ምሳሌ ክሊኒክ Mesale Medical Clinic Plc

ምሳሌ ክሊኒክ Mesale Medical  Clinic Plc Explore the Future of HEALTH
BUILD YOUR FUTURE

Vitamin D
31/05/2024

Vitamin D

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿✝  ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች       በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላምና                 በጤና አደረሳችሁ።በበዓላት ወቅት ዘመድ ከዘመዱ፣ ጓደኛ...
05/05/2024

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

✝ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላምና
በጤና አደረሳችሁ።

በበዓላት ወቅት ዘመድ ከዘመዱ፣ ጓደኛ ከጓደኛው፣ ጎረቤት ከአብሮ አደጉ ብቻም ሳይሆን የቅርቡም የሩቁም "እንኳን አደረሳችሁ" መባባል የተለመደ እና ኢትዮጵያዊነት ውበትን ያላበሰ መልካም ጉርብትናን የሚያጠናክር ነው።

♥ በዓሉ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ፣ የሰላም ፣
የፍቅር ፣ የደስታ የመተሳሰብ እና የአንድነት
እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

💚💛❤️መልካም በዓል💚💛❤️

┈┈┈••✦✦••┈┈┈

Eid Mubarak !!💫
10/04/2024

Eid Mubarak !!💫

የአንገት በላይ ህክምና ክፍልENT Department የአንገት በላይ ህክምና ክፍላችን ለአዎቂዎችም ሆነ ለህፃናት ማንኛውም አይነት የአንገት በላይ ችግሮች ማለትም:-> አለርጂዎች> የጆሮ ኢንፌ...
05/03/2024

የአንገት በላይ ህክምና ክፍል
ENT Department
የአንገት በላይ ህክምና ክፍላችን ለአዎቂዎችም ሆነ ለህፃናት ማንኛውም አይነት የአንገት በላይ ችግሮች ማለትም:-
> አለርጂዎች
> የጆሮ ኢንፌክሽን
> የቶንሲል ህመም
> የጆሮ የመስማት መቀነስ ህመሞች
> የሳይነስ ህመሞች
> የጉሮሮ ህመም
> የምግብ መዋጥ ችግር
> በእንቅልፍ ወቅት የመታፈን ህመም
> የጆሮ፣ የጉሮሮ እንዲሁም የአፍንጫ አከባቢ ቀዶ ህክምና ጎዳዬችን እናመክራለን እንዲሁም በውጪ ሀገር ሆነ በሀገር ውስጥ ህክምናውን እንዲያደርጉ ቦታ እናመቻቻለን ።

📌የስራ ሰዓት:- ዘወትር ሰኞና ቅዳሜ በስራ ከሰዓት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት በ 📞0936659999/ 0913673460 ይደውሉ።🚨
👉ኮተቤ ኮሌጅ አዋሽ ባንክ አካባቢ ስላም ዳቦ ቤት እንገኛለን።
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ.

የወንድ ልጅ ግርዛት Circumcision 📎👉ግርዛት ማለት ቀዶ ህክምናን በመጠቀም የወንድ ልጅን የብልት ጫፍ የሚሸፍነውን አላስፈላጊ የቆዳ ክፍል ማስወገድ ማለት ነው፡፡👉ጥቅሞቹለሽንት ቧንቧ ...
31/01/2024

የወንድ ልጅ ግርዛት Circumcision 📎
👉ግርዛት ማለት ቀዶ ህክምናን በመጠቀም የወንድ ልጅን የብልት ጫፍ የሚሸፍነውን አላስፈላጊ የቆዳ ክፍል ማስወገድ ማለት ነው፡፡
👉ጥቅሞቹ
ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድል ይቀንሳል፡፡
ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል፡፡
ጥሩ የሆነ የወሲብ ፍላጎት እንዲሁም የግንኙነት ህይወት እንዲኖር ይረዳል፡፡
በወንድ ብልት ላይ ሊከሰት ከሚችል ካንሰር በሽታ ይከላከላል፡፡
የብልት ጫፍ ቆዳ ላይ የሚከሰት መቆጣትን ይከላከላል፡፡
የብልት ጫፍ ቆዳ መሸብሸብ እንዲሁም ከልክ በላይ ወደ ፊት በመምጣት ከሚከሰት የሽንት መቋጠር እና ኢንፌክሽንን ይከላከላል፡፡
በቀላሉ የብልት ጫፍ ንጽህናን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
👉የወንድ ልጅ ግርዛት መቼ መከናወን አለበት?
ወንድ ልጅ እንደተወለደ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ግርዛቱን በጤና ተቋም ውስጥ ማከናወን ከላይ የተጠቀሱትን የጤና ጥቅሞች በተሻለ መልኩ ማግኘት ያስችላል ከዚህም በተጨማሪ በቀዶ ጥገና ምክንያት ከሚደርስበት ቁስለት በቶሎ ማገገም እንዲችል ይረዳዋል።ለመዳን ከግርዛቱ በኃላ ከ7 እስከ 10ቀን ይፈጃል።
👉ከግርዛት በኃላ እነዚህን ካስተዋሉ ባለሙያ ያማክሩ📌
ከግርዛቱ በ12 ሰአት ውስጥ የሽንት ሂደት ያልተስተካክለ ከሆነ
ቀጣይነት ያለው መድማት ካለ
ከብልት ጫፍ መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ ከወጣ
ከግርዛቱ በኃላ ቀለበቱ ከሁለት ሳምንት በላይ ሳይወድቅ ከቆየ

፨👉🥼‌ተቋማችን ከ2009 ዓ/ም ከተቋቋመበት ጌዜ ጀምሮ ለህፃናት እና ለአዋቂዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እየሰጠን የሚገኝ ሲሆን አሁንም አገልግሎቱ ለማግኘት የምትፈልጉ ደምበኞች ከታች በተፃፈው አድራሻ እንገኛለን ።💉
ለህክምና ላብራቶሪና አልትራሳውንድ እና ለምክር አገልግሎት በ +251936659999 / +251913673460 ይደውሉ። ኮተቤ ኮሌጅ አዋሽ ባንክ አካባቢ ስላም ዳቦ ቤት አጠገብ እንገኛለን።

የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ | Cleft Lip and Palate የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ በእርግዝና ጊዜ ሕጻኑ በእናቱ ማህጸን ውስጥ ሲያድግ የሚከሰት የፊትና የመነጋገርያ አካላት ትክክለ...
31/01/2024

የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ | Cleft Lip and Palate

የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ በእርግዝና ጊዜ ሕጻኑ በእናቱ ማህጸን ውስጥ ሲያድግ የሚከሰት የፊትና የመነጋገርያ አካላት ትክክለኛ ቅርጽ ይዞ አለማደግ ነው። የከንፈር መሰንጠቅ የላይኛው ከንፈር ሳይገጣጠም ወይም ለሁለት ተፍክሎ መፈጠር ሲሆን የላንቃ መሰንጠቅ ደግሞ የላይኛው የአፍ ጣሪያ ለሁለት ሲሰነጠቅ ማለት ነው።
የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ከላይ ወይም ከታችኛው የአፍ ክፍል አሊያም በሁለቱም ሊከሰት የሚችል የተፈጥሮ የአካል ጉዳት ነው። የከንፈር መሰንጠቅ ከላንቃ ጋር ወይም አለላንቃ በአመት 700 ሕጻናት በአሜሪካን አገር ውስጥ ይጠቃሉ። ይህ መሰንጠቅ ከሴቶች ይልቅ ወንዶችን በሁለት እጥፍ የሚያጠቃ ሲሆን ከዝርያዎች ውስጥ ደግሞ የኤዥያ አገር ዝርያ ያላቸውን፥ ላቲኖችንና የአሜሪካ ተወላጅ የነበሩትን ይበልጥ ያጠቃል። ይህ አይነት ችግር ያለባቸው ልጆች በንግግር እና በመመገብ ጊዜ ችግር ይገጥማቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በመስማት፥ የጆሮ መቁሰል እና የጥርስም ችግር ሊገጥማቸው ይችላል።
ምክንያት (Cause):
አብዛኛውን ጊዜ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ምክንያቶች አይታወቁም። አብዛኛው ተመራመርዎች የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ የሚመጣው ከዘር እና ከአከባቢው ተጽእኖ እንደሆነ ያምናሉ። ወንድሞቹና እህቶቹ፥ ወላጆቹ ወይም ዘመዶቹ እንደዚህ አይነት ችግር ካለባቸው አዲስ በሚወለድ ልጅ ላይ ይህ ችግር የመከሰት እድሉ በጣም ሰፊ ነው። ሌላ ምክንያት ሊሆን የሚችለው እናት በእርግዝና ጊዜ የሚትወስደው መድኃኒት ነው። ከዚህም ሌላ ሕጻኑ በማኅጸን ውስጥ በነበረበት ጊዜ ለቫይረስ ወይም ለአደገኛ ኬሚካል የተጋለጠ ከሆነም ለከንፈርና ለላንቃ መሰንጠቅ ምክንያት ሊሆነው ይችላል።
ከዚህም በተጨማሪ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ በእርግዝና ጊዜ አመጋገብ ሥርዓት አለመጠበቅ፥ ማጨስ፥ እና የስኳር በሽታ ያላባቸው ሴቶች የሚወልዱአቸው ልጆች ለዚህ ጉዳት የመጋለጥ እድላቸው በጣም የሰፋ ነው። ስለዚህ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሴቶች ለማርገዝ ከማቀዳቸው በፊት ወይም ከማርገዛቸው በፊት ከግል የጤና ባላሙያቸው ጋር መወያየት ይጠበቅባቸዋል።
ምልክቶቹ (symptoms):
አንድ ልጅ ከውልደቱ በፊት የሚከሰት የአካል መጓደል ስለሆነ ልጁ ሲወለድ አብዛኛውን ጊዜ የላይኛው ከንፈሩ እስከ አፍንጫው ሥር ድረስ ለሁለት የመከፈልና የአፍ ጣሪያ የሆነው ላይኛው ወይም የታችኛው ለሁለት ተክፍሎ ይታያል። ሌላው የአፍንጫ ቅርጽ መለወጥ፥ የጥርስ መገጣጠም አለመቻል፥ የክብደት መቀነስ፥ የመመገብ ችግር፥ጡት ሲጠባ ወደ አፍንጫ የመግባት፥ በቂ እድገት አለማሳየት፥ ተደጋጋሚ የጆሮ ቁስለትና መናገር አለመቻል ናቸው።
ምርመራ (Exams and Tests):
መሰንጠቅ በሰውነት ቅርጽ ላይ ለውጥ ስለሚያመጣ የከንፈርና የላንቃን መሰንጠቅ በቀላሉ በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ገና በእናቱ ማሕጸን ያለ ልጅ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ እንዳለበት በአልትራሳውንድ ማወቅ ይቻላል። ይህ ካልሆነ ግን ሕጻኑ እንደተወለደ አካላዊ ምርመራ ተደርጎለት የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ ይቻላል። አንዳንድ ጊዜ ምርመራዎች ሌላ ሥርዓቱን ያልጠበቀ የአካል እድገት መኖሩንና አለመኖሩንም ለማወቅ ይጠቅማል።
መከላከያው (Prevention):
የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ በእርግዝና ገና በመጀመረያዎቹ ወራት በጽንሱ ላይ የሚከሰት ሲሆን ከዘር የሚመጣ ከሆነ መከላከል አይቻልም። ነገር ግን ከአከባቢያው ተጽእኖ የሚመጣ ከሆነ ሴቶች በእርግዝና ወራት ለዚህ ጉዳት መነሻ የሆኑትን ነገሮች ላይ በሚያደርጉት ጥንቃቄ መከላከል ይቻላል። ስለዚህ ከእርግዝና በፊት የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን በማረጋገጥ፥ የተመጣጠነ ምግብን በሥርዓቱ በመመገብና ከእርግዝና በፊትና በኃላ የወላጅ ቫይታሚን በመውሰድ፥ በእርግዝና ጊዜ ጤናን ሊጎዱ የሚችሉትን አደጋዎች በማራቅ፥ በእርግዝና ጊዜ ያለ ጤና ባለሙያ ምክር ምንም አይነት መድኃኒት ባለመውሰድ፥ ባለማጨስ፥ ሕገወጥ መድኃኒቶችን አለመጠቀም፥ አልኮል ባለመጠጣት፥ እና ለጨረር የሚያጋልጥ የጤና ምርመራ ባለማድረግ ከዚህ የአካል ጉዳት ጽንሱን መከላከል ይቻላል።
ህክምናው ወይም መድኃንቱ (Medication):
አብዛኛውን ጊዜ ሕጻኑ በ6 ሳምንታትና በ9 ወራት መካከል ሲሆን የቀዶ ህክምና ይደረግለታል። ችግሩ በአፍንጫ አከባቢ ከፍተኛ ጉዳት ካደረስ ወደፊት ቀዶ ህክምናው ሊያስፈልግ ይችላል። ብዙውን ጊዜ የላንቃ መሰንጠቅ ሕጻኑ በአግባቡ መናገር እንዲችል አንድ ዓመት ሲሞላው ሊገጥም ይችላል። አንዳንድ ጊዜ የቀዶ ህምናው እስኪሰራለት ድረስ የሕጻኑን ላንቃ በሰው ሰራሽ ፕላስቲክ በመዝጋት እንዲመገብ ማድረግ ይቻላል። ንግግር እንዲችል የማድረግና የጥርስ ህክምና ክትትል በተደጋጋሚ ያስፈልጋል።
ከዚህም ሌላ ጥርሶችን በተለይም ደግሞ የመንጋጋ ጥርሶችን ለማስተካከል፥ የመንጋጭላዎችን አለመመጣጠን ለማስተካከል፥ የአፍ ቀዶ ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል። ከተበላሹ ጥርሶች ጋርም ሆነ ከመንጋጭላዎች እንድሁም ከድድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የቀዶ ህክምና መከታተል ያስፈልጋል።
ለህክምና ላብራቶሪ አልትራሳውንድ እና ለምክር አገልግሎት በ +251936659999 / +251913673460 ይደውሉ። ኮተቤ ኮሌጅ አዋሽ ባንክ አካባቢ ስላም ዳቦ ቤት አጠገብ እንገኛለን።

የማህጸን ጫፍ ካንሰር  Cervical cancerየማኅጸን ጫፍ ካንሰር በዓለም ዙሪያ በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች አንዱ ነው። በየዓመቱ ከ500,000 በላይ አዳዲስ የማኅጸን ጫፍ ካንሰ...
17/01/2024

የማህጸን ጫፍ ካንሰር Cervical cancer
የማኅጸን ጫፍ ካንሰር በዓለም ዙሪያ በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች አንዱ ነው። በየዓመቱ ከ500,000 በላይ አዳዲስ የማኅጸን ጫፍ ካንሰር እንደሚያዙ ይገመታል። አብዛኛዎቹ ህመሞች የሚከሰቱት ምርመራና ህክምና ውስን በሆነባቸው ታዳጊ ሀገራት ነው። ቅድመ ምርመራ ማድረግ ብሎም አዘውትሮ መመርመር የተሳካ ሕክምና የማግኘት አጋጣሚውን በእጅጉ ሊያሻሽል ይችላል።
ጥቂት ስለማህፀን ጫፍ ካንሰር
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ማለት በማህፀን ጫፍ ላይ ያልተለመደ የህዋስ እድገት ሲከሰትና ይህም በመላው የማህፀን ጫፍ አካባቢ ሲዛመት ነው፡፡
የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
የደም መርጋት
የደም መፍሰስ
ፊስቱላ
የሆድ ድርቀት
የመሽናት ችግር
መካንነት
የውስጣዊ አካል ከጥቅም ውጪ መሆንና የመሳሰሉትን ጉዳቶች በማምጣት የማህፀን በር ካንሰር እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ህመም ነው፡፡
ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽማ የምታውቅ ሴት ሁሉ ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ አጋጣሚ ሊኖራት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ፡-
- በለጋነት ዕድሜ (ከ20 ዓመት እድሜ በታች) የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች፣
- ከተለያዩ ወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች፣
- በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ያጋጠማቸው ሴቶች (ለምሳሌ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ)፣ እንዲሁም
- በአባላዘር በሽታ የተያዙ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
-የማህፀን በር ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች
የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት የህመም ስሜትና ምልክት ሳያሳይ ከ15 እስከ 20 ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡ በሽታው ከተባባሰ በኋላ ግን፡-
- ከወር አበባ ወቅት ውጭ የማህጸን ደም መፍሰስ፣
- የወር አበባ ጊዜ የተራዘመና ከባድ መሆን፣
- የመውለጃ ጊዜ ወይም ዕድሜ ካለፈ በኋላም የደም መፍሰስ ማጋጠም፣
- ያልተለመደ ወይም ለየት ያለ ጠረን ያለው የብልት ፈሳሽ፣
- ድካም፣ የወገብ ህመም፣ ክሳት፣ የሆድ ህመም እና የመሳሰሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡
የማህፀን በር ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ፣ በተጨማሪም
- ከ20 ዓመት ዕድሜ በታች የሚገኙ ሴቶች የማህጸን በራቸው ያልዳበረ በመሆኑ በለጋነት ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ያለመፈጸም፣
- ኤች ፒ ቪ ክትባትን መከተብ፣
- አንድ ለአንድ መወሰን፣
- የአባላዘር በሽታን መከላከል ዋነኞቹ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡
የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራን በጤና ተቋም በማድረግ፣ ተጋላጭነትዎን ይቀንሱ፡፡
በጥር የዓለም የማህጸን ጫፍ ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው ስለሆነም በማህጸን ጫፍ ካንሰር ነፃ የምክር አገልግሎት ስላለ ወደ ክሊኒካችን ይምጡ....
ለህክምና ላብራቶሪ አልትራሳውንድ እና ለምክር አገልግሎት በ +251936659999+251913673460 ይደውሉ። ኮተቤ ኮሌጅ አዋሽ ባንክ አካባቢ ስላም ዳቦ ቤት አጠገብ እንገኛለን።

06/01/2024
Christmas Gifts 🧧🎄
26/12/2023

Christmas Gifts 🧧🎄

በክሊኒክ የሚደረጉት መሰረታዊ የኩላሊት ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸው። ለምንስ ተመረጡ?  1- የግፊት ምርመራ እና የስኳር ምርመራ - ደም ግፊት እና ስኳር ህመም ቀዳሚዎቹ የኩላሊት መስነፍ ም...
26/12/2023

በክሊኒክ የሚደረጉት መሰረታዊ የኩላሊት ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸው። ለምንስ ተመረጡ?

1- የግፊት ምርመራ እና የስኳር ምርመራ - ደም ግፊት እና ስኳር ህመም ቀዳሚዎቹ የኩላሊት መስነፍ ምክንያቶች ስለሆኑ እነዚህን ችግሮች አስቀድሞ ማግኘትና መቆጣጠር የኩላሊት በሽታ የመከሰት እድልዎን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ስለሚያስስችል

2- ሽንት ምርመራ- የኩላሊት መጎዳትን ምልክት ሊሰጠን ይችላል በተለይ ሽንት ላይ ፕሮቲን ከታየ ጠቃሚ መረጃ ነው። በተጨማሪም የሽንት መስመር ኢንፌክሽን መኖሩን ሊያረጋግጥልን ይችላል።

3- የደም ኩላሊት ማጣራት አቅም ምርመራ (Renal Function Test) - ይህ ምርመራ በዋነኛነት የኩላሊትን ማጣራት አቅም ይለካል። የኩላሊት መስነፍ ችግር ካለ መኖሩንና ደረጃውን ይነግረናል።

4- አልትራሳውንድ፦ የሽንት መስመር በጠጠር በእጢ ወይም በሌላ ምክንያት መዘጋቱን፣ ኩላሊቶቹ በእይታ የተጎዱ መሆኑንና አለመሆኑን መለየት ይቻላል።

ውድ ተገልጋዮቻችን እነዚህን ሁሉ ምርመራዎች በሶስት መቶ ብር ብቻ ለገና እና ጥምቀት በስጦታ አበርክተልንዎታል። በስጦታው ይጠቀሙበት እና የኩላሊትዎን ጤና ይፈትሹ።
አድራሻችን - ኮተቤ አካባቢ ዋናው መንገድ ላይ ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13673460
0936659999ያገኙናል ።

ስላልተጠበቀ የጽንስ መቋረጥ ( Unexpected Abortion) ማወቅ ያለብን አንኳር ነጥቦች * የተለያዩ ሀገሮች እና አለማቀፋዊ የጤና ተቋማት በተለያዩ መንገድ  ቢተረጉሙትም በእኛ ሀገር ...
25/10/2023

ስላልተጠበቀ የጽንስ መቋረጥ ( Unexpected Abortion) ማወቅ ያለብን አንኳር ነጥቦች
* የተለያዩ ሀገሮች እና አለማቀፋዊ የጤና ተቋማት በተለያዩ መንገድ ቢተረጉሙትም በእኛ ሀገር ግን የጽንስ መቋረጥ የምንለው ከ 28 የእርግዝና ሳምንት በታች እድሜ ያለው ወይም ክብደቱ ከ 1000 ግራም በታች የሆነ ፅንስ በራሱ ጊዜ ወይንም ሆን ተብሎ ሲቋረጥ ነው ።
* በህክምና ከተረጋገጡ እርግዝናዎች ውስጥ እስከ 15% የሚሆነው በራሱ ጊዜ እንደሚቋረጥ ጥናቶች ያሳያሉ።
መንስኤዎቹ ምን ምን ናቸው?
* ያልተጠበቀ የጽንስ መቋረጥ መንስኤዎች ውርጃ እንደሚከሰትበት ጊዜ ይለያያሉ
- በተለይ በመጀመሪያዎቹ 3 የእርግዝና ወራት ውስጥ በራሱ ጊዜ የሚከሰት የጽንስ መቋረጥ ከግማሽ በላይ የሚፈጠረው በክሮሞዞም የአፈጣጠር ችግር ነው ።
* ከዚህ በተጨማሪ የጽንስ መቋረጥ ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን ከነዚህም መካከል :⁠-
- ልዩ ልዩ ኢንፌክሽኖች
- የማህጸን የአፈጣጠር ችግር
- የማህጸን ጫፍ በበቂ ሆኔታ ያለመዘጋት ችግር
- እንደ ስኳር ፣ የእንቅርት ሆርሞን ከመጠን በላይ መብዛት ወይም ማነስ ፣ ከመጠን በላይ ክብደት መጨመር ውፍረት፣ ሾተላይ የመሳሰሉ የጤና ችግሮች እንድሁም ተለያዩ መድሀኒቶች እና አካላዊ ጥቃቶች..... ወዘተ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።
ምን ምን አይነት ምልክቶች አሉት?
- ለተወሰኑ ወራት የወር አበባ መቅረት እና ከዚህ በኋላ በብልት የሚወጣ የደም መፍሰስ እና የሆድ ቁርጠት ወይም ወደ ታች የመጫን ስሜት
- እንደ አይነቱ እና እንደ ፈሰሰው የደም መጠን የተቆራረጠ እና ስጋ የመሰለ ነገር መውጣት፣ የእንሽርት ውሀ መፍሰስ፣ ራስ ምታት ወይንም ማዞር ፣ ድካም ድካም ማለት ፣ ትኩሳት ፣ ከማህፀን የሚወጣ ሽታ ያለው ፈሳሽ ... ወዘተ የመሳሰሉ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላሉ።
ምን ምን አይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ አለብን?
- በመጀመርያ የጤና ባለሙያዎችን በማማከር የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም ያልተፈለገ እና ያልታቀደ እርግዝናን መከላከል
- ባጋጣሚ ያልተፈለገ እርግዝና ከተፈጠረ አሁንም በጊዜው የጤና ባለሙያዎችን ማማከር እና ያለ ህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ምንም አይነት ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ የጽንስ ማቋረጫ መድሀኒቶችንም ሆነ ዘዴወችን አለመጠቀም።
- ከላይ የተዘረዘሩት የጽንስ መቋረጥ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ በአቅራቢያ ወደ የሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማግኘት
ህክምናው ምንድነው?
* የሚሰጠው ህክምና እንደ ሁኔታው አይነት እና ያስከተለው ተያያዥ የጤና ችግር የለያያል። ለምሳሌ :⁠-
- ክትትል ብቻ ማድረግ(expectant management)
- ማህፀንን መጥረግ ወይም መድሀኒት መስጠት
- የደም ማነስ ካለ እንደየደረጃው የደም ማነስ ክኒን ወይም ደም መስጠት
- እናትዮዋ ሾተላይ ከሆነች የሾተላይ መድሀኒትን መስጠት
- ኢንፌክሽን ካለ ኢንፌክሽኑን ማከም
- የህመም ማስታገሻዎችን መስጠት
- ስለጽንስ መቋረጥ በቂ ግንዛቤ እንድኖር ማስተማር እና ሎሎች የስነ ተዋልዶ አገልግሎቶችን መስጠት ዋና ዋናዎቹ ናቸው
ለህክምና ላብራቶሪ አልትራሳውንድ እና ለምክር አገልግሎት በ +251936659999+251913673460 ይደውሉ። ኮተቤ ኮሌጅ አዋሽ ባንክ አካባቢ ስላም ዳቦ ቤት አጠገብ እንገኛለን።

Address

Addis Abeba

Telephone

+251936659999

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምሳሌ ክሊኒክ Mesale Medical Clinic Plc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ምሳሌ ክሊኒክ Mesale Medical Clinic Plc:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram