11/06/2024
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ የሆነው የታዋቂዋ አርቲስት ዘሪቱ ልጅ ሞት ሲሆን ዋናውን ትችት ቦታ የያዘች የ44 ዓመቷ ጎልማሳ
መስከረም ለቼሳ ናት መስከረም በአመት 50,000 ተማሪዎች ከሚመረቁበት በCicinnate ዩንቨርሲቲ ነው የተማርኩት የምትለዋ መስከረም የትምህርት መረጃዋን ካላየው በዶክተሬቷ ስለማላምን ይቅርታ ዶክተር ለማለት ይከብደኛል ።
ምክንያቱም ብዙ የተማሩ በልፋታቸው ዶክትሬታቸውን የወሰዱ በተማሩትና ባወቁት ዕውቀት ልክ ህዝባቸውን የሚያጋጩ ሳይሆን የሚያጋለግሉ ቅን የሠላም ሰባኪ ዜጎችን ባየሁበት ዓይን ጥላቻን ና መለያየትን ብቻ የሚሰብክን በጥላቻ የታወረን ሰው ዶክተር ያለ ማለት መብቱ ዬኔ ብቻ ነው ።
መስከረም ሰሞኑን በአርቲስት ዘሪቱ ልጅ ሞትን አስታካ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ በተከታታይ ቀናት በተለያዩ ፅሁፎቿ 3 ጊዜ በማያገባት ገብታ እኩያ ልጇ የሞተባትን እናት ስለ አለቃቀሷ ስታብጠለጥላት አይቼ
እቺ ሴት ልጅ ወልዳ ስለ እናትነት ታውቅ ይሆን ብዬ ማንነቷን ለማወቅ የፌስ ቡክ ፕሮፋይሎቿ /ብዙ የፌስ ቡክ ገጿች አሏት በሁሉም ውስጥ ገብቼ አየሁት ። በ1999 እኤአ የዛሬ 25 ዓመት12 ክፍልን ሐረር ተማረች በአጠቃላይ 44 ዓመት ዕድሜ ያላት ያረጠች ሴት ሆና አገኘኋት ። ስለዚህ እናትነት ምን እንደ ሆነ የልጅ ሞት ምን ያህል እንደሚያንገበግብ አታውቅም ።
የመስከረም 75% የገጿ ፅሁፎች ፕሮቴስታንትን የሚያጥላላ ኦርቶዶክስን በፕሮቴስታንት ላይ የሚያነሣሣ የጥላቻ ፅሁፎች ናቸው ። እኛ ኢትዮጵያን ግማሹ ቤተሰብ ፕሮቴስታንት ገሚሶቹ ደግሞ ኦርቶዶክሶች ሆነው በአንድ ጥላ ሥር አንድ በሚያደርጉን ሀሳቦች በአንድነት በሚለያዩን ሀሳቦች ደግሞ ተቻችለን ና ተከባብረን በፍቅር በአንድ ጣሪያ ስር ተስማምተን የምንኖር ዜጎች ነን ።
መስከረም ለቺሣ ግን ጊዜዋን በጥላቻ ላይ መድባ ቤተሰብን ለመለያየት አጥብቃ እየሰራች የምትገኝ ጉድ ናት ።
ዘሪቱ አንድ ግለሰብ ናት ስለ እራሷ ና ስለ ሞተው ልጇ የተናገረች ታድያ ኦርቶዶክስን ና ፕሮቴስታንትን ምን አገባን
ታድያ መስከረም ከ1 አሰከ 3 ፅሁፎችሽ እውን በለቅሶው ላይ የተባሉ የተነጓሩ ሀሳቦች ናቸውን?-
1. ሰው ሲሞት ማልቀስ የሴይጣን ነው ብላለች ኦርቶዶክሳዊያንን በዝምታ ግራ አጋብታለች ።........
2. "እኔ የያዝኩት 'መንፈስ ቅዱስ' የሚያጽናና ከመኾኑ የተነሳ፡ እንደሌላው [በውስጠ ታዋቂ፡ እንደ ኦርቶዶክሶች] ቤተሰቤ ሲሞት ምርር ብዬ አላለቅስም" የሚል መናፍቃዊ መልእክት ለማስተላለፍ ነው ያላለቀሰችው ።......
3 ጴንጤዎች ሆይ! እግዚአብሔርን ከሌሎች የበለጠ እንደምታምኑ ለማሳየት፡ ሰው ሲሞትባችሁ፡ ከገዛ እንባችሁ እና ተፈጥሯዊ ስሜታችሁ ጋር፡ የግድ ትንቅንቅ እየገጠማችሁ፡ ስብከት መስበክ የለባችሁም።
በማለት ያልተባለ ብላ የዕውቀቷን ያህል ለመምከር ሞክራለች ። በለቅሶው ላይ የነበሩ በርካቶቹ ከፕሮቴስታንቶች በላይ ኦርቶዶክሶች እንደነበሩ ማን በነገረሽ
መስከረም እስቲ ትንሽ ቁጭ ብለሽ ኢትዮጵያዊ ሆነሽ ለማሰብ ሞክሪ የሞተው ልጅ ቆንጂዬ ኢትዮጵያዊ ነውና ነጠላሽን ደርበሽ ሄደሽ ዘሪቱን ና ቤተሰቧን አፅናኝ እሱ ነው የኢትዮጵያዊያን ወግ እንጂ በሀዘን ላይ ሀዘን መጨመር አይደለም ።
የእናትነት ስሜት እስከ ቀብር ቀን ብቻ መስሎሽ ከሆነ። ነገ ተነገወዲያ ከልጆቿ ጋር በተጨወተች ቁጥር ና እሱን የሚያስታውሳት ነገር ባየች ቁጥር የሞተው ልጇን እያሰበች የእድሜ ልክ ሀዘኗን በልቧ ተሸክማ የምትኖረውን እናት አላለቀሰችም አምርራ ማልቀስ አለባት ጡጡጡጡጡ የምትሉ ቱልቱላዎች የልጇ ሞት ይባቃታል ና አያገባችሁ ገብታችሁ አታንቦጫርቁ ከልጅቷ ላይ ወረድ በሉላት
የግል ጥላቻችሁንንም በኦርቶዶክስ ስም በመርጨት እምነቶችን ለማጋጨት አትሞክሩ እላለሁ ለመስከረም ለቺሣ እንዲደርስ ላይክና ሼር አድርጉ