14/06/2025
Every day, mothers bring life into this world.
But for some, childbirth comes with life-threatening complications, and one of the most serious is heavy bleeding.
A mother can lose over a liter of blood during delivery.
In those moments, a safe birth can depend entirely on one thing: the availability of donated blood.
In Ethiopia, postpartum hemorrhage (severe bleeding after birth) is the leading cause of maternal death, responsible for up to half of all cases, not because it can’t be treated, but because blood isn’t always available when it’s needed most.
🩸 Blood can’t be manufactured.
🩸 It comes only from kind, willing people like you.
When you give blood, you’re not just donating a unit.
You’re giving a mother the chance to live.
To hold her baby. To return home.
💡 On this World Blood Donor Day, we honor donors.
And we call on everyone who can: Give blood. Give life. Give hope.
በየቀኑ እናቶች አዲስ ህይወት ወደዚህች ዓለም ያመጣሉ። ነገር ግን ለአንዳንዶች ወሊድ ለህይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ይዞ ይመጣል፤ ከእነዚህም ውስጥ ዋነኛው ከባድ የደም መፍሰስ ነው።
አንዲት እናት በወሊድ ጊዜ ከግማሽ እስከ አንድ ሊትር ወይም ከዛም በላይ በላይ ደም ሊፈሳት ይችላል። በእነዚህ ወሳኝ ጊዜያት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ወሊድ ሙሉ በሙሉ በአንድ ነገር ላይ ሊመሰረት ይችላል፦ በልገሳ የተገኘ ደም መኖር።
በኢትዮጵያ ከወሊድ በኋላ የሚከሰት ከባድ የደም መፍሰስ (Postpartum Hemorrhage) ለእናቶች ሞት ዋነኛው መንስኤ ነው። ከእናቶች ሞት ውስጥ እስከ ግማሽ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፤ ይህም ችግሩ መፍትሄ ስለሌለው ሳይሆን፣ ደም በሚያስፈልግበት ወሳኝ ሰዓት ሁልጊዜ ስለማይገኝ ነው።
ደም ሲለግሱ፣ የሚሰጡት አንድ ዩኒት ደም ብቻ አይደለም።
ለአንዲት እናት በህይወት የመቆየት እድል እየሰጡ ነው።
ልጇን እንድታቅፍ ፤ ወደ ቤቷ እንድትመለስ።
💡 ዛሬ በዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን፣ የደም ለጋሾችን እናከብራለን።
እናም ደም መስጠት ለሚችል ሁሉም ሰው ጥሪ እናቀርባለን፦ ደም ይለግሱ፤ ህይወት እና ተስፋ ይስጡ።