MELA Wellness Center

MELA Wellness Center Empowering Health, Transforming Lives
Email: melawellnesscenter@gmail.com
Phone: 09 09 55 88 77
Visit our website:www.melawellness.org

21/02/2026

ሁሌ ምዝገባ ሁሌም ትምህርት አለ🙌

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል መከተል የሚያስፈልገው አመጋገብ1) የጨው አጠቃቀምን በጣም መቀነስ እና በምትኩ የምግብ ጣዕም የሚሰጡ ቅመሞችን መጠቀምለምሳሌ:- ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ፣ቀረፋ...
11/11/2025

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል መከተል የሚያስፈልገው አመጋገብ

1) የጨው አጠቃቀምን በጣም መቀነስ እና በምትኩ የምግብ ጣዕም የሚሰጡ ቅመሞችን መጠቀም
ለምሳሌ:- ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ፣ቀረፋ፣ሎሚ...

2)ቀይ ስጋ፣ጮማ፣የወተት ተዋፅዖ...የእንስሳት ተዋፅዖ ፕሮቲን እና ቅባት በጣም መቀነስ

አሳ እና እንቁላል በመጠኑ መጠቀም

3) የተቀነባበሩ የፉርኖ ውጤቶች እና የተለያዩ ማጣፈጫና ቀለም የተጨመረባቸው ምግቦች፣ስኳር፣ በዘይት የተንቸከቸኩ ፈጣን ምግቦች... አለመመገብ

በምትኩ

አትክልት፣ ፍራፍሬ ፣ ጥራጥሬ፣ ከነአሰሩ የተዘጋጁ አህሎች፣ የቅባት እህሎች...ማዘውተር

4) በፖታሽየም፣ ማግኒዚየም እና ካልሽየም የበለጸጉ ምግቦችን ይበልጥ ማዘውተር
ለምሳሌ:- አሳ፣ሙዝ፣እንቁላል(በመጠኑ)

አቮካዶ፣ አረንጓዴ አትክልቶች፣ ስራስሮች፣ ጥራጥሬዎች፣የቅባት እህሎች ...

5) የአልኮልና የካፊን መጠጦችን አለመጠቀም

6)ከአመጋገብ በተጨማሪ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ ኸርባሎችን በመጠኑ መጠቀም

7)ከአመጋገብ በተጨማሪ በቀን ቢያንስ ለ30ደቂቃ የአካል እንቅሰቃሴ ማድረግ

መራመድ፣ሳይክል መንዳት፣ ...

21/10/2025

🤔የአካል እንቅስቃሴ ለእነዚህ በሽታዎች ምን ያደርጋል?

ከዋና ዋና የበሽታ መከላከያ መንገዶች መካከል የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ አንደኛው ነው። የበሽታዎችን አስከፊ ውጤት ለመቆጣጠር እና ለመቀነስም ይረዳል።

🥏1. የልብ እና የደም ሥር በሽታዎች

- የልብ እና የአተነፋፈስ ስርዓትን በማስተካከል አጠቃላይ የልብ እና አተነፋፈስ ስርዓቱ ያስተካክላል ።
- ደም ግፊት እና ኮሌስትሮልን ይቆጣጠራል።
- የልብን ጉዳት ይከላከላል።
- የደም ስርጭትን ያሻሽላል።

🥏2. የሁለተኛ ዓይነት የስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes)

- የሰውነት ኢንሱሊን አጠቃቀምን ያሻሽላል ።
- የደም ስኳርን በመቆጣጠር ይረዳል ።
- ስኳር በሽታን ይከላከላል።

🥏3. ውፍረት (Obesity)
- ካሎሪ ያቃጥላል።
- የሰውነት የስብ መጠንን ለመቀነስ እና ጤናማ ክብደት ለመጠበቅ ይረዳል።

🥏4. የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች (e.g., Asthma, COPD)

- የመተንፈሻ ችሎታን ያሻሽላል።
- የመተንፈሻ ጡንቻዎችን ያበረታል።
- ጥሩ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።

🥏5. የአእምሮ ጤና (Mental Health)

እንቅስቃሴ በስራ እና ሀሳብ የደከመ አዕምሮን የማደስ አቅም አለው ። የጭንቀት ሆርሞንን (Cortisol) በመቀነስ እንዲሁም ጥሩ እንዲሰማን የሚያደርግ ሆርሞን (Endorphin) በመጨመር የአዕምሮን ጤና ይጠብቃል ።

💥Diabetes Mellitus💥
13/10/2025

💥Diabetes Mellitus💥

💥💥💥የምስራች መላ የጤናማ ኑሮ ማማከርና ማሰልጠኛ ማዕከል የ*Pulmonary Function Test እና*ECG(Electro Cardiography) ምርመራ እጅግ በታላቅ ቅናሽ መስጠት መጀመሩን...
11/10/2025

💥💥💥የምስራች መላ የጤናማ ኑሮ ማማከርና ማሰልጠኛ ማዕከል የ
*Pulmonary Function Test እና
*ECG(Electro Cardiography) ምርመራ እጅግ በታላቅ ቅናሽ መስጠት መጀመሩን ስንነግርዎ በደስታ ነው።💥💥💥

10/10/2025

የስኳር ሱስ

ልክ እንደ አልኮል፣ መጠጥ፣ ሲጋራ ፣ ካፊን(ቡና)... ሱሶች ስኳርና የተለያዩ አርቴፊሻል ማጣፈጫ የተጨመረባቸው ምግቦች እና ፈጣን የተጠበሱ ምግቦች ሱስ እንደሚሆኑ እና በዚህ ምክንያት ከፍተኛ የረሀብ ስሜት፣ የራስ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣የድካምና የህመም ስሜት፣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ ... የመሳሰሉ የህመም ስሜቶች እንደሚያስከትሉ ጥናቶች ያመላክታሉ ።
ከዚያም እነዚህን ምግቦች በተደጋጋሚ የመብላት ፍላጎትን ይጨምራል። ሲበሉም ለጊዜው የረሀብ እና የህመም ስሜቱ ይቀንሳል።
🍔🧇🍟🍕🧈🍡🧁🍰🍩🍪🍿🍫
ነገር ግን እነዚህ ምግቦች ፋይበር እና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ስለሌላቸው ከተመገቡ 2-3 ሰዓት ባልሞላ እንደገና የረሀብ እና የህመም ስሜቱ ይጀምራል። ስለዚህ ሰውነት ከሚያስፈልገው የካሎሪ መጠን በላይ ብዙ መመገብን ያስከትላል ።
ይህን አላስፈላጊ ተጨማሪ የምግብ መጠን ደግሞ ሰውነት ተጠቅሞ ስለማይጨርሰውና የነዚህን አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች መርዝ ሰውነታችን በቀላሉ ማስወገድ ስለማይችል በስብ መልክ ያስቀምጠዋል።

ይህም ከመጠን ላለፈ ውፍረት፣ለስኳር ህመም፣ በተለያዩ ባክቴሪያና ጀርሞች በቀላሉ መጠቃት፣ ለልብ ህመምና የደም ግፊት መጨመር፣ የጉበት ስብ መከማቸት፣ ለጥርስ ህመምና መቦርቦር፣ ለሆርሞን መዛባት፣ ለድካምና አቅም ማነስ፣ ብስጩነት፣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ የካንሰር ተጋላጭነትን መጨመር....ወዘተ ብዙ የጤና መታወክን ያስከትላል።
🥗🍲🥙🍆🥕🫑🫛🥦🥬🍍🥭🍑🍒🫐🍇🍓🥝🥒🌶🍅🫜🧄🧅
💌ስለዚህ ተፈጥሮአዊ የሆኑና ፋይበርና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ያላቸውን እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣የቅባት አህሎች፣ አረንጓዴ አትክልቶችና ተፈጥሮአዊ ጣፈጭ ያላቸውን ፍራፍሬዎችን በመመገብ ጤናችንን ከሚያውኩና ከማይጠቅሙ ምግቦች እንጠበቅ፤ መልዕክታችን ነው⚠️
ከእኛ ጋር አመጋገብዎን፣ሰውነትዎን እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤዎን ያስተካክሉ ፤ እናግዝዎታለን።
☎️፦ 09 09 55 88 77

07/10/2025

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

✅ "ሙቅ ውሃ በተፈጥሮ የተዘጋጀ የቤት ውስጥ ህክምና መስጫ ነው ይሉታል" ጃፓናውያን ማለዳ እንደተነሱ ለብ ያለ ውሃን የመጠጣት ልምድ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን፥ ይህም እጅግ በርካታ ህመሞችን ለማዳን እና ለመከላከል እንደሚያስችልም ነው በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ማረጋገጥ የተቻለው።

ለብ ያለ ውሃን መጠጣት ለረዥም ጊዜ ታዋቂ የሆኑ በሽታዎችንና ዘመን አመጣሽ በሽታዎችን ሳይቀር ለማዳንም ሆነ ለመከላከል እንደሚያስችል ጥናቶች አመላክተዋል ።

✏️ለአብነትም
🔘ለጨጓራ ህመም፣
🔘ለብሮንካይትስ፣
🔘ለኩላሊት፣
🔘ለስኳር ህመም፣
🔘ለአስም፣
🔘ለሳምባ ነቀርሳ፣
🔘ለወር አበባ መዛባት
🔘ለምግብ አለመስማማት፣
🔘ለደም ግፊት፣
🔘ለቁርጠት፣
🔘ለካንሰር፣
🔘ለራስ ምታት፣
🔘ፈጣን የልብ ምትን ለማስተካከል፣
🔘ለድርቀት ፣
🔘ማጅራት ገትር በሽታን ለመከላከል፣
🔘ከልክ ላለፈ ውፍረት፣
🔘ለጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ህመሞች እና ለሌሎችም ፍቱን ነው።

t.me/melawellnesscenter
በ 0909558877 በመደወል ያማክሩን።

24/09/2025

✅ የchia seed የጤና ጥቅሞች
የቺያ ዘሮች ጥቃቅን ናቸው ግን ደግሞ በንጥረ ነገር የተሞሉ ናቸው 🌱.
የ Chia seed ዋና የጤና ጥቅሞች እነሆ:-
1. በ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የተሞሉ ናቸው
ፋይበር, ፕሮቲን, ኦሜጋ -3, ካልሲየም, ማግኒዥየም እና antioxidants በዉስጣቸዉ ይይዛሉ::
2. የምግብ መፈጨት ሂደትን(digestive system) ይደግፋል
ከፍተኛ ፋይበር (በ 2 የሾርባ ማንኪያ ዉስጥ 10 ግራም አካባቢ) በዉስጡ ስላለው የምግብ መፈጨት ሂደትን በማስተካከል ከሆድ ድርቀት ይከላከላል::
3. የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ይረዳል
የሚሟሟው ፋይበር የግሉኮስን absorbtion በማዘግየት በደም ዉስጥ ያለዉን የስኳር መጠን ለማስተካከል ያግዛል::
4. የልብ ጤናን ይደግፋል
ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ እና ፋይበር ኮሌስትሮልን እና ትራይግላይሴራይድን ለመቀነስ ይረዳሉ::
5. ክብደትን ለማስተካከል
Chia seed በዉሃ ሲዘፈዘፍ ፈሳሹን በመምጠጥ ስለሚበዛ በቶሎ የጥጋብ ስሜት ስለሚፈጥር ብዙ መብላትን በመከላከል ክብደት መጨመርን ለመከላከል ያግዛል::
6. የአጥንት ጤና
በካልሲየም, ፎስፈረስ እና ማግኒዥየም የበለፀጉ ስለሆኑ ለአጥንትና ጥርስ ጥንካሬ አስፈላጊ ነው::
7. ኢነርጂ እና ጽናት
በታሪካዊዎቹ AZTEC እና Mayan ስልጣኔዎች ተዋጊዎቻቸዉ ጉልበት እንዲሰጣቸዉ በማሰብ chia seedን
ይመገቡ ነበር::
8. ቆዳን ከእርጅና ለመከላከል
Chia seed በዉስጡ antioxidants ስላሉት ጤናማ ቆዳን ጠብቆ ለማቆየት ያግዛል::

ከጤና ሁኔታችሁ እና ከምትወስዱት
መድኃኒት አንፃር በምን ያህል መጠን መጠቀም እንደምትችሉ ለማወቅ በዚህ ሊንክ ወይም በ 0909558877 በመደወል ያማክሩን።

MELA Wellness Centerበጣም ከ ታላቅ ቅናሽ ጋር   _CPD_ይመዝገቡ  🖌 Topic: - Integrative prevention and management of Non-communicable ...
16/09/2025

MELA Wellness Center

በጣም ከ ታላቅ ቅናሽ ጋር _CPD_ይመዝገቡ

🖌 Topic: - Integrative prevention and management of Non-communicable Diseases (NCDs)

አስደሳች ዜና ለሁሉም ጤና ባለሙያዎች

**የሙያ ፍቃዳችሁን ላላሳደሳችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ ✅

*** ልዩ የሚያደርጉን ***

👌 1ኛ ልዩ የሚያደርገን ተመጣጣኝ ዋጋ (Benefit packages)
15 CEU =400 BIRR
30 CEU=900 BIRR
45 CEU=1400 BIRR
60 CEU=1900 BIRR

👌 2ኛ ልዩ የሚያደርገን በጤና ሚኒስቴር እውቅና ያለው የ CPD ስልጠናዎች የሚቀርቡበት ማዕከል መሆኑ

For All department (ለሁሉም ዲፓርትመንት)
1. GP
2. HO
3. Nutrition/Dietician
4. Anesthesia
5. Nurse
6. Midwifery
7.Pharmacy
8. Laboratory
9. others health professional

👌 3ኛ ልዩ የሚደርገን ሁሌም ምዝገባ ሁሌም ስልጠና አለ፡፡
👌 4ኛ ካሻዎት online በምንሰጠው ስልጠና ባሉበት ሆነው የሚፈልጉትን CEU ነጥቦች እንዲያሟሉ እናግዛለን፡፡

👉Training starts: on September 02, 2025 (ነሃሴ 26፣2017 ዓ.ም)
👉 There will be special discount for those who come in group.

ለበለጠ መረጃ
📱 +251909558877
እንዲሁም
በቴሌግራም ያናግሩን
አድራሻ ፡ ቦሌ ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም ብሎክ 33 የቤት ቁጥር 004

26/08/2025

🚨 CPD Training Opportunity

We are excited to announce the launch of our Integrative Prevention & Management of NCDs Training at MELA Center for Integrative Health and Wellness.
📌 Start Date: September 2, 2025
📌 Format: Weekly sessions – Onsite & Online
📌 Accreditation: CPD-accredited by the Ethiopian Medical Association (15 CEUs per module)
🔹 Module 1: Integrative health approaches & metabolic disease pathophysiology
🔹 Module 2: In-depth learning on Diabetes Mellitus, Hypertension & Obesity
✅ For medical doctors, health officers, nurses, nutritionists, personal trainers, and other health professionals
✅ Gain evidence-based skills in prevention & integrated care of NCDs and Metabolic diseases
✅ Certificate of completion + CPD credits
📞 Register online at www.melawellness.org or call +251909558877
Join us in building stronger capacity for NCD prevention and care in Ethiopia and beyond.

Web site created using create-react-app

09/05/2025

ለጤናዎ በመላ መላ ይፈልጉለት!!
በመላ የተቀናጀ የጤና ማማከር፤ክትትል እና ስልጠና ፕሮግራም ህይወቶን ይለውጡ!
በመላ የጤና ማዕከል ጤናዎን ይጠብቁ! 🌟

የሰውነት ውፈረት ለመቀነስ እና በቦርጭ ምክንያት የሚከሰቱ በሸታዎችን ለመከላከል እና ለማስቆም ይፈልጋሉ?
የስኳር በሽታን ና ደም ግፊት ጉዳት በምግብና በአጋል ብቃት እንቅስቃሴ መከላከል እና ተጋላጭነትን ለመቀልበስ ወስነዋል?
የኮለስትሮል(Cholestrol) እና ሆርሞን(Hormon) መጠን መዛባትን ማስተካከል ያስፈልጎታል?
የሰውነት ቅርፅ በምግብና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስተካከል ያስፈልጎታል?
የሰውነት ክብደት መጨመርና የጡንቻ መዳበር ፍላጎት አሎት?
የተቀናጀ አጠቃላይ የጤናማነት ምርመራ፤ክትትል፤ምክርና ስልጠና በሃኪም፤በስነ-ምግብ ባለሙያና (Dietician) በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለሙያ (Personal trainer) አገልግሎት በአንድ ቦታ ለማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ወደ መላ መጠተው ለጤናዎ መላ ይፈልጉለት
መላ!! የአዲስ ጤናማ ሂወት ዜይቤ አጋር
ዪደውሉልን⤵️
☎️ 09 09 55 88 77
Website: www.melawellness.org

05/04/2025

ለጤናዎ በመላ መላ ይፈልጉለት!!
በመላ የተቀናጀ የጤና ማማከር፤ክትትል እና ስልጠና ፕሮግራም ህይወቶን ይለውጡ!
በመላ የጤና ማዕከል ጤናዎን ይጠብቁ! 🌟
የሰውነት ውፈረት ለመቀነስ እና በቦርጭ ምክንያት የሚከሰቱ በሸታዎችን ለመከላከል እና ለማስቆም ይፈልጋሉ?
የስኳር በሽታን ና ደም ግፊት ጉዳት በምግብና በአጋል ብቃት እንቅስቃሴ መከላከል እና ተጋላጭነትን ለመቀልበስ ወስነዋል?
የኮለስትሮል(Cholestrol) እና ሆርሞን(Hormon) መጠን መዛባትን ማስተካከል ያስፈልጎታል?
የሰውነት ቅርፅ በምግብና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስተካከል ያስፈልጎታል?
የሰውነት ክብደት መጨመርና የጡንቻ መዳበር ፍላጎት አሎት?
የተቀናጀ አጠቃላይ የጤናማነት ምርመራ፤ክትትል፤ምክርና ስልጠና በሃኪም፤በስነ-ምግብ ባለሙያና (Dietician) በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለሙያ (Personal trainer) አገልግሎት በአንድ ቦታ ለማግኘት ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ወደ መላ መጠተው ለጤናዎ መላ ይፈልጉለት
መላ!! የአዲስ ጤናማ ሂወት ዜይቤ አጋር
ዪደውሉልን⤵️
☎️ 09 09 55 88 77

Address

Bulbula
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MELA Wellness Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share