MEBA STAR Medical Clinic

MEBA STAR Medical Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MEBA STAR Medical Clinic, Medical and health, Tulu Dimtu Arsema Adebabay, Addis Ababa.

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ ለጤናችሁ የሚተጋው መባ ስታር ሜዲካል ክሊኒክ ነው     ቸር ያሰማን ሰናይ ጊዜ!!!
07/01/2025

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሳችሁ ለጤናችሁ የሚተጋው መባ ስታር ሜዲካል ክሊኒክ ነው
ቸር ያሰማን ሰናይ ጊዜ!!!

  ክሊኒክ✍️  #ደረቅ  #ሳል  #አይነተኛ  #ምልክታቸው  #የሆኑ  #ህመሞች⏩  #ደረቅ ሳል በምናስልበት ወቅት ተከትሎ አክታ እማናስወግድ ከሆነ( ከሌለ)ነው፡፡⏩  #ዋና  #ዋና  #ምክንያ...
02/01/2025

ክሊኒክ

✍️ #ደረቅ #ሳል #አይነተኛ #ምልክታቸው #የሆኑ #ህመሞች

⏩ #ደረቅ ሳል በምናስልበት ወቅት ተከትሎ አክታ እማናስወግድ ከሆነ( ከሌለ)ነው፡፡

⏩ #ዋና #ዋና #ምክንያቶች

🔵 #አስም፡- አስም የምንለው የመተንፈሻ ትቦ ሊያብጥና በማበጡም ሲጠብ የሚፈጠር ነው፡፡ተያይዞም እነዚህ ምልክቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ ፡-

🔹 ሲርታ ድምጽ መሰማት
🔹 የትንፋሽ ማጠር
🔹 የደረት ውጋት
🔹 ሳል ከእንቅልፍ የሚረብሽ

🔵 #ቃር፡- ይህ ችግር የጨጓራ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወደላይ (ወደ ምግብ ትቦና ጉሮሮ) ሲመለስ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ይህ አሲድ ሳል እንዲቀሰቀስ ያደርጋል ተያይዞም ፡-

🔹የደረት ማቃጠል
🔹 የምግብ / ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስ
🔹 ረጅም ጊዜ የሚስተዋል ደረቅ ሳል
🔹ጉሮሮ አካባቢ ያበጠ ስሜት መሰማት
🔹 የድምጽ መቀየር

🔵 #የቫይረስ #ኢንፌክሽን፡- እንደ ጉንፋን ፣ ኮሮና የመሳሰሉት ቫይረሶች ደረቅ ሳልን የማስከተል አቅም አላቸው፡፡

🔵 #ለኬሚካሎች #እና #ብናኞች #መጋለጥ፡- ይህ ሁኔታ በስራችን / በአካባቢያችን ተጋላጭነት ካለ አለርጂን በመፍጠር ደረቅ ሳልን ያስከትላሉ ፡፡

🔵 #አንዳንድ ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች

🔵 #ትክትክ በተለይ በህጻናት ላይ

🔵 #የሳንባ ካንሰር

🔵 #የልብ ድካም

🔵 #የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ተያይዞ ያሉ ምልክቶች

🔹 ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት ማሳል
🔹 የደረት ህመም
🔹 በሚተነፍሱበት ወቅት ወይም በማሳል ወቅት የደረት ህመም
🔹 ክብደት መቀነስ
🔹 ድካም
🔹 ትኩሳት
?? የምሽት ላብ
🔹 ብርድ ብርድ ማለት

⏩ #ደረቅ #ሳልን #ለመከላከል

🔹 #በጨው #መጉመጥመጥ፦ በመጠኑ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ጨው በመጨመር ቀና ብለን ጉሮሯችንን እንዲያጸዳ በማድረግ መጉመጥመጥ ደረቅ ሳልን ለመከላከል ወይም በቀላሉ ለማስቆም ይችላል።

🔹 #ፍራፍሬዎችን #አዘውትሮ #መመገብ፦ ፍራፍሬዎችን በጭማቂ መልክም ይሁን ጥሬያቸውን አዘውትሮ መጠቀም ፍራፍሬዎቹ በውስጣቸው ባለው ንጥረ ነገር አማካኝነት ለደረቅ ሳል እንዳንጋለጥም ይረዱናል።

🔹 #አረንጓዴ #ሻይ፦ አረንጓዴ ሻዩን በሻይ ቅጠሉ ማሸጊያ ጀርባ ላይ ባለው አጠቃቀም መሰረት ካፈላን በኋላ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣትም ደረቅ ሳልን ለማከም ፍቱን ነው ። የአረንጓዴ ሻይ እና የማር ጥምረት ደረቅ ሳልን ከማከም ባሻገርም በደረቅ ሳል ወቅት የሚከሰቱ የጉሮሮ ህመሞችንም ለማከም ይረዱናል።

🔹 #የዝንጅብል #ሻይ፦ በፈላ ሻይ /ከተገኘ አረንጓዴ ሻይ / ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ዝንጅብል በመጨመር መጠቀምም ለደረቅ ሳል መፍትሄ ነው።

#አድራሻ :- ወደ ቤ/ያን መንገድ ላይ

!!!

 # #መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ✍️ #ለደም  #አይነትዎ  #ተስማሚ  #የሆኑ  #ምግቦችን  #ያውቃሉ ?👉👉  #የሰው ልጅ የደም አይነት ማወቅ የሚቻለው  በቀይ የደም ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ን...
02/01/2025

# #መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ

✍️ #ለደም #አይነትዎ #ተስማሚ #የሆኑ #ምግቦችን #ያውቃሉ ?
👉👉 #የሰው ልጅ የደም አይነት ማወቅ የሚቻለው በቀይ የደም ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ገሮችን በመመርመር ነው ፡፡ በዚህም መሠረት የደም አይነት ኦ(0) ፣ ኤ(A) ፣ ቢ (ኤቢ(AB) ተብለው በአራት ይከፈላሉ፡፡ የተመገብነው ምግብ ጨጓራ ላይ ከተፈጨ በኋላ በአንጀት ውስጥ አልፎ የተወሰኑ ውህደቶች ከተከናወኑ በኋላ በደም አማካኝነት ወደ ሰውነት ይሰራጫል በዚህም ሂደት ውስጥ ምግብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ውህደትን ይፈጥራሉ፡፡
👉👉 #የደም #አይነትዎ #ኦ #ከሆነ ( )
የምግብ ፕሮፋይል
🔵 ባለ ከፍተኛ ፕሮቲን ስጋ ተመጋቢ ነዎት
👉 #ተስማሚ #ምግቦች
🔵 ስጋ
🔵 አሳ
🔵 አትክልት
🔵 ፈራፍሬ
👉👉 #ክብደት #ለመጨመር #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 ስንዴ
🔵 በቆሎ
🔵 ምስር
🔵 ጥቅል ጎመን
🔵 ድንች
👉👉 #ክብደት #ለመቀነስ #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 ጉበት
🔵 ቀይ ስጋ
🔵 ቆስጣ
🔵 ብሮክሊ
🔵 የባህር ውስጥ ምግቦች
👉👉 #የደም #አይነት #ኤ ( )
🔵 የምግብ ፕሮፋይል
🔵 ቅጠላ ቅጠል ተመጋቢ
👉 #ተስማሚ #ምግቦች
🔵 አትክልት
🔵 የባህር ውስጥ ምግቦች
🔵 ጥራጥሬዎች
🔵 ፍራፍሬዎች
👉👉 #ክብደት #ለመጨመር #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 ስጋ
🔵 ወተት
🔵 ኩላሊት
🔵 ስንዴ
👉👉 #ክብደት #ለመቀነስ #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 የአትክልት ዘይት
🔵 የአኩሪ አተር ምግቦች
🔵 አትክልቶች
🔵 አናናስ
👉👉 #የደም #አይነት #ቢ ( )
🔵 የምግብ ፕሮፋይል
🔵 የአትክልትና ስጋ የተመጣጠነ ተመጋቢ
👉 #ተስማሚ #ምግቦች
🔵 ወተት
🔵 ጥራጥሬዎች
🔵 ቦሎቄ
🔵 አትክልት እና ፍራፍሬ
👉👉 #ክብደት #ለመጨመር #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 በቆሎ
🔵 ምስር
🔵 ለውዝ
🔵 አጃ
🔵 ስንዴ
👉👉 #ክብደት #ለመቀነስ #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 አትክልት
🔵 እንቁላል
🔵 ጉበት
🔵 ሻይ
👉👉 #የደም #አይነት #ኤቢ ( )
🔵 የምግብ ፕሮፋይል
🔵 የሁሉም ምግብ ድብልቅ ተመጋቢ
👉 #ተስማሚ #ምግቦች
🔵 ስጋ
🔵 የባህር ውስጥ ምግቦች
🔵 ወተት
🔵 አትክልት
🔵 ፍራፍሬ
👉👉 #ክብደት #ለመጨመር #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 ቀይ ስጋ
🔵 በቆሎ
🔵 ቦሎቄ
👉👉 #ክብደት #ለመቀነስ #የሚረዱ #ምግቦች
🔵 የባህር ውስጥ ምግቦች
🔵 ወተት
🔵 አትክልት

#አድራሻ፦ቱሊዲምቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሎ ወደ ቤተክርስቲያን መሄጃ መንገድ ላይ
👉0922-405044
👉0927-275536

#ለጤናዎት-እንተጋለን

 #መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ🔷🔷 #የካበተ-ልምድ-ባላቸው ዶ/ሮች-ይከታተሉ✍️ #የልጆች  #አመጋገብ  #ከ6 ወር - 1አመት👉 👉  #ልጆቻችን ምግብ ከጀመሩ በኃላ ምን ያህል በቀን ውስጥ መመገ...
31/12/2024

#መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ
🔷🔷 #የካበተ-ልምድ-ባላቸው ዶ/ሮች-ይከታተሉ

✍️ #የልጆች #አመጋገብ #ከ6 ወር - 1አመት
👉 👉 #ልጆቻችን ምግብ ከጀመሩ በኃላ ምን ያህል በቀን ውስጥ መመገብ ይኖርባቸዋል?
👉 👉ከ6-8 ወር
👉 የጡት ወተት ወይም ድቄት ወተት
👉 ምግብ ከ 2-3 ጊዜ በቀን መመገብ ይኖርባቸዋል
👉 👉 #ቢበሉ የሚመከረው
👉 ከጥራጥሬ እና ከእህል ዘሮች ፡-የተፈጨ ሩዝ ፣አጃ ፣ገብስ…
👉 ከፍራፍሬ ፡-አፕል፣ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣…
👉 ከአትክልት፡-ስዃር ድንች፣ ካሮት፣ ፎሶሊያ፣ ዝኩኒ፣ ድንች…
👉 ፕሮቲን ፡- ዶሮ
👉 👉ከ8-10 ወር
👉 የጡት ወተት ወይም ድቄት ወተት
👉 ምግብ 3 ጊዜ በቀን መመገብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም መቆያ (snack) 1 ጊዜ ቢበሉ ይመከራል
👉 ከጥራጥሬ እና ከእህል ዘሮች ፡- ሩዝ፣ ገብስ፣ ተልባ፣ አጃ….
👉 ፍራፍሬ፡- አቮካዶ፣ ሙዝ፣ አፕል፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ኮክ….
👉 አትክልት፡-አበባ ጎመን፣ ብሮኮሊ፣ ስኳር ድንች፣ የፈረንጅ ቃሪያ፣ ፎሶሊያ፣ በደርጃን፣ ዱባ…
👉 ፕሮቲን፡-ዶሮ፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ አሳ…(እንቁላል አላርጅክ ከሆነባቸው ማቆም)
👉 👉10-12
👉 የጡት ወተት ወይም ድቄት ወተት
👉 ምግብ 3 ጊዜ በቀን መመገብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም መቆያ (snack) 1-2 ጊዜ ቢበሉ ይመከራል
👉 ከጥራጥሬ እና ከእህል ዘሮች ፡- ማንኛውም የእህል ዘር ለልጆች አመቺ ሆኖ የተሰራ
👉 ፍራፍሬ፡-አቮካዶ፣ ሙዝ፣ አፕል፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ኮክ…. ቡርትካን፣ ስትሮበሪ ከ 12 ወር በኃላ
👉 አትክልት ፡-አበባ ጎመን ፣ብሮኮሊ፣ ስኳር ድንች፣ የፈረንጅ ቃሪያ፣ ፎሶሊያ፣ በርጃን፣ ዱባ…
👉 ፕሮቲን፡-ዶሮ፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ አሳ…

#አድራሻ ፦ቱሊዲቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሉ-ግራር-ዛፍ-ፊት-ለፊት

☎0922-405044
☎0927-275536

 #መባ- ስታር - ሜዲካል -መካከለኛ-ክሊኒክ 🔹🔹 #የካበተ ልምድ ባላቸው ዶክተሮች ይከታተሎ  #ሽንት  #በምንሸናበት  #ጊዜ  #የማቃጠል  #ስሜት  #መንስኤውና  #መፍትሄውሽንት በምንሸናበ...
29/12/2024

#መባ- ስታር - ሜዲካል -መካከለኛ-ክሊኒክ

🔹🔹 #የካበተ ልምድ ባላቸው ዶክተሮች ይከታተሎ

#ሽንት #በምንሸናበት #ጊዜ #የማቃጠል #ስሜት #መንስኤውና #መፍትሄው

ሽንት በምንሸናበት ጊዜ የህመም ወይም የማቃጠል ስሜት መሠማት በህክምና ቋንቋ ዲስዮሪያ (Dysuria) ይባላል። ይህ የማቃጠል ስሜት በምንሸናበት ጊዜ ወይም ከሸናን በኋላ ይከሰታል።

ይህ ችግር በተፈጥሮአዊ የመራቢያ አካል አቀማመጥ ምክንያት በሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። ሴቶች አጭር የሽንት ፊኛ ቱቦ አላቸው (ሽንትን ከሽንት ፊኛ ወደ ውጪ የሚያወጡ)። እና የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ከሰገራ መውጫ ቀዳዳና ከሴት አባላዘር በጣም በቅርብ እርቀት ተጠጋግተው ይገኛሉ።

☑️ ሽንት ከሸናሁ በኋላ ለምን የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል?

ይህ የማቃጠል ስሜት ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዘ ነው። ኢንፌክሽኑ በማንኛውም የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ክፍል ውስጥ ሊከሰት ይችላል።

በአንድ ክፍል ላይ ከጀመረን በኋላ ካልታከምነው ወደተለያዮ ክፍሎች ይዛመታል። በዚህም ኢንፌክሽን ዩሬትራ፣ የሽንት ፊኛ፣ ዩሬተር እና ኩላሊት የመጠቃት ዕድል አላቸው።

ሽንት ከሸኑ በኋላ የማቃጠል ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፦

1. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

ይህ በጣም ከተለመድት ምክንያቶች ውስጥ አንድ ነው። ይህ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መነሾ ወደ ሽንት ሥርዓት የመግባት ዕድል ባገኙ ባክቴሪያዎች ምክንያት ይከሰታል። ከዚያም ወደተያያዙ የሰውነት ክፍሎችና ዩሬትራ ይዛመታል። የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሌሎች ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:-

🔹 የሆድ ህመም ወይም በሚሸኑበት ጊዜ ህመም።
🔹 ፒንክ ወይም ቀይ ቀለም ያለው ሽንት።
🔹 ከወትሮው ለየት ያለ ጥሩ ያልሆነ ሽታ ያለው ሽንት።
🔹 የሽንት ፊኛቸው ባዶ ቢሆን እንኳን ለመሽናት መጣደፍ/መቸኮል።
🔹 የጀርባ ህመምና አጠቃላይ የህመም ስሜት መሰማት።
🔹 በዳሌ አካባቢ የምቾት ማጣት ስሜት።

ይህ ኢንፌክሽን ከሽንት ቧንቧ መስመር ካለፈ ለምሳሌ ወደ ኩላሊት ከተዛመተ ምልክቶቹ በደንብ ይወጣሉ ከነዚህም ምልክቶች መካከል ፦

🔹 ትኩሳት
🔹 የጀርባ ህመም
🔹 የጎን ወይም ዳሌ አካባቢ ህመም
🔹 ማቅለሽለሽ
🔹 ማስመለስና
🔹 ተቅማጥ ናቸው።

☑️ ለሽንት ቧንቧ የሚያጋልጡ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-

🔸 በዕድሜ የገፉ ሰዎች
🔸 የስኳር በሽተኞች
🔸 ሴቶች
🔸 የኩላሊት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች
🔸 እርጉዝ ሴቶች
🔸 በመጠን ትልቅ የሆነ ፕሮስቴት ዕጢ ያላቸው ሰዎች (በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች)
🔸 የሽንት መሽኒያ ቱቦ ወይም ካቲተር የተገጠመላቸው ሰዎች።

2. በግብረ - ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች

ባክቴሪያዎች በምንሸናበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ለመከሰቱ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው። ይህም የብልት ኸርፐስ፣ ክላሚዲያ እና ጨብጥ ይጠቀሳሉ። ሌሎች ከግብረ - ሥጋ ግንኙነት ኢንፌክሽን ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እነሆ:-

👉 ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ
👉 ከማቃጠል ስሜት በተጨማሪ የማሳከክ ምልክት

3. የብልት ኢንፌክሽን

የብልት ኢንፌክሽን ለምሳሌ እንደ ይስት ኢንፌክሽን (Yeast Infection) የማቃጠል ስሜት ከማስከተላቸው በተጨማሪ በብልት አካባቢ ማሳከክና መቅላት (Redness) ምልክቶች ያስከትላሉ።

ሌሎች የይስት ኢንፌክሽን ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ:-

🍀 ያልተለመደ ነጭ አይብ የመሰለ የብልት ፈሳሽ
🍀 በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመምና የማቃጠል ስሜት መሰማት
🍀 በውጫዊ የብልት አካባቢ የህመምና የማሳከክ ስሜት መሰማት።

4. የዩሬትራ አቀማመጥ (Urethral structu

 #መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ✍️ #የጡንቻ  #ህመም  #ምልክቶች⏩  #ድንገት ሰውነትን ሽምቅቅ  ከታተሉን፡-⏩  #ምልክቶች🔵 የሰውነት ህመም ስሜት🔵 ሰውነትን እንደተፈለገ ማንቀሳቀስ አለመቻል...
28/12/2024

#መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ

✍️ #የጡንቻ #ህመም #ምልክቶች

⏩ #ድንገት ሰውነትን ሽምቅቅ ከታተሉን፡-

⏩ #ምልክቶች

🔵 የሰውነት ህመም ስሜት
🔵 ሰውነትን እንደተፈለገ ማንቀሳቀስ አለመቻል
🔵 ቁርጥማት
🔵 ብርድ ብርድ ማለት ይጠቀሳሉ፡፡
⏩ #መንስኤዎቹ
🔵 ከባድ ስራዎችን ማዘውተር
🔵 ረፍት አለማድረግ
🔵 የመውደቅ ወይም የመመታት አደጋ
🔵 የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
🔵 ለኮሌስትሮል ማስተካከያ ተብለው የሚወሰዱ መድሀኒቶች
🔵 የጡንቻ መቆጣት
🔵 የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሳያሟሙቁ መጀመር
🔵 በሰውነት ውስጥ የፖታሲየም ንጥረ-ነገር እጥረት መከሰት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

⏩ #በቤት #ውስጥ #ሊያደርጓቸው #የሚችሉት #መፍትሄዎች

🔵 ረፍት ማድረግ
🔵 የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶችን መውሰድ
🔵 የታመመው ጡንቻ ላይ በበረዶ መያዝ ነገር ግን 3 ቀን ካለፈው ለብ ያለ ውሀን መጠቀም
🔵 ሰውነትን ለማሳሳብ መሞከር
🔵 ከባድ ስራዎችን ማቆም

#አድራሻ፦ቱሊዲቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሎ-ግራር-ዛፍ-ፊት-ለፊት

📞0922-405044
📞0927-275536

 #መባ-ስታር-ክሊኒክ♦♦እርጉዝ ሴት እንዴት መተኛት አለባት?  ♦በእርግዝና ወቅት በተለመደው መንገድ መተኛት ምቾት ለምን ይነሳናል ?  ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት ብዙ ለውጦች ስለሚመጡ ምቾ...
28/12/2024

#መባ-ስታር-ክሊኒክ

♦♦እርጉዝ ሴት እንዴት መተኛት አለባት?

♦በእርግዝና ወቅት በተለመደው መንገድ መተኛት ምቾት ለምን ይነሳናል ? ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት ብዙ ለውጦች ስለሚመጡ ምቾት አይኖረንም
፡-የሆድ መጠን ይጨምራል
፡- የጀርባ ህመም
፡-የደረት ህመም
፡-የትንፋሽ ማጠር
፡-የእንቅልፍ እጦት እነዚህ ምቾት እንዳይኖር ያደርጋሉ

👉 በእርግዝ ወቅት ተመራጭ ወይም መሆን ያለበት አተኛኘት
በአብዛኛው ተመራጭ የሚሆነው በጎን መተኛት ነው ለፅንሱም ለእናትየውም መቾት ይሰጣል

 አንዱን እግር ዘርግቶ ከላይ ያለውን እግር ማጠፍ በሁለቱም እግር መሃል ትራስ መጠቀም

 የጀርባ ህመም ካለ በጎን መተኛት እናም ከሆድ ስር ትራስ ለመጠቀም መሞከር

 በምሽት የደረት ማቃጠል ካለ ከወገብ በላይ ትራሶችን መጠቀም

 ቀኑን ያሳለፈ እርግዝና ከሆነ የትንፋሽ ማጠር ይከሰታል በዚህ ጊዜ በጎን ተኝቶ ከፍ ለያደርግ የሚችል ትራስ መጠቀም፡፡

ይህም ማለት ሁልግዜ ምቾት ይሰማናል ከማለት አይደለም ስለዚህ አቅጣጫ እየቀያየርን መተኛት አለብን የደም ዝውውራችን ጤናማ እንዲሆን መገላበጥ አለብን ስንገላበጥ ግን ተነስተን ትንሽ ቁጭ ብለን መሆን አለብት፡፡

👉👉 በእርገዝና ወቅት ማስወገድ ያለብን አተኛኘት
 በጀርባ መተኛት ፡- የጀርባ ህመምን ፡የአተነፋፈስ ችግርን ፡ የመቀመጫ ኪንታሮትን ፡ዝቅተኛ የሆነ የደም ግፊትን እና
የደም ዝውውርን ለልብ እና ለሰውነታችን መቀነስ የመሰሉትን ያመጣል

 በሆድ መተኛት፡-በእርግዝና ጊዜ ሆድ እየገፋ አካላዊ ለውጥ ይኖራል እና ሆድ መተኛት በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

#አድራሻ፦ #ቱሊዲምቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሎ-ግራር-ዛፍ-ፊት-ለፊት
👉0922-405044
👉0927-275536

#ለጤናዎ-እንተጋለን

 #መባ-ስታር-ክሊኒክ✍️  #የኩላሊት  #ህመም  #ግንዛቤ⏩  #መንስኤዎች 🔹 የስኳር ህመም 🔹ከፍተኛ የደም ግፊት – 🔹ሽንት መቋጠር 🔹 ሌላ የኩላሊት በሽታ 🔹 በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የኩ...
28/12/2024

#መባ-ስታር-ክሊኒክ

✍️ #የኩላሊት #ህመም #ግንዛቤ

⏩ #መንስኤዎች

🔹 የስኳር ህመም
🔹ከፍተኛ የደም ግፊት –
🔹ሽንት መቋጠር
🔹 ሌላ የኩላሊት በሽታ
🔹 በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የኩላሊት እድገት ችግር
🔹አንዳንድ መድሃኒቶች – እንደ አስፕሪን እና አይቡ ፕሮፊን የመሳሰሉ መድሃኒቶች
🔹 ኩላሊት ላይ የሚደርስ ጉዳት

⏩ #ምልክቶች

🔹ብዙ ጊዜ ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ እስኪደርስ እንደታመምን ላናውቅ እንችላለን።
🔹የደም ማነስ
🔹ደም የተቀላቀለበት ሽንት
🔹 የጠቆረ ሽንት
🔹 ንቁ አለመሆን
🔹 የሽንት መጠን መቀነስ
🔹 የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ
🔹 የድካም ስሜት
🔹 የደም ግፊት
🔹 እንቅልፍ እጦት
🔹የቆዳ ማከክ
🔹 የምግብ ፍላጎት መጥፋት
🔹ወንዶች ላይ የብልት መነሳት ችግር
🔹 በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ
🔹 የትንፋሽ እጥረት
🔹ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት
🔹 በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት
🔹ራስ ምታት

⏩ #የኩላሊት #በሽታ #ደረጃዎች

🔹 🔹 ጂኤፍአር ሬት(GFR rate) የኩላሊት ጤንነት የሚታወቅበት መለኪያ ነው። የጂኤፍአር መጠን የኩላሊታችንን ጤነንት ይናገራል።

🔹 #ደረጃ 1 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ጤነኛ ነው። ቢሆንም ግን የኩላሊት በሽታ እንዳለ ታውቋል።
🔹 #ደረጃ 2 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ90 ሚሊ ሊትር በታች ሲሆን ኩላሊታችን ውስጥ በሽታ እንዳለ ያሳውቃል፡፡
🔹 #ደረጃ3 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ60 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
🔹 #ደረጃ 4 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ30 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
🔹 #ደረጃ 5 – የጂ.ኤፍ.አር መጠናችን ከ15 ሚሊ ሊትር በታች ነው። የኩላሊት ማቆም ያጋጥማል፡፡

⏩ #አብዛኛው የኩላሊት በሽታ ታካሚ በሽታው ከስቴጅ 2 አያልፍበትም። ነገር ግን ህመሙ እንዳይባባስ ህክምና በማድረግ የኩላሊትን ጉዳት መከላከል ተገቢ ነው።

⏩ #ስኳር በሽታ ያላቸው ሰዎች ዓመታዊ ህክምና ማድረግ አለባቸው። ሽንታቸው ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን በመለካት ኩላሊታቸው አለመታመሙን ማረጋገጥ አለባቸው።

⏩ #ህክምና

🔹 🔹 የተለያዩ ህክምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር አገልግሎት ላይ ይውላሉ። ከባድ ኩላሊት በሽታ ያላቸው ሰዎች ብዙ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል።
🔹 የደም ማነስ ህክምና
🔹 የደም ግፊትን ማከም
🔹 ዳያሊሲስ
🔹 ኩላሊት ንቅለ-ተከላ
🔹 የአመጋገብ ለውጥ

#አድራሻ፦ቱሉዲቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሉ-ግራር-ዛፍ-ፊት-ለፊት-ለፊት
📞0922-405044
📞0927-275536

 #መባ ስታር ክሊኒክ👉እነዚህን ካስተዋሉ የወባ በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችል ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ!    ➡ ከባድ ትኩሳት እና ራስ ምታት ➡ የማንዘፍዘፍ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት➡ የማ...
28/12/2024

#መባ ስታር ክሊኒክ

👉እነዚህን ካስተዋሉ የወባ በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችል ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ!


➡ ከባድ ትኩሳት እና ራስ ምታት
➡ የማንዘፍዘፍ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት
➡ የማላብ
➡ ማቅለሽለሽና ማስመለስ
➡ የጡንቻ ወይም የመገጣጠሚያ ህመም
➡ ድካም
➡ ቶሎ ቶሎ መተፈስ እና የልብ ምት መጨመር
➡ ማንቀጥቀጥ እና ራስን መሳት

#አድራሻ :-

!!!

!

28/12/2024
 ✍️  #ደረቅ  #ሳል  #አይነተኛ  #ምልክታቸው  #የሆኑ  #ህመሞች⏩  #ደረቅ ሳል በምናስልበት ወቅት ተከትሎ አክታ እማናስወግድ ከሆነ( ከሌለ)ነው፡፡⏩  #ዋና  #ዋና  #ምክንያቶች🔵 #...
28/12/2024



✍️ #ደረቅ #ሳል #አይነተኛ #ምልክታቸው #የሆኑ #ህመሞች

⏩ #ደረቅ ሳል በምናስልበት ወቅት ተከትሎ አክታ እማናስወግድ ከሆነ( ከሌለ)ነው፡፡

⏩ #ዋና #ዋና #ምክንያቶች

🔵 #አስም፡- አስም የምንለው የመተንፈሻ ትቦ ሊያብጥና በማበጡም ሲጠብ የሚፈጠር ነው፡፡ተያይዞም እነዚህ ምልክቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ ፡-

🔹 ሲርታ ድምጽ መሰማት
🔹 የትንፋሽ ማጠር
🔹 የደረት ውጋት
🔹 ሳል ከእንቅልፍ የሚረብሽ

🔵 #ቃር፡- ይህ ችግር የጨጓራ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወደላይ (ወደ ምግብ ትቦና ጉሮሮ) ሲመለስ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ይህ አሲድ ሳል እንዲቀሰቀስ ያደርጋል ተያይዞም ፡-

🔹የደረት ማቃጠል
🔹 የምግብ / ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስ
🔹 ረጅም ጊዜ የሚስተዋል ደረቅ ሳል
🔹ጉሮሮ አካባቢ ያበጠ ስሜት መሰማት
🔹 የድምጽ መቀየር

🔵 #የቫይረስ #ኢንፌክሽን፡- እንደ ጉንፋን ፣ ኮሮና የመሳሰሉት ቫይረሶች ደረቅ ሳልን የማስከተል አቅም አላቸው፡፡

🔵 #ለኬሚካሎች #እና #ብናኞች #መጋለጥ፡- ይህ ሁኔታ በስራችን / በአካባቢያችን ተጋላጭነት ካለ አለርጂን በመፍጠር ደረቅ ሳልን ያስከትላሉ ፡፡

🔵 #አንዳንድ ለሌላ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች

🔵 #ትክትክ በተለይ በህጻናት ላይ

🔵 #የሳንባ ካንሰር

🔵 #የልብ ድካም

🔵 #የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ተያይዞ ያሉ ምልክቶች

🔹 ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት ማሳል
🔹 የደረት ህመም
🔹 በሚተነፍሱበት ወቅት ወይም በማሳል ወቅት የደረት ህመም
🔹 ክብደት መቀነስ
🔹 ድካም
🔹 ትኩሳት
?? የምሽት ላብ
🔹 ብርድ ብርድ ማለት

⏩ #ደረቅ #ሳልን #ለመከላከል

🔹 #በጨው #መጉመጥመጥ፦ በመጠኑ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ጨው በመጨመር ቀና ብለን ጉሮሯችንን እንዲያጸዳ በማድረግ መጉመጥመጥ ደረቅ ሳልን ለመከላከል ወይም በቀላሉ ለማስቆም ይችላል።

🔹 #ፍራፍሬዎችን #አዘውትሮ #መመገብ፦ ፍራፍሬዎችን በጭማቂ መልክም ይሁን ጥሬያቸውን አዘውትሮ መጠቀም ፍራፍሬዎቹ በውስጣቸው ባለው ንጥረ ነገር አማካኝነት ለደረቅ ሳል እንዳንጋለጥም ይረዱናል።

🔹 #አረንጓዴ #ሻይ፦ አረንጓዴ ሻዩን በሻይ ቅጠሉ ማሸጊያ ጀርባ ላይ ባለው አጠቃቀም መሰረት ካፈላን በኋላ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣትም ደረቅ ሳልን ለማከም ፍቱን ነው ። የአረንጓዴ ሻይ እና የማር ጥምረት ደረቅ ሳልን ከማከም ባሻገርም በደረቅ ሳል ወቅት የሚከሰቱ የጉሮሮ ህመሞችንም ለማከም ይረዱናል።

🔹 #የዝንጅብል #ሻይ፦ በፈላ ሻይ /ከተገኘ አረንጓዴ ሻይ / ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ዝንጅብል በመጨመር መጠቀምም ለደረቅ ሳል መፍትሄ ነው።

#አድራሻ :-

!!!

 #መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ      💙💙 #የካበተ-ልምድ-ባላቸው-ዶ/ሮች-ይከታተሉ✍  #በተደጋጋሚ  #በሆድ  #ጥገኛ  #ትላትል  #እጠቃለሁ  #ምን  #ይሻላል?⏩  #የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ...
28/12/2024

#መባ-ስታር-ሜዲካል-ክሊኒክ
💙💙 #የካበተ-ልምድ-ባላቸው-ዶ/ሮች-ይከታተሉ

✍ #በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል?

⏩ #የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡

⏩ #ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች

🔹 በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
🔹 የተበከለ ዉሃ
🔹 በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ
🔹 በባዶ እግር መሄድ
🔹 የግል ንፅህና አለመጠበቅ
🔹 የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
🔹 በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር

⏩ #ምልክቶች

🔹 የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
🔹 የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር
🔹 ማቅለሽለሽና ማስመለስ
🔹 የሆድ ህመም/ቁርጠት
🔹 በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት
🔹 የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት
🔹 በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ

⏩ #የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች

🔹 ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ
🔹 ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል
🔹 ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
🔹 ንፅህና መጠበቅ
🔹 ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
🔹 በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት

⏩ #ህክምና

🔹ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡

👉 👉 የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡

#አድራሻ፦ቱሊዲቱ-አርሴማ-አደባባይ-ገባ-ብሉ
☎0922-405044
☎0927-275536

#ለጤናዎ-እንተጋለን

Address

Tulu Dimtu Arsema Adebabay
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MEBA STAR Medical Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share