AhadCare - ፩ ኬር

AhadCare - ፩ ኬር AhadCare is a platform that connects Doctors and Healthcare seekers remotely, bypassing geographic, infrastructure, and economic limitations.

14/03/2026

አሐድ ኬር....
ባሉበት ሆነው ሐኪም ካስፈለገዎ፣
አሐድኬር ላይ በእጅ ስልክዎ፣
ወይም በድረገጽ ኢንተርኔት ካለዎ፣
"ሀሎ" ቢሉ!
ስፔሻሊስት እና ሰብስፔሻሊስት ያገኛሉ!

ጤና ለሁሉም!

በስልክ ሐኪም ለማግኘት፦
0943722272
በኦንላይን ሐኪም ለማግኘት፦
ahadcare.com

07/03/2026

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!

ባሉበት ሆነው ሐኪም ካስፈለጎት፣
አሐድኬር ላይ ከታች በተቀመጠው ስልክ በመደወል ወይም የአሐድኬርን ድረገጽ በመክፈት የሚፈልጉትን ስፔሻሊስትም ሆነ ሰብስፔሻሊስት ሐኪም ማግኘትና ማማከር እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በተለያዩ የአገራችን ክፍል፣ በገጠርም ሆነ በከተማ፣ እንዲሁም በውጭ አገር በተለያዬ ምክንያት የሐኪም ምክር ና ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው እንዲደርስ ለሌሎችም መልዕክቱን ያጋሩ ።

ስልክ፦ +251943722272
ድረ - ገጽ:- ahadcare.com

AhadCare

#አሐድኬር
#ጤናለሁሉም

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!በእኩለ ሌሊት ድንገተኛ እና ሊቋቋሙት በማይቻል ከፍተኛ የጀርባ ወይም የጎን ውጋት ከእንቅልፍዎ ነቅተው ያውቃሉ? ለብዙ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም በሞቃት ፀሐይ ...
02/03/2026

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!

በእኩለ ሌሊት ድንገተኛ እና ሊቋቋሙት በማይቻል ከፍተኛ የጀርባ ወይም የጎን ውጋት ከእንቅልፍዎ ነቅተው ያውቃሉ?

ለብዙ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም በሞቃት ፀሐይ ላይ ረጅም ሰዓት ለሚሰሩ ወይም ሞቃታማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች፣ ይህ ከፍተኛ ህመም የኩላሊት ጠጠር የመጀመሪያው ምልክት ሊሆን ይችላል።

የኩላሊት ጠጠር በሀገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በስራ ላይ ያሉ እና አምራች የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ሰለባ ያደርጋል። ይህ ከፍተኛ የጤና ቀውስ በቀላሉ መከላከል የምንችለው ወይም ችግር ሳይፈጥር ታክመን የምንድነው ዓይነት በሽታ ነው።

ቀደም ብሎ ማወቅ፣ በቂ ውሃ የመጠጣት ልማድ እና መቼ የህክምና እርዳታ ማግኘት እንዳለብን መረዳት ከከፋ የህመም ስቃይና የኩላሊት ጉዳት ያድነናል፤ የረጅም ጊዜ ጤናችንንም ይጠብቃል።
የበለጠ መረጃ አሐድኬር ድረገጽ ላይ ያገኛሉ።

https://ahadcare.com/kidney-stones-ethiopia/

ባሉበት ሆነው ሐኪም ማማከር ካስፈለጎት አሐድኬር ላይ ዶክተሮችን ያገኛሉ። 👇
https://ahadcare.com/listing-category/online-doctors/

#አሐድኬር


የኩላሊት ጠጠር በሀገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በስራ ላይ ያሉ እና አምራች የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ሰለባ ያደርጋል። ይህ ከፍተኛ ስቃይ እና የኩ...

የጡት ካንሰርን ቀድሞ በማወቅ የራስን፣ የእናትን፣ የእህትንና የሚስትን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል ያውቃሉ? 🌸ውድ የAhadcare ቤተሰቦችና ኢትዮጵያውያን፤ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ የ...
23/02/2026

የጡት ካንሰርን ቀድሞ በማወቅ የራስን፣ የእናትን፣ የእህትንና የሚስትን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል ያውቃሉ? 🌸

ውድ የAhadcare ቤተሰቦችና ኢትዮጵያውያን፤

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰትና ለህልፈተ ሕይወት ዋነኛ መንስኤ እየሆነ የመጣ በሽታ ነው። ነገር ግን አንድ መልካም ዜና አለን፦ ካንሰሩ ገና በጅምሩ ከተደረሰበት በሕክምና መዳን ይችላል!

አስቀድሞ የማወቅ፣ የመጠንቀቅ ና ትኩረት የመስጠት አስፈለጊነት

🔍 በኢትዮጵያ አዳዲስ በካንሰር ከሚታመሙ ታካሚ እናቶች 32% ያህሉ የካንሰር ዓይነቱ የጡት ካንሰር እንደሆነ፣ እና በካንሰር ከሚሞቱት ውስጥ ከ17% በላይ የሚሆነው ሞት በዚህ አሰቃቂ በሽታ ምክንያት እንደሆነ፤

🔍 እንዲሁም በሽታው ዘግይቶ ከተገኘ ለ5 ዓመት በሂወት የመቆየት ዕድሉን ወደ 22% ዝቅ እንዳደሚያደርገውና ይህ ችግር ከሰሃራ በታች ካሉ ደሃ አገራት በላይ በአገራችን የባሰ መሆኑ፣ ይህም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ባሉ እናቶች ላይ የበለጠ አስከፊ መሆኑን በቅርቡ በአገራችን የተሰራ ጥናት አመላክቷል።

🔍 የጡት ካንሰር በአብዛኛው መጀመሪያ ላይ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ላይኖረው ቢችልም ስር እየሰደደ ሲሄድ ግን ለማዳን የሚያስቸግርና በማስታገሻ መድሃኒት ስሜቱን መቀነስ የማንችለው እጅግ ከፍተኛ የህመም ስቃይና ለአስታማሚም የሚከብድ አስቀያሚ መጥፎ ጠረን ጭምር በመፍጠር ለሞት የሚዳርግ አስከፊ በሽታ ነው።

🔍 ይሁን እንጅ ቀድሞ በማወቅ ይህንን ታሪክ መለወጥ ይቻላል!

ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ቀላል እርምጃዎች ዋናዎቹ፡-

2. በየወሩ እራስዎን ይመርምሩ፡- የወር አበባ በቆመ ከ3ኛው እስከ 5ኛው ባሉ ቀናት ጡትዎን በመስታወት ፊት በመቆም ወይም በሚመች ቦታ በመተኛት ይፈትሹ። (አሃድኬር ድረገጽ ላይ ሙሉ ቅደም ተከተሉን እንዲያነቡ ከዚህ ጽሁፍ ስር መስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ )

3. በባለሙያ ይታዩ፡- እድሜዎት ከ 40 ዓመት በላይ ከሆነ ጡትዎት ጤነኛ ቢመስሎትም በአመት አንዴ በባለሙያ ቼክ ይደረጉ።

3. ምልክቶችን ይለዩ፡- በጡት ላይ አዲስ እብጠት፣ የቆዳ ቀለም መቀየር፣ ወይም የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሳብ፣ ቁስለት፣ ወይም የጡት ጫፍ ፈሳሽ ካዩ በፍጥነት ወደ ሐኪም ይሂዱ።

4. ጤናማ አኗኗርን ይከተሉ፡- የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር፣ ስፖርት መስራት እና ጡትን ማጥባት የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን ከሚቀንሱ ጥንቃቄዎች ዋናዎቹ ናቸው።

በቤትዎ ውስጥ ማድረግ ያለቦት የምርመራ ብልሃት፣ በ ሐኪም ስለሚደረጉ ምርመራዎች እና ስለ ሕክምና አማራጮች የበለጠ መረጃ በአሃድኬር ድረ-ገጽ ላይ ያንብቡ።

👉 ሙሉ ጽሁፉን እዚህ ያንብቡ፡ https://ahadcare.com/breast-cancer-ethiopia/

ይህንን መረጃ ለእናቶችና ለእህቶችዎ በማጋራት ግንዛቤ ይፍጠሩ!

#የጡትካንሰር #ጤና #አሃድኬር World Health Organization (WHO)

የፊንጢጣ ኪንታሮትን መከላከልና በቤት ውስጥ ማከም  እንደሚችሉ ያውቃሉ?
14/02/2026

የፊንጢጣ ኪንታሮትን መከላከልና በቤት ውስጥ ማከም እንደሚችሉ ያውቃሉ?

ኪንታሮት በፊንጢጣ ቱቦ ውስጥ እና ዙሪያ የሚገኙ የደም ስሮች እና ህብረ ህዋሳት ሲያብጡ ወይም ሲቆጡ የሚፈጠር ችግር ነው። በአኗኗር ዘዴ መከላከልና ማከም ይቻላል።

ጤና ይስጥልኝ!  ማንኛውም ሰው በድንገት እነዚህን 4 ምልክቶች ካዬ በአስቸኳይ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ በሐኪም መታየት እንደሚያስፈልግ ያስታውሱ።1. የሆድ ህመም 2. ፈስና ...
01/02/2026

ጤና ይስጥልኝ!

ማንኛውም ሰው በድንገት እነዚህን 4 ምልክቶች ካዬ በአስቸኳይ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ በሐኪም መታየት እንደሚያስፈልግ ያስታውሱ።

1. የሆድ ህመም
2. ፈስና ሰገራ መከልከል
3. የሆድ መነፋት
4. ተደጋጋሚ ትውከት

4ቱ ምልክቶች በድንገት ሲከሰቱ የድንገተኛ አንጀት መዘጋትን ያመለክታሉ። ድንገተኛ የአንጀት መዘጋት ምልክቶች ያጋጠመው ሰው ሰአታትን ሳይሆን ደቂቃዎችን እንዳያባክን ይመከራል።

ቢዘገይ ምን ይፈጠራል? እንዴትስ ሊታከም ይችላል?

ሰፋ ያለ መረጃ 👇👇

https://ahadcare.com/bowel-obstruction/

ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ!






📢 የአንጀት መዘጋት፣ በሜካኒካዊ ወይም ሜካኒካዊ ባልሆነ ምክንያት የተመገብነው ምግብና ለምግብ መፈጨት አስፈላጊ የሆኑ ፈሳሾች መደበኛ የእንሽርሽሪት እንቅስቃሴ ሲቋረጥ የሚከሰት ሲ...

እንኳን ለ 2018 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም ና በጤና አደረሳችሁ!Happy Ethiopian Christmas!
07/01/2026

እንኳን ለ 2018 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም ና በጤና አደረሳችሁ!

Happy Ethiopian Christmas!


Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 02:00 - 21:30
Tuesday 02:00 - 21:30
Wednesday 02:00 - 21:30
Thursday 02:00 - 21:30
Friday 02:00 - 21:30
Saturday 02:00 - 21:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AhadCare - ፩ ኬር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram