንደማይፈቀድ ያረጋግጣሉ።
•ማር ውስጥ ያለ ባክቴሪያ (*Clostridium botulinum*) ከአንድ ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት አሳሳቢ የሆነ በሽታ ሊያስከትል ይችላል። ይህ ባክቴሪያ ቦቱሊኒዝም የሚባል በሽታን ያመጣል።
•ከ1 አመት በታች ያሉ ሕፃናት ሰውነታቸው ይህን ቶክሲን መከለከል ስለማይችሉ ፓራሊስስ ሊያመጣባቸው ይችላል።
ከአንድ ዓመት በላይ? ✅
ከ1 ዓመት በኋላ፣ ሰውነታቸው ይህን ቶክሲን መከለከል ስለሚችሉ በትንሽ መጠን ማስጀመር ይችላል።
ይህንን መረጃ ሌሎች ወላጆች እንዲያውቁ ያጋሩ!
ልጆቻችን በጤና እንዲያድጉ በጋራ እንስራ!
Join - https://t.me/currrrrrr99