Fikir PsychΨ

Fikir PsychΨ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fikir PsychΨ, Health & Wellness Website, Addis Ababa.

ሰላም ሴቶች ዛሬ ቀናችን ነው😁 እንኳን አደረሳችሁ። 🎉አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሴትነት ለእናንተ ምንድን ነው?Lets talk to heal.☺️https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️
08/03/2026

ሰላም ሴቶች ዛሬ ቀናችን ነው😁
እንኳን አደረሳችሁ። 🎉
አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሴትነት ለእናንተ ምንድን ነው?
Lets talk to heal.☺️
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

የልብ  እንቆቅልሽስለ ፍቅር፣ ክብር እና አታችመንት(The Heart's Riddle: On Love, Respect, and Attachment)ለመነጋገር የፊታችን እሁድ ማታ ከ 3:30 ጀምሮ በፍቅ...
27/02/2026

የልብ እንቆቅልሽ
ስለ ፍቅር፣ ክብር እና አታችመንት
(The Heart's Riddle: On Love, Respect, and Attachment)
ለመነጋገር የፊታችን እሁድ ማታ ከ 3:30 ጀምሮ በፍቅር ሳይክ ይጠብቁን ከባለሙያ ጋር እንመጣለን 🙏

Fikir psych"Where you talk to heal"🦋
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

የእናንተ የፍቅር ግንኙነት ምን ይመስላል?አታችመንት ስታይል (Attachment Style) በሥነ ልቦና ውስጥ በልጅነት ጊዜ በልጅና በእንክብካቤ ሰጭ  (እናት/አባት ወይም አሳዳጊ መካከል የሚ...
14/02/2026

የእናንተ የፍቅር ግንኙነት ምን ይመስላል?

አታችመንት ስታይል (Attachment Style) በሥነ ልቦና ውስጥ በልጅነት ጊዜ በልጅና በእንክብካቤ ሰጭ (እናት/አባት ወይም አሳዳጊ መካከል የሚፈጠር ስሜታዊ ትስስርና ግንኙነት ዘይቤ ሲሆን፣ ይህም በአዋቂነት ጊዜ በፍቅር ግንኙነቶችና በሌሎች ግንኙነቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያሳድራል።

ዋና ዋናዎቹ አታችመንት ስታይል የምንላቸው እነዚህ ናቸው።

1. ደህንነቱ የተጠበቀ (Secure Attachment)
- ልጁ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተወደደና ድጋፍ የሚያገኝ ይሰማዋል።
- ቅርበትንም ነጻነትንም በቀላሉ ይቀበላል።
- በአዋቂነት፡ እምነት ያለው ግንኙነት፣ ጤናማ ግንኙነት፣ ስሜታዊ መረጋጋት፣ በቀላሉ ይተማመናል።

2. ጭንቀት ያለበት (Anxious / Preoccupied Attachment)
- የመተው ፍርሃት በጣም ከፍተኛ ነው።
- ቀጣይነት ያለው ማረጋገጫና ቅርበት ይፈልጋል።
- በአዋቂነት፡ ቅናት፣ ስሜታዊ ጥገኛነት፣ ስለ ግንኙነት ያለማቋረጥ ዋጋት፣ ብዙ ጭንቀት።

3. ቸልተኛ (Avoidant / Dismissive Attachment)
- እንክብካቤ ሰው ስሜታዊ ርቀት ወይም መካድ ነበረው።
- ስሜቶችን ይደብቃል፣ ብቻውን መተማመን ይማራል።
- በአዋቂነት፡ ቅርበትን ይርቃል፣ ነጻ ይመስላል ግን ቅርበት ሲፈልግ ይቸገራል፣ ስሜታዊ ርቀት ይኖረዋል።

4. የተዛባ (Disorganized /
Fearful -Avoidant Attachment)
- እንክብካቤ ሰው አስፈሪ ወይም የሚያስፈራ ነበር (ብዙውን ጊዜ ከአሰቃቂ ታሪክ ጋር የተያያዘ)።
- ልጁ ቅርበት ይፈልጋል ነገር ግን ይፈራልም፣ የተደባለቀ ባህሪ ያሳያል።
- በአዋቂነት፡ ስሜታዊ አለመረጋጋት፣ እምነት መገንባት አለመቻል፣ ከአሰቃቂ ተጽእኖዎች ጋር የተያያዙ ቅጦች።

ከዚህ በመነሳት የእርሶ የፍቅር ግንኙነት ጤናማ ነው ብለው ያስባሉ?ካልሆነ ከታች ያለውን መጠይቅ ሰርተው ምን ላይ እንዳሉ ራሶትን እና ግንኙነቶን ይመርምሩ።

ለሚመለከታችሁ ብቻ Happy Valentine's Day.❤️🪄

Fikir psych"Where you talk to heal"🦋
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

ሰላም የፍቅር ስነልቦና አባላት በውስጥ መስመር ከተጠየቅናቸው ጥያቄዎች በደንበኛችን ፍቃድ መሰረት ለእናንተ ያስተምራል ያልነውን ለውይይት እንሆ ብለናል።ያንብቡት"ሰዎች የገጠማቸውን ችግሮች እ...
12/02/2026

ሰላም የፍቅር ስነልቦና አባላት በውስጥ መስመር ከተጠየቅናቸው ጥያቄዎች በደንበኛችን ፍቃድ መሰረት ለእናንተ ያስተምራል ያልነውን ለውይይት እንሆ ብለናል።ያንብቡት

"ሰዎች የገጠማቸውን ችግሮች እየነገሩን ማልቀስ ቢፈልጉ ወይም ቢያለቅሱ መከልከል ወይም ማልቀሳቸውን ማስቆም ይኖርብናል ወይ? ሰዎችስ ሲያለቅሱ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን እና የሌለብን?"

እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳብ አስተያየታችሁን ስጡን እና እንወያይ።መልካም ጊዜ!
ሌሎችም በግል ማማከር የምትፈልጉ በውስጥ ፃፉልኝ🙏

Fikir psych"Where you talk to heal"🦋
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።🙏https://t.me/fikirpsych
18/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።🙏
https://t.me/fikirpsych

18/01/2026
ለራስ የህመም መለያ መስጠት (Self Diagnosis) ምን ማለት ነው? አንድ ሰው የራሱን የአእምሮ ወይም የስነ-ልቦናዊ ችግር በባለሙያ ግምገማ ሳይደረግለት፣ በራሱ ስሜት፣ በኦንላይን መረጃ...
09/01/2026

ለራስ የህመም መለያ መስጠት (Self Diagnosis) ምን ማለት ነው?

አንድ ሰው የራሱን የአእምሮ ወይም የስነ-ልቦናዊ ችግር በባለሙያ ግምገማ ሳይደረግለት፣ በራሱ ስሜት፣ በኦንላይን መረጃዎች ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባየው ነገር መሰረት መለያ መስጠት ወይም “ይህ ነው” ብሎ መወሰን ነው።

በስነ-ልቦና መስክ አንድ ሰው የህመም መለያ ማግኘት የሚችለው በዘርፉ ከሰለጠኑ ባለሙያዎች ብቻ ነው ስንልራስን ምርመራ ምርመራው በራሱ የሚያስፈልጉት ቅድመሁኔታዎች ስላሉት ነው። ለምሳሌ
- ልዩ የባለሙያ ስልጠና
- የተደራጀ እና ጥልቅ ግምገማ
- የግለሰቡን፣ የማህበረሰቡን እና የባህሉን ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ መረዳት ነው።

ለራስ መለያ መስጠት ብዙ ጊዜ ወደ ስህተት ግንዛቤ፣ ወደ ተሳሳተ እርዳታ ወይም የበለጠ ግራ መጋባት ሊያመራ ይችላል።

ህመምህን መለየት እና መግለጽ ጥሩ መጀመሪያ ነው፣ ግን መጨረሻ አይደለም። ባለሙያ እርዳታ መጠየቅ የራስን ጤና መንከባከብና የብስለት ምልክት ነው።

ባሉበት ሆነው ሙያዊ፣ተአማኒ እና ርህራሄ የተሞላ ህክምና ከፍቅር ስነልቦና የምክክር አገልግሎት ያግኙ!

ፍቅር ስነ ልቦና "በምክክር እንዳን"🗣👩‍⚕️
https://t.me/fikirpsych

⭐️ለመላው የፍቅር ሳይክ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንሆ ታላቅ የምስራች!🎉🎉“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።”የሉቃስ ወንጌል 2፥10-11...
08/01/2026

⭐️ለመላው የፍቅር ሳይክ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንሆ ታላቅ የምስራች!🎉🎉

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።”
የሉቃስ ወንጌል 2፥10-11

🍭🍭🍭መልካም በዓል ይሁንልን🍭🍭🍭
Fikir Psych"Where you talk to heal"🦋
Lalibela, Ethiopia
https://t.me/fikirpsych

30/12/2025

This year come to end.For next year
What do you plan on this wheel of life?
Lets talk to heal.🦋
Join us -https://t.me/fikirpsych

በሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ ስሜቶች (extreme emotions) ሲሰማንሁለቱም ተመሳሳይ የፊዚዮሎጂ ምላሾችን ይሰጣሉ። ስለዚህ አእምሮህን መቀየር ጭንቀትን ወደ ተነሳሽነት ለመቀየር ያስችላል።...
27/12/2025

በሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ ስሜቶች (extreme emotions) ሲሰማንሁለቱም ተመሳሳይ የፊዚዮሎጂ ምላሾችን ይሰጣሉ። ስለዚህ አእምሮህን መቀየር ጭንቀትን ወደ ተነሳሽነት ለመቀየር ያስችላል።

ይህ ዘዴ (cognitive reappraisal)ይባላል። በሳይንሳዊ ጥናቶች የተረጋገጠም ነው።በዚህ ዘዴ አንድ ሁኔታን ወይም ክስተትን ትርጉም እንደገና በመተርጎም የሚነሳውን ስሜት እንቀይራለን። ለምሳሌ፣ አሉታዊ ሁኔታን በአዎንታዊ ወይም ገለልተኛ መልኩ በማየት ጭንቀትን ወደ ተነሳሽነት ወይም ደስታ መቀየር ይቻላል።ይህም ስሜትን የመቆጣጠሪያ (Emotional Regulation) አንዱ ዘዴ ነው።

ብዙ ጊዜ የሚጠቀምበት ሰው የተሻለ የስነ-ልቦና ጤና፣ ያነሰ ጭንቀት፣ የተሻለ ግንኙነት እና ከፍተኛ ተነሳሽነት ይኖረዋል።

መልካም ቀን🙏
ፍቅር ስነልቦና "በምክክር እንዳን"
Fikir psych "Where you talk to heal."
https://t.me/fikirpsych🦋

26/12/2025

🔝ከወሊድ በኋላ እናቶች ላይ ከሁለት ሳምንት የበለጠ እነዚህን ምልክቶች ካያችሁ የባለሙያ እርዳታ እንዲያገኙ ይርዷቸው።

የወሊድ በኋላ የሚመጣ ድብርት (Postpartum Depression) ምልክቶች
😔 የማያቋርጥ ሀዘን፣ እርካታ የውስጥ ሰላም ማጣት
😢 ያለ በቂ ምክንያት ብዙ መልቀስ
😴 የእንቅልፍ ችግር (ብዙ መተኛት ወይም መተኛት አለመቻል)
🍽️ የመመገብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር
😓 ድካም፣ ኃይል መጣል
😞 እራስን የመውቀስ እና ብቁ አይደለሁም የሚል ስሜት
😶 ከሕፃኑ ጋር መቀራረብ አለመፈለግ
😟 ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ብዙ ማሰብ
🧠 ትኩረት መቀነስ፣ ውሳኔ መስጠት መቸገር
🚨 ራስን መጎዳት ወይም ሕፃኑን መጎዳት የሚመጡ ሐሳቦች (አደገኛ)

👉 በእነዚህ ሁኔታዎች ወዲያውኑ የጤና ባለሙያ ማግኘት አስፈላጊ ነው።

ፍቅር ስነልቦና "በምክክር እንዳን"
Fikir psych "Where you talk to heal."
https://t.me/fikirpsych

24/12/2025

ሴት ልጅ ስትማር...👩‍🏫
"ምግብ ብቻ ሳይሆን የልጆቿን አእምሮም ታበስላለች።"መማር ያስከብራል ሀገርን ያኮራል!
መልካም ቀን🦋
https://t.me/fikirpsych
https://vm.tiktok.com/ZMDNTDJgr/

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fikir PsychΨ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram