Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል

Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ  ሆስፒታል We are committed to becoming the premiere Neuroscience Institute in Africa, excelling in Mental Health, Neurology, and Neurosurgery.

This is the official page of Eka Kotebe General Hospital, Addis Ababa, Ethiopia. We are committed to becoming the first Neuroscience Institute in East Africa, with a focus on Mental Health, Neurology, and Neurosurgery.

ኤካ ኮተቤ  ሆስፒታል ለአመራር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ!ቢሾፍቱ  — ኤካ ኮተቤ  ሆስፒታል በቅርቡ በሆስፒታሉ አዲስ መዋቅር ተወዳድረው ለአመራርነት የተመረጡ ባለሙያዎችን ክህሎ...
14/03/2026

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለአመራር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ!

ቢሾፍቱ — ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በቅርቡ በሆስፒታሉ አዲስ መዋቅር ተወዳድረው ለአመራርነት የተመረጡ ባለሙያዎችን ክህሎት የሚያሳድግና ተቋማዊ ሪፎርሙን የሚያፋጥን ጥልቅ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ ሰጠ።

የስልጠናውን መርሃ-ግብር በንግግር የከፈቱት የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ አለሙ እንደገለጹት፤ አዲሱ መዋቅር ውጤታማ እንዲሆን አመራሩ በዘመናዊ የሥራ አመራር ዕውቀት ራሱን ማብቃት ይኖርበታል ብለዋል
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ አመራሮች የአሰራር ስልቶችን በመቀየስና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን በማቀላጠፍ ለታካሚዎች ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ግልጋሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ይህ ስልጠና በዋናነት ትኩረት ያደረገው በቀጣይ በሚከናወኑ የሆስፒታሉ የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ የጥራት ደረጃን ለማዘመን በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ነው።

የስራ ሀላፊዎች የስራ መዘርዝርን በመውሰድ ተፈጻሚ እንዲያደርጉ ዘመናዊ የሥራ ስልቶችን መዘርጋት፣ ግልጽ የሆኑ የተጠያቂነት መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ ሠራተኞችን የሚያበረታቱ የማትጊያ መመሪያዎችን ሥራ ላይ ማዋል የሚሉ ነጥቦች በስልጠናው በስፋት ተዳስሰዋል።

እነዚህ መመሪያዎች ተቋሙ የላቀ፣ የተቀላጠፈና በውጤት ሊለካ የሚችል የሥራ ባህል እንዲገነባ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የየክፍሉ ዳይሬክተሮች እና የዴስክ ኃላፊዎች በስራቸው ለሚገኙ ባለሙያዎች ስራን በቁጥርና በጊዜ ለክቶ የመስጠት፣ የሥራ አፈፃፀምን ተከታትሎ የመረከብ እንዲሁም በትጋት ለሚሠሩ ባለሙያዎች ተገቢውን ዕውቅና የመስጠት ክህሎታቸውን የሚያሳድጉ የሥልጠና ሞጁሎች ቀርበውላቸዋል።

በተጨማሪም በሥራ ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን አስቀድሞ በመለየትና መፍትሔ በመስጠት፣ የሆስፒታሉን ራዕይ ዳር ለማድረስ የሚያስችል "ተቋማዊ የአሠራር ሮድ ማፕ" ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ሰልጣኞቹ በቆይታቸው የቀሰሟቸውን ዕውቀቶች በሥራ ላይ እንዴት ማዋል እንደሚችሉ የሚያሳዩ ዕቅዶችን አቅርበው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

"የአገልግሎት ጥራት አርማችን"

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙአዲስ አበባ – ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የኒውሮ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ለመሆን እየሰራ ባለው ጠንካራ ጥረት፣ ከ...
11/03/2026

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ – ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የኒውሮ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ለመሆን እየሰራ ባለው ጠንካራ ጥረት፣ ከውጭ አገራት ተቋማት ጋር የሚያደርገውን ትብብር ከመጠናከር ባሻገር ከአገር በቀል ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት እያሳደገ ይገኛል።

🤝በዚሁ መሰረት ዛሬ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ ስራን የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርሟል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታልን በመወከል የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር መገርሳ አለሙ እና የቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ግዛው ተገኝተዋል። እንዲሁም ዲላ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤሊያስ አለሙ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ መምህር ትዛለኝ ተስፋዬ ተሳትፈዋል።

🏥የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር መገርሳ አለሙ እንደገለጹት፤ ከአገር በቀል ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የታካሚዎችን የህክምና ጥራት ለማሻሻልና አገር በቀል እውቀቶችን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በተለይም የስነ-አእምሮ ህክምና ማዘመን እና በምርምርና ጥናት መስኮች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚደረግ ትብብር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አስታውቀዋል።

🎓የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤሊያስ አለሙ በበኩላቸው፤ ተቋማቱ በጋራ መስራታቸው ወጣት የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራትና አገር በቀል እውቀቶችን በማበልፀግ የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚረዳ ገልጸዋል። እንዲሁም ይህ ትብብር በተለይ የስነ-አእምሮ ህክምናን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው አመልክተዋል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የስራ ትስስር የሚያጠናክር ሲሆን፣ በጋራ የውል ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርዓቱ በስኬት ተጠናቋል።

“✨ ጥራትን ለማሻሻልና ምርምርን ለማሳደግ በጋራ እንሰራለን!”

08/03/2026
ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የሴቶችን ቀን በልዩ ድምቀት አከበረ፤ በዕለቱ የሕክምና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በሴት ባለሙያዎች ተሰጥቷልአዲስ አበባ — የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115...
07/03/2026

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የሴቶችን ቀን በልዩ ድምቀት አከበረ፤ በዕለቱ የሕክምና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በሴት ባለሙያዎች ተሰጥቷል

አዲስ አበባ — የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሴቶች ቀን (ማርች 8) "50 ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃልና "በመስጠት መቀበል" (Give to Gain) በሚል ንቅናቄ በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በበዓሉ ላይ በጤና ሚኒስቴር የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታሉ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ተምሳሌታዊ የፓናል ውይይት

በዕለቱ በተካሄደው የልምድ ልውውጥና የፓናል ውይይት ላይ ከተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተወጣጡ ስኬታማ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል። ውይይቱ የተለያየ የሥራ እርከን ያላቸውን ባለሙያዎች ያሳተፈ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም፦
• የቀዶ ሕክምና (Surgeon) ስፔሻሊስት
• የማህፀንና ፅንስ ሕክምና ስፔሻሊስት
• የሳይካትሪስት ስፔሻሊስት
• የነርሲንግ ባለሙያ
• የጽዳት አገልግሎት ሠራተኛ
• የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነበሩ።
እነዚህ ባለሙያዎች በሙያዊ ጉዟቸው ያጋጠሟቸውን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች በሴትነት ብርታትና በትጋት እንዴት እንዳለፉ የሚያሳይ አነቃቂ የሕይወት ተሞክሯቸውን ለታዳሚው አጋርተዋል። ይህም በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ላይ የሚገኙ ሴቶች ያላቸውን አቅምና የላቀ ተጋድሎ ያሳየ ነበር።

"ደሜን ለወገኔ" — ከ50 ዩኒት በላይ ደም ተሰበሰበ
በዓሉን በበጎ አድራጎት ተግባር ለማድመቅ በተከናወነው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር የሆስፒታሉ ሠራተኞችና እንግዶች ባሳዩት ከፍተኛ ተሳትፎ ከ50 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰብ ተችሏል። ይህም በተለይ ለእናቶችና ለሕፃናት ሕይወት መትረፍ "በመስጠት ውስጥ መቀበል" እንዳለ በተግባር የታየበት አጋጣሚ ሆኗል።

ታሪካዊ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ
የዘንድሮውን አከባበር ለየት ካደረጉት ኩነቶች መካከል ዋነኛው በሆስፒታሉ የታየው የሥራ ድባብ ነው። በዕለቱ በሁሉም የሕክምና ክፍሎች ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በሴት ሐኪሞችና ባለሙያዎች ብቻ እንዲከናወኑ የተደረገ ሲሆን፣ እንግዶችም በክሊኒካል አገልግሎቱ የታየውን የሴቶች የላቀ ብቃትና ዝግጁነት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
"በመስጠት መቀበል" በሚል መርህ የተከበረው ይህ ዕለት፣ በጤናው ዘርፍ ውስጥ የሴቶችን የማይተካ ሚና ይበልጥ ያጎላና ለቀጣይ ትውልድ ሴት ባለሙያዎች "እኛም እንችላለን" የሚል ትልቅ ተምሳሌትነትን ያሳየ ነበር።

“የአገልግሎት ጥራት አርማችን”

07/03/2026
ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በጤናው ዘርፍ ሪፎርም እና በአዳዲስ አመራሮች ሹመት ላይ ውይይት አካሄደ!አዲስ አበባ — ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በጤናው ዘርፍ የተዘረጋውን አዲሱን የሪፎርም አተገባበር በይፋ...
05/03/2026

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በጤናው ዘርፍ ሪፎርም እና በአዳዲስ አመራሮች ሹመት ላይ ውይይት አካሄደ!

አዲስ አበባ — ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በጤናው ዘርፍ የተዘረጋውን አዲሱን የሪፎርም አተገባበር በይፋ በመቀበል ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ፣ በስትራክቸሩ ወደ አመራርነት ለመጡ አዳዲስ ተሿሚ አመራሮች ጋር የትውውቅና የሥራ አካሄድ መመሪያ ውይይት አካሄደ።

ሆስፒታሉ ስትራክቸር በመስራት የዳይሬክተር እና የዴስክ ኃላፊዎችን በብቃትና በውድድር መመልመል የቻለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ-ግብር አከናውኗል።

በመድረኩም የተነሱ ሀሳቦች

የአሰራር ገለጻ፦ የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ አለሙ፣ ስለ ሆስፒታሉ አጠቃላይ አሰራርና ስለ ሰትራክችር እና የሆስፒታሉ ኦርጋኖ ግራም አስፈላጊነት ጥልቅ ገለጻ አድርገዋል።

የሥራ መዘርዝር (JD)፦ በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ዘርፍ በኩል ወ/ሪት ትዕግስት አማረ፣ አዲስ ለተመደቡ የዳይሬክተር እና የኬዝ ቲም ኃላፊዎች የሥራ መዘርዝርና ኃላፊነታቸውን የሚያብራራ ሰነድ አቅርበዋል።

አገልግሎት ደረጃ (Service Standard)፦ ዶ/ር ፍቃዱ አዱኛ በበኩላቸው፣ ሆስፒታሉ ለተገልጋዮች የሚሰጠው አገልግሎት ሊያሟላ ስለሚገባው ዓለም አቀፍና አገራዊ ስታንዳርድ ገለጻ ሰጥተዋል።

የአሰራር ጥራትን ለማስጠበቅ፦ በሜዲካል ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ጌታቸው ደሞዝ አሰራርን በማዘመንና ጥራትን በማስጠበቅ የመረካከብ ሂደቱን በማሳለጥ በቀጣይ የአሰራር ሪፓርት ፍሰት ምን እንደሚመስል ጥልቅ ገለጻ ሰጥቷል
በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሜዲካል ዳይሬክተሩና በሆስፒታሉ ቺፍ ኤክኪዩቲቭ ምላሽና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ተሳታፊዎቹ በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል አዳዲስ ሪፎርሞችና አመራሮች ሲመጡ ሥራዎች ከዜሮ የመጀመር ልምድ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን የተደረገው "ቀልጣፋ የሥራ ሽግግር" ግን ችግሮችን የሚቀርፍና ለሥራው ቀጣይነት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን በአድናቆት ገልጸዋል።

በመጨረሻም የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሆስፒታሉ አሰራሮችን በማዘመንና ጥራትን በመጠበቅ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸዋል። አዲሶቹ አመራሮችም ለተቋሙ ስኬት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

"የአገልግሎት ጥራት አርማችን"

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል   በዓል በሰላም አደረሰዎዓድዋ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ግጥም ሲታወስ------------------------------------------------ዋ!... ያቺ...
01/03/2026

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል
በዓል በሰላም አደረሰዎ

ዓድዋ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ግጥም ሲታወስ
------------------------------------------------

ዋ!... ያቺ አድዋ
ዋ!...
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ!... ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው!
ዋ! … ዓድዋ …
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እደገና፡፡
… ዋ! … ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

መልካም በዓል

"የአገልግሎት ጥራት አርማችን"

ስለ ሄፓታይተስ A እና E ማወቅ ያለብን ነገሮች! 1. ምንነታቸው:ሄፓታይተስ A እና E በቫይረስ አማካኝነት የሚመጡ የጉበት በሽታዎች ናቸው። እነዚህ ቫይረሶች በብዛት የሚገኙት ንጽህናቸው ባ...
27/02/2026

ስለ ሄፓታይተስ A እና E ማወቅ ያለብን ነገሮች!

1. ምንነታቸው:
ሄፓታይተስ A እና E በቫይረስ አማካኝነት የሚመጡ የጉበት በሽታዎች ናቸው። እነዚህ ቫይረሶች በብዛት የሚገኙት ንጽህናቸው ባልተጠበቁ ምግብ፣ ውሃ እና ንፅህናው ባልተጠበቀ የመጸዳጃ አጠቃቀም ነው።
2. ምልክቶች (Symptoms):
የዓይን እና የቆዳ ቢጫ መሆን (Jaundice)
ከፍተኛ ድካም እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የሽንት ቀለም መቀየር (እንደ ሻይ መጥቆር)
ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና የሆድ ህመም
3. ህክምና (Treatment):
ልዩ የሆነ የቫይረስ ማጥፊያ መድኃኒት የላቸውም፤ ዋናው ህክምና በቤት ውስጥ የሚደረግ ጥንቃቄ ነው።
እረፍት፡ ሰውነት በሽታውን እንዲቋቋም በቂ እረፍት ማድረግ።
ምግብ፡ ቅባት የሌላቸው እና በቀላሉ የሚፈጩ ምግቦችን መውሰድ።
ፈሳሽ፡ ድርቀትን ለመከላከል በቂ ውሃ እና ጭማቂ መጠጣት።
ማስጠንቀቂያ፡ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ማንኛውንም መድኃኒት ወይም አልኮል አለመውሰድ (ጉበትን የበለጠ ስለሚጎዱ)።
4. መከላከያ መንገዶች (Prevention):
-እጅን በሳሙና እና በውሃ በደንብ መታጠብ (በተለይ ከሽንት ቤት መልስ)።
-የሚጠጣ ውሃን አፍልቶ መጠቀም።
-ምግብን በደንብ አብስሎ መመገብ (በተለይ ስጋ እና አትክልት)።
-ለሄፓታይተስ A ክትባት መውሰድ።

“የአገልግሎት ጥራት አርማችን”

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የስታፍ ፎረም አካሄደ አዲስ አበባ – ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የስታፍ ፎረም ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም የስራ አፈጻጸም ሪፓርት ቀርቧል በተጨማሪም የስታፍ ተወካይ በመድረኩ ተመ...
26/02/2026

ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የስታፍ ፎረም አካሄደ

አዲስ አበባ – ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የስታፍ ፎረም ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም የስራ አፈጻጸም ሪፓርት ቀርቧል በተጨማሪም የስታፍ ተወካይ በመድረኩ ተመርጧል፡፡

በሆስፒታሉ ግቢ በተካሄደው የስታፍ ፎረም፣ የባለፉት ስድስት ወራት የክሊኒካል አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም ሆስፒታሉ እየሰጣቸው ያሉ የጤና አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።

በተለይም በሆስፒታሉ እየተገነቡ የሚገኙት ትላልቅ ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ሁኔታ የፎረሙ ዋነኛ አጀንዳ ነበር። የፕሮጀክቶቹን መጠናቀቅ፣ ለሆስፒታሉ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለጤናው ዘርፍ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚኖረው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

በአፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ከሰራተኞች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ አለሙ እና ከቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር ረድኤት ሰለሞን ዝርዝር እና ግልጽነት የተሞላባቸው ምላሾች እና ግንዛቤዎችን የሚሰጡ ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።

በመድረኩም የሆስፒታሉ የሰራተኞች ተወካዮች ምርጫ የተካሄደ ሲሆን አዲስ የተመረጡት ተወካዮችም "የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ እንዲሁም ለሆስፒታሉ ዕድገት በቁርጠኝነት እንሠራለን" ሲሉ ቃለ መሐላ በመፈጸም ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል፣ መርሃግብሩም ተጠናቋል።

“የአገልግሎት ጥራት አርማችን”

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ኢኖቬሽን ሃብ ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት መዘጋጀቱ በሀገራችን የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ማዕከል  አዳዲስ ሀሳቦች የሚፈልቁበት ወደ ተግባር...
17/02/2026

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ኢኖቬሽን ሃብ ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት መዘጋጀቱ በሀገራችን የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ማዕከል አዳዲስ ሀሳቦች የሚፈልቁበት ወደ ተግባር የሚቀየሩበት "የፈጠራ ማዕከል" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ዋና ዋና ነጥቦች

ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታልና መሰል የጤና ተቋማት የሚሰጠው ጥቅም
ይህ ሃብ በሆስፒታሉ ውስጥ መገንባቱ "Health-Tech" ወይም የጤና ቴክኖሎጂን ለማዘመን ትልቅ ዕድል ይሰጣል።

 ዘመናዊ የህክምና መረጃ አያያዝ፦ ለሆስፒታሉ ታካሚዎች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡ የዲጂታል ሲስተሞችን (E-Health) እዚያው ማዕከሉ ውስጥ በማልማት ስራ ላይ ማዋል ይቻላል።
 የህክምና መሣሪያዎች ጥገናና ፈጠራ፦ ከውጭ የሚመጡ ውድ የህክምና መሣሪያዎች ብልሽት ሲገጥማቸው፣ በማዕከሉ ያሉ መሃንዲሶች ጥገና እንዲያደርጉ ወይም መለዋወጫዎችን በ "3D Printing" እና መሰል ቴክኖሎጂዎች እንዲያመርቱ ይረዳል።
 የቴሌ-ሜዲሲን (Telemedicine) ልማት፦ ሐኪሞች ርቀት ላይ ሆነው በቴክኖሎጂ ታካሚዎችን እንዲያክሙ የሚያስችሉ የሶፍትዌር መተግበሪያዎችን ለማልማት ይጠቅማል።
 ለጥናትና ምርምር፦ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚታዩ የጤና አገልግሎት ክፍተቶችን በጥናት በመለየት፣ በኢኖቬሽን ማዕከሉ በኩል ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄዎችን ወዲያውኑ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል።
ለሌሎች መሰል ተቋማት እንደ አርአያነት
ይህ ማዕከል ለሌሎች የመንግስትና የግል ተቋማት የሚከተሉትን ትምህርቶች ይሰጣል፦
• የተቋማት ትስስር (Collaboration)፦ አንድ ተቋም ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የፈጠራ ማዕከል ማቋቋም እንዳለበት ማሳያ ይሆናል።
• የሃብት አጠቃቀም፦ ያሉትን ግብዓቶች (ቦታ፣ የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ) በማቀናጀት እንዴት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ለሌሎች ሆስፒታሎችና ዩኒቨርሲቲዎች አርአያ ይሆናል።
"የፈጠራ ሆስፒታል" (The Innovative Hospital) ስም መገንባት
አንድ ሆስፒታል የራሱ የፈጠራ ማዕከል ሲኖረው፣ ለታካሚዎች የሚሰጠው ስነ-ልቦናዊ እሴት ከፍተኛ ነው።
• ታካሚዎች "እዚህ ሆስፒታል ውስጥ አዳዲስ ግኝቶችና መፍትሄዎች ይፈጠራሉ" የሚል እምነት እንዲያድሩባቸው ያደርጋል። ይህም ኢትዮጵያን በጤናው ዘርፍ የሪፈራል መዳረሻ (Medical Hub) ያደርጋታል።
ለሀገርና ለወጣቶች የሚሰጠው ጥቅም
ማዕከሉ ከግለሰብ አልፎ የሀገርን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥበት አቅም አለው።
• የወጣቶች የፈጠራ አድማስ ማስፋት፦ ወጣቶች ያላቸውን ተሰጥኦ ወደ ገቢ ማግኛና ወደ ስራ ፈጣሪነት (Entrepreneurship) እንዲቀይሩ በማድረግ፣ የሥራ አጥነትን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ይረዳል።
ዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት፦ ሀገሪቱ የጀመረችውን የ "Digital Ethiopia 2025" ስትራቴጂ ዳር ለማድረስ እንደነዚህ ያሉ ማዕከላት የዲጂታል እውቀትና ክህሎት ማፍሪያ ይሆናል።

“የአገልግሎት ጥራት አርማችን”

16/02/2026

Celebrating my 1st year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram