Ethiopian Health and Nutrition Research Institute Library

Ethiopian Health and Nutrition Research Institute Library Yea, Library the resource center its symmetry Open door of destiny

11/04/2024
27/11/2023

10
**********************************************************
1. /መቀየር!
የመጀመሪያው የኩላሊት በሽታ ምልክት የሽንት ሥርዓት መለወጥ ነው፡፡ መለወጥ ስንል የሽንት መጠን እና ሽንትዎን የሚሸኑበት የጊዜ ልዩነት ነው።
✔ ሌሎች ለውጦች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
• ሌሊት ሽንት ለመሽናት ደጋግመው መነሳት
• ለመሽናት መቸኮል
• ከተለመደው ጠቆር ያለ ሽንት
• አረፋ ያለው ሽንት
• ደም የተቀላቀለበት ሽንት
• ሲሸኑ መቸገር/በጣም መግፋት ለመሽናት
• በሚሸኑበት ጊዜ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት ናቸው።
2. !
ተረፈ ምርቶችንና ትርፍ ፈሳሾችን ከሰውነታችን ማስወገድ የኩላሊት ስራ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ሲሳነው ግን የትርፍ ፈሳሽና ውሃ መከማቸት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ እነዚህ እብጠቶች በእጅ፣ እግር፣ ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያ፣ ፊት እና አይን አካባቢ ይፈጠራሉ፡፡
3. !
ኩላሊት ተግባሯን በትክክል መወጣት በሚያቅታት ወቅት አብዛኛውን ጊዜ የመዛል ስሜት ይሰማናል፡፡ ይደክምዎታል ወይም በአጠቃላይ ባላወቁት ምክንያት ሃይል/ጉልበት ያጥርዎታል፡፡
የዚህ ምልክት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች የደም ማነስና በሰውነት ውስጥ የተረፈ ምርቶች/ቆሻሻዎች መከማቸት ነው፡፡
4. !
በኩላሊት በሽታ ምክንያት የደም ማነስ የሚከሰት ከሆነ በተደጋጋሚ ያዞርዎታል የዚህም ችግር የራስ መቅለል፣ ባላንስ ማጣት ዓይነት ስሜቶች/ምልክቶች
ይታይብዎታል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የደም መነስ በሽታው ወደ አእምሮ በቂ የሆነ ኦክስጂን እንዳይደርስ ስለሚያደርግ ነው፡፡
5. !
ይህ ነው የማይባል የህመም ስሜት በጀርባዎና በሆድዎ ጎንና ጎን መሰማት የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት በትክክል ስራውን መስራት ካልቻለች የመገጣጠሚያ ህመም፣ መገተር/ ለማጠፍ መቸገርና ፈሳሽ ይስተዋላል፡፡
6. !
ድንገተኛ የሆነ የቆዳ መሰነጣጠቅ፣ ሽፍታ፣ ማቃጠል/መለብለብ እና ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ተጨማሪ የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው፡፡ ኩላሊት ተግባሩን በትክክል አለመወጣት ቆሻሻዎችና መርዛማ ነገሮች በሰውነት ውስጥ እንዲከማቹ አስተዋጽዎ ስለሚያደርግ በርከት ላሉ የቆዳ ችግሮች ያጋልጣል፡፡
7. !
የኩላሊት በሽታ የአፋችን ጣዕም ብረት ብረት እንዲለን ወይም አፋችን የአሞኒያ (የሽንት) ሽታ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ይህ የሚሆነው ደካማ የሆነ የኩላሊት ተግባር በደም ውስጥ ያለው የዩሪያ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
ዩሪያ በምራቅ በመሰባበር ወደ አሞኒያ ይቀየራል ይህም አፋችን መጥፎ የሆነ ሽንት የሚመስል ሽታ እንዲኖረው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
8. !
በኩላሊት በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ በጣም የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡ የማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ስሜት በአብዛኛው የሚኖረው ጠዋት ከእንቅልፍዎ በሚነሱበት ወቅት ነው፡፡
9. ?
ይህ በኩላሊት በሽታ ምክንያት በተፈጠረ ደም ማነስ ምልክት ነው፡፡ በማያውቁት ምክንያት የብርድ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል ምንም አየሩ ሙቀት ቢሆንም እንኳን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከማዞርና ድካም በተጨማሪ የሚበርድዎት ከሆነ በፍጥነት ህክምና ያግኙ፡፡
10. !
የትንፋሽ እጥረት የኩላሊት በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት ተግባሯን በትክክል አለመወጣቷ በሳንባ ውስጥ በዛ ያለ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል፡፡ ይህ የትንፋሽ ማጠር በኩላሊት ችግር ምክንያት በተፈጠረ የደም ማነስ ሊሆን ይችላል፡፡
መልካም ጤንነት!!
ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።

15/12/2022

ቢቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ

የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን!
2ኛተሰ 3÷16
እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን ሲፈጥር ሁሉም በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ ነው ነገር ግን የጥንት ጠላታችን የሆነው ዲያብሎስ ‘ፀላኤ ሰናይ’ የመልካም ነገር ተቃዋሚ ነውና በተንኮል ገብቶ ሰውን ከአምላኩ አለያየው ሰውም ሰላም፣ ፍቅር፣ እረፍትና ሕይወት ከሆነው አምላኩ ተለያይቷልና ባዶ ሆነ ስለሆነም ወደ ምድር ሲመጣ እርስ በርስ እየተጣላና እየተጠፋፋ መኖር ግድ ሆነበት ሰላሙን ተነጥቋልና ይህን የተመለከተው አምላካችን ያጣነውን ሰላም ይሰጠን ዘንድ ሊታረቀን መጣ በመስቀሉም ሰላምን አደረገ፡፡ ሰውን ከአምላኩ፣ ሰውን ከወገኑ ሰውን ከራሱ አለያይቶ የነበረው የጥል ግድግዳ አፈረሰ ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሰላሜን እተውላችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም አለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም" ሲል ዘለአለማዊ ምንም ነገር ሊያጠፋው የማይችል ሰላሙን አደለን፡፡ ይህ ሰላም ሁከትና መከራ ጭንቅ በሰፈነበት ዓለም ያለመናወጥ ሊያኖረን የሚችል ኃይል አለው ምክንያቱም የኛ ጌታ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም ከሚገዛው ከዲያብሎስ በላይ ነውና፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም መኖር ይከብድ ይሆናል ነገር ግን ኃይልን በሚሰጥ በክርስቶስ ሁሉ ይቻላል ቃሉም የሚያዘን ከጠላቶቻችን ጋር በፍቅር እንድንኖርና የያዝነውን ሰላም ለዓለም ማዳረስ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ግን እኛ መጀመሪያ በዚህ አዕምሮን በማያልፍ ሰላም መሞላት አለብን አለበለዚያ እኛ ሰላም ሳይኖረን ለሌላው ሰላምን ልናድል አይቻለንም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰላም በጥቂቱ
#ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ሽሽ፣ በንጹህም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል፡፡ 2ኛ ወደ ጢሞ 2፣22
#በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፡፡ የምታመሰግኑም ሁኑ፡፡ ወደ ቆላስየስ3፣15
#የእግዚአብሔር መንግስት ጽድቅና ሰላም በመንፈስም ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና፡፡ ሮሜ 14፣17
#ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና ስለመንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው፡፡ ሮሜ 8፣6
#እንግዲህ በእምት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ ሮሜ 5፣1
#ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፣ የሰላምንም መንገድ አያውቁም፡፡ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡ ሮሜ 3፣16
#ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፣ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና፡፡ ወደ ዕብ 12፣4
#ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም፡፡ ልባችሁ አይታወክ አይፍራ፡፡ ዩሐ14፣27
#የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን! 2ኛተሰ 3÷16
#ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፣ እረስ በርሳችሁ ተስማሙ፡፡ ማር 9፣50
አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት ሚድያ

Address

Arbegnoch Road
Addis Ababa
1242

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health and Nutrition Research Institute Library posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Health and Nutrition Research Institute Library:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram