Fama Medium Clinic Halaba

Fama Medium Clinic Halaba Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fama Medium Clinic Halaba, Medical and health, Alaba K'ulito.

10/03/2025

መላዉ የኢስላምና እምነት ተከታዮች ረመዳን ከርህም

*ፋማ medium clinic ሃላባ

16/06/2024

ኢድ _ሙባረክ
Fama medium clinic halaba

ስለ ህጻናት ቁርጠት( Infantile colic) ወላጆች ማወቅ ያለባቸው 🔻🔻አስር ነጥቦች‼️***📌ወላጆችን በተደጋጋሚ ሀኪምን 🩺እንዲጎበኙ ምክኒያት ከሆኑ  ህመሞች አንዱ በተለምዶ ቁርጠት (...
17/01/2024

ስለ ህጻናት ቁርጠት( Infantile colic) ወላጆች ማወቅ ያለባቸው 🔻🔻አስር ነጥቦች‼️
***

📌ወላጆችን በተደጋጋሚ ሀኪምን 🩺እንዲጎበኙ ምክኒያት ከሆኑ ህመሞች አንዱ በተለምዶ ቁርጠት (Infantile colic) የሚባለው ነው። ቁርጠት በተወለዱ በመጀመሪው ወር በጨቅላ ህጻናት ላይ የሚከሰት ሲሆን በቀን ለሶስት ሰአትና ከዛ በላይ ፣ በሳምንት ለሶስት ቀናትና ከዛ በላይ እንዲሁም ለሶስት ሳምንታትና ከዛ በላይ የሚቆይ የለቅሶና መነጫነጭ ስሜት ነው። ስለዚሁ ህመም ወላጆች ማወቅ ያሉባቸው 10 ነጥቦችን በዛሬው ጽሁፍ ይዤ ቀርቤያለሁ እስከመጨረሻው አንብቡት።

🔹1. የህፃናት ቁርጠት (infantile colic) መንስኤው ምንድን ነው?

▶️በመንስኤው ላይ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ ወጥ የሆነ መግባባት ባይኖርም የአንጀትና ባጠቃላይ የስርአተ ልመት ኢንዛይሞች ከአለመጎልመስ ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ ይታሰባል።

🔹2. ህመሙ እስከ መቼ ይቀጥላል ?

▶️በአብዛኛው ህጻናት ዘንድ ህመሙ እስከ ሶስት ወር የሚቆይ ሲሆን አልፎ አልፎ ግን በጣም ጥቂት ህጻናት ላይ እስከ ዘጠኝ ወር ሊዘልቅ ይችላል።

🔷3. የምታጠባ እናት ከምትበላው ምግብ ጋር የቁርጠት ህመም ምን ግንኙነት አለው?

▶️የምታጠባ እናት ቡና፣ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች ወይም የላም ወተት ብትቀንስ ቁርጠት ላለባቸው ህፃናትን ቁርጠቱ እንዲቀንስላቸው ሊያግዝ ይችላል።

🔹 4. የጣሳ ወተትን በመቀየር ቁርጠትን መከላከል ይቻላል?

▶️ህጻኑ የጣሳ ወተት ሲወስድ የመነጫነጭና ማልቀስ ምልክት ካለው የጣሳ ወተቱን ቢቀየር ይመከራል ።

🔹5. ቁርጠት ላለበት ልጅ 💊መድሀኒት ቢሰጠው ለህመሙ ይረዳዋል?

▶️የቁርጠት መንስኤ የተለያዩ ምክኒያቶች በመሆናቸው እንዲሁም የህመሙ ባህሪ ከልጅ ልጅ ስለሚለያይ ለቁርጠት ወጥ የሆነ ህክምና የለውም። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት መድሀኒት መስጠት ለቁርጠት ብዙ ጠቀሜታ አይሰጥም።

🔹6. በወላጆች በኩል ቁርጠቱን ለማስታገስ ምን ቢደረግ ይመከራል?

▶️ህጻኑን ዘና እንዲልና እንዲረጋጋ የሚያደርጉ ለምሳሌ ገላን በሙቅ ውሀ ማጠብ፣ ለስለስ ባለ ብርድ ልብስ መጠቅለና፣ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ህጻኑን መወዝወዝ( rocking motion)፣ ለስላሳ ሙዚቃ መክፈትና እሹሹ እያሉ ማረጋጋት ህጻኑ ህመሙ ቀለል እንዲልለት ይረዳል።

🔹7. ለረጅም ሰአት ህጻኑ በማልቀሱ ምን ጉዳት ያመጣበታል?
▶️ህፃኑ ለረጅም ሰአት በማልቀሱ የሚመጣ ጉዳት የለም። ህጻኑ የአካል ጥንካሬው ጥሩ ከሆነ፣ በደምብ የሚጠባ እንዲሁም በጥሩ የእድገት ደረጃ ላይ ካለና ቆዳ ከለሩም ካልተለወጠ፣ የ ትኩሳት ምልክት ካልታየበት ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ቢያለቅስም ያን ያህል አሳሳቢ አይደለም። ስለዚህ ወላጆች ህፃናትን ለማረጋጋት ከሚጠቀሙበት መንገዶች ውጪ ከ አምስት እስከ አስር ደቂቃ ህፃኑ እንዲያለቅሱ በመተው ራሱን በራሱ እንዲያረጋጋ ማድረግ ይቻላል ።

🔹8. ቁርጠቱ ከሌላ ህመመ ጋር አለመያያዙን በምን ምርመራ ማወቅ ይቻላል?

▶️ለቁርጠት የሚደረግ ምርመራ የለም። ነገር ግን ቁርጠቱ ሲከሰት ህፃኑ በ ህፃናት ህክምና ባለሙያ እንዲታይ በማድረግ የችግሩ መንስኤ ቁርጠት ወይም ሌላ ህመም መሆኑን ማወቅ ይቻላል። ህጻኑ በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ከታየ በኋላ ከአንጀት ጋር የሚያያዝ ችግርን ከተጠረጠረ ራጅ ወይም አልትራሳውንድ ምርመራ እንደሁኔታው ሊታዘዝ ይችላል።

🔹9. ቁርጠት የያዘውን ህፃን በሀኪም እንዲታይ ማድረግ ያለብን መቼ ነው?

▶️አብዛኞቹ የቁርጠት ህመሞች በተደጋጋሚ ጊዜ ሰአት ለይተው የሚከሰቱ ናቸው። ለምሳሌ ቁር

ingrown nail(የጥፍር ቆዳ ውስጥ መግባት) 👉  በብዛት የሚከሰተው የእግር አውራጣት ጥፍር ላይ ቢሆንም ማንኛውንም ጥፍር ሊያጠቃ ይችላል                   ምክንያቶች  👉  ጠ...
17/01/2024

ingrown nail(የጥፍር ቆዳ ውስጥ መግባት)
👉 በብዛት የሚከሰተው የእግር አውራጣት ጥፍር ላይ ቢሆንም ማንኛውንም ጥፍር ሊያጠቃ ይችላል
ምክንያቶች
👉 ጠባብ ጫማ ማድረግ እና ጥፍርን በአግባቡ ያለመቁረጥ ዋናወቹ ናቸው
👉 በተጨማሪም አደጋ እና ጥፍር ከጣት አኳያ ትልቅ ከሆነ ሊያስከትሉ ይችላሉ
ምልክት
👉 መቅላት ማበጥ እና ህመም ይኖረዋል
👉 ኢንፌክችን ፈጥሮ መግል ሊይዝ ይችላል
ህክምና
👉 ሞቅ ባለ ውሀ ለተወሰኑ ደቂቃወች በቀን ከ3-4 ጊዜ መዘፍዘፍና ማድረቅ
👉 ምቾት ያለው ጠባብ የሆነ ጫማ ማድረግ
👉 የህመም ማስታገሻ መውሰድ
👉 ጥፍሩን ቀስ አርጎ አንስቶ በጥፍሩ እና በቆዳው መሀል ጥጥ መጨመር:: ጥጡን በየቀኑ መቀየር
👉 በቀዶ ህክምና ማስወጣት: በክሊኒካችን ቀዶ ህክምናው ስላለ መምጣት ይችላሉ

Eman wegaretin elishone yayowFAMA MEDIUM CLINIC HALABA
13/01/2024

Eman wegaretin elishone yayow

FAMA MEDIUM CLINIC HALABA

በድጋም enikuan lazeman malawecha la sera Beal beslm aderesachw
12/01/2024

በድጋም enikuan lazeman malawecha la sera Beal beslm aderesachw

Eman wegaretin elishone
12/01/2024

Eman wegaretin elishone

 #የትርፍ አንጀት ሕመምምክንያቱየትርፍ አንጀት በሽታ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው የትርፍ አንጀቱ በሰገራ፥ በሌላ እንግዳ አካል ወይም በካንሰር ስዘጋ ነው። የትርፍ አንጀት ሲቆስል ስለሚያብጥ የሚ...
19/10/2023

#የትርፍ አንጀት ሕመም

ምክንያቱ

የትርፍ አንጀት በሽታ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው የትርፍ አንጀቱ በሰገራ፥ በሌላ እንግዳ አካል ወይም በካንሰር ስዘጋ ነው። የትርፍ አንጀት ሲቆስል ስለሚያብጥ የሚዘጋው በቁስለትም ሊሆን ይችላል።
በሽታው የሚከሰተው ባክተሪያዎች የትርፍ አንጀትን ግድግዳ ሲወሩትና ሲያቆስሉት ነው።

ምልክቶቹ

የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች በእርግጥ የህመሙን ስሜት ቦታ ለማመልከት አስቸጋር ቢሆንም በእምብርት አከባቢ የህመም ስሜት መሰማት፥ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፥ የሆድ ህመም እንደጀመረ ማቅለሽለሽና ማስታወክ፥ ከ38 እስከ 39.2 ድግር ሲሸልስ የሚደርስ የሰውነት ሙቀት መጨመር፥ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት፥ እና ተቅማጥ ጥቅቶቹ ናቸው።

ምርመራው

የትርፍ አንጀት በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለዋወጠ ስለሆነ ምርመራውን ለማካሔድ እጅግ አስቸጋር እየሆነ ነው። በሽታውን ለመመርመር ብዙ ጊዜ የጤና ባለሙያው ምልክቶቹን በማየት፥ የጤንነት ሁኔታውን ከበሽተኛው በመጠየቅና የሆድ ምርመራ በማድረግ ሊያውቅ ይችላል። ምርመራውም የህመሙን ሁኔታ ለማወቅ በሽተኛውን የሚያመው አከባቢ ጫን በማለት የአካላዊ ምርመራ በማድረግ፥ የበሽተኛው ሰውነት መመረዙን የሚያሳዩ ከፍተኛ ነጭ የደም ሴል በብዛት መኖሩን የደም ምርመራ በማድረግ፥ እና የሽንት ምርመራ በማድረግ ማወቅ ይቻላል።

መከላከያው

በአብዛኛው ከፍተኛ የሆነ ቃጫነት ያለበትን ምግብ በብዛት በማይመገቡ አገሮች ውስጥ የትርፍ አንጀት በሽታ አናሳ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ለምን እንደሆነ በእርግጥ አይታወቅም፤ ሆኖም ግን እንደ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት ከፍተኛ ቃጫነት ያለበት ምግብ ሰገራችንን ስለሚያለሰልሰው፥ በትርፍ እንጀት ሄደው መወተፍን ስለሚቀንስ ሊሆን ይችላል። ቃጫነት ያለባቸው ምግቦችም ሁሉም የአገዳ እህሎች፥ ስንዴ፥ ሩዝ እና ፓስታ፥ እንደ ካሮት ያሉ የሥራሥር አትክልቶች፥ እና ፍራፍሬዎች ናቸው። እነዚህን ምግቦች ማዘውተር የትርፍ አንጀት በሽታን ለመከላከል ይጠቅማል::

Fama Medium Clinic Halaba

Coming Soon
09/10/2023

Coming Soon

Address

Alaba K'ulito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fama Medium Clinic Halaba posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share