Digital Hakim

Digital  Hakim Physicians activist

ሁላችንም መብታችንን ለማስከበር ህጉን ቀድሞ ማወቁ አስፈላጊ ነዉ፡፡ሚመለከታቸዉ አካላትም ግዴታቸዉ መሆኑን አዉቀዉ እንዲሰሩ እናሳዉቃለን፡፡
09/10/2025

ሁላችንም መብታችንን ለማስከበር ህጉን ቀድሞ ማወቁ አስፈላጊ ነዉ፡፡
ሚመለከታቸዉ አካላትም ግዴታቸዉ መሆኑን አዉቀዉ እንዲሰሩ እናሳዉቃለን፡፡

 fans
08/10/2025

fans

08/10/2025

በ1990ዓ.ም የወጣው የጤና ባለሙያዎች የጥቅማ ጥቅም አዋጅ ማለትም የTopup፣የተጋላጭነት፣የቤት አበል ጊዜወን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማሻሻል ለነገ የማይባል የጤና ጥበቃ ሚንስትር ሀላፊነትም ግዴታም ጭምር ነው

ማዕከላዊ ኢትዮጵያዛሬ ማለትም  በቀን 28/01/2018 ዓ.ም  ሞያ ፍቃድ ለማሳደስ ነው ይህ ሁሉ ባለሙያ የሚጉላላው።
08/10/2025

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ
ዛሬ ማለትም በቀን 28/01/2018 ዓ.ም ሞያ ፍቃድ ለማሳደስ ነው ይህ ሁሉ ባለሙያ የሚጉላላው።

ደሞዝ ዱዩቲ በተሻሻለው ተደራጁ ጠይቁ አንድነት ሐይል ነው
08/10/2025

ደሞዝ ዱዩቲ በተሻሻለው
ተደራጁ ጠይቁ
አንድነት ሐይል ነው

08/10/2025

ሁሉም የጤና ተቋማት ደሞዝም ሆነ የተረኝነት/Duty ክፍያ ከመስከረም 1, 2018 ጀምሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአዲሱ ስኬል እና የዱቲ መመሪያ መሰረት እንዲከፍሉ አጥብቀን እናሳውቃለን።
አንድነት ሀይል ነው

08/10/2025

ሰላም Digital Hakim🙏
በተለይ የጤና ዘርፍ ከሲቪል ሰርቫንት እራሱን ችሎ እንዲወጣ ጫናዉ ከፍተኛ መሆን አለበት ።
እንቅስቃሴያችሁን እኔም በግሌ የሚደግፍ ሲሆን በተለይ ከሳይንስ ጋር ምንም ዓይነት ቁርኝት ሳይኖረው የመንግስት ሠራተኛ ሆንኩ ባይ መሃይም ስብስብ የጤና ዘርፍ ላይ እየተስተዋለ ያለውን መጥፎ ተግባር የሚያወግዘውን ባለሙያ እንደፈለገ በፈለገው ቃላት የስድብ ናዳ እያወረደበት ማየቴ በጣም ያሳዝነኛል።
ዘርፉ በአጠቃላይ ከሲቪል ሰርቫንት መ/ቤት መውጣቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ተስፋ የሚጭር ደሃውን ማህበረሰብ ያቀፈ እኩል ተጠቃሚነትን የሚያጎላ የወደቀው የጤና ሥርዓት በእግር እንዲቆም የሚያስችል ትልቅ መሰረት ነዉ።
ስለሆነም ማንም ኢትዮጵያዊ የጤና ዘርፍ ባለሙያዎችን ለማፍራት ማህበረሰቡም ሆነ መንግስት ምን ዓይነት ስልት እንደሚከተል ምን ዓይነት መንገድ እንደሚጓዝ በተጠንቀቅ ማወቅ ያለበት ስለሆነ በዋነኛነት ዘርፉን በአጠቃላይ ከcivil servant እራሱን ችሎ እንዲቆም ሥራዎች እንዲሰሩ challenge ማድረግ ትልቅ የሆነውን የጤና ሴክተር ችግር ፈቺ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ።

08/10/2025

የጤና ባለሙያው በመንግስት ሲቀጠርም የግሉን ከፍቶ ለመስራትም መከራ ሆኗል!! የግል ክሊኒክና የግል ፋርማሲ ለመክፈት መስፈርቱ ከባድ ነው!! ስታንዳንድ በሌለው ከተማ የመንግስት ጤና ተቋማት ያላማሉትን ስታንዳርድ እኛ እንጠየቃለን!!

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮም ሙያ ፊቃድ እድሳት ቀን እሰከ 30/02/2018ዓ.ም አራዝሟል ።🙏🙏🙏🙏
08/10/2025

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮም ሙያ ፊቃድ እድሳት ቀን እሰከ 30/02/2018ዓ.ም አራዝሟል ።🙏🙏🙏🙏

08/10/2025

የጤና ባለሙያውን አግባብነት ያለው የመብት ጥያቄ ለማስከበር የምታደርጉትን ያላሳለሰ ትግል ከልቤ አደንቃለሁ የአቅሜንም አበረክታለሁ።
በመቀጠል ደቡብ ወሎ የሚገኘው የአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ደመወዝ የከፈለው በድሮው ነው።
እንድሁም የነሀሴ እና የጳጉሜ ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ እስከ አሁን አልተከፈለም።
ሆስፒታሉ ከቅርብ ጊዜ ውድህ እጅጉን ባለሙያ የሚጨቆንበትና የመብት ረገጣ የሚካሄድበት ተቋም ሆኗል።
ተቋሙ ውስጥ ይሰራል የሚባለው ሰራተኛ መብቱን የማይጠይቅ; የእነሱን ሀሳብ ብቻ እንደወረደ ተቀብሎ የሚያስፈፅምና የሚፈፅም ነው።
በዚህም የተነሳ ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ ባለሙያው ተቋሙን ለመልቀቅ አማራጮችን እየተመለከተ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
ድሮ እጅጉን የሚፈለገው; በጠንካራ አስተዳደር የሚታወቀው ይህ ሆስፒታል አሁን ላይ በተቃራኒ ሆኖ ማየት አሳዛኝ ነው።
በቅርቡ እንኳን ከክልሉ ሶስተኛ ሆኖ የ2 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ መሆኑ ሲታወቅ ይህንን ሽልማት አስመልክቶ አንዱ የአስተዳደር ሰራተኛ " የአስተዳደሩ ጥረት ነው እንጅ ለሽልማት ያበቃው ባለሙያው ምንም የተለየ ነገር አላደረገም; ባለሙያው የእለት ከእለት ስራውን ነው ያከናወነው " ሲል እጅግ ተስፋ አስቆራጭ እና የባለሙያውን ልብ የሰበረ ንግግር አድርጓል።
በእናንተ በኩል ይህን በደል ለህዝብ በማቅረብ ሆስፒታሉ ወደ ቀደመ ከፍታው እንድመለስ እናድርግ።

አመሰግናለሁ

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የባለሙያዎችን ጫና ና የኛንም ጥሪ ተቀብላቹ ሙያ ፊቃድ እድሳት ቀን እሰከ 30/2/2018ዓ.ም ሰላራዘማችሁ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏 ።
08/10/2025

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የባለሙያዎችን ጫና ና የኛንም ጥሪ ተቀብላቹ ሙያ ፊቃድ እድሳት ቀን እሰከ 30/2/2018ዓ.ም ሰላራዘማችሁ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏 ።

08/10/2025

ስለህክምናው /ጤናው ሴክተር አታውሩ በቃችሁ የሚለው በዝቷል። አብዛኞቹ አታውሩ የሚሉት ደሞ ስድስተኛ ክፍል ያላለፉ ነገር ግን በስድብ የበለፀጉ/የከበሩ ናቸው።🤔

Address

Kazanchis
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Digital Hakim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category