Minch Medium Clinic

Minch Medium Clinic Private Medium Clinic

04/05/2024
16/05/2022
16/05/2022

Vaccines accompany us through different stages of our lives and protect against:
Cervical cancer
Cholera
COVID-19
Diphtheria
Ebola
Hep B
HPV
Influenza
Japanese encephalitis
Malaria
Measles
Meningitis
Mumps
Pertussis
Pneumonia
Polio
Rabies
Rotavirus
Rubella
Tetanus
Typhoid
Varicella
Yellow Fever

08/05/2022
08/05/2022

የተከበራችሁ የሃገራችን ነርሶች እንኳን ለ 2014/2022 ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን አደረሳችሁ!

በቅድሚያ እንኳን ለ 2014/2022 ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን አደረሳችሁ እንላለን፡፡ የዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን (ሜይ 12) በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንቦት 4 2014 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ May12/ 2022) የዘመናዊ ነርስነት ሙያ መስራች የሆነችውን የፍሎረንስ ናይቲንጌልን የልደት በዓል መሰረት በማድረግ ይከበራል፡፡ ይህንኑ በዓል የኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር በየዓመቱ የሚያከብር ሲሆን የዘንድሮው መሪ ቃል “A Voice to Lead - Invest in Nursing and respect rights to secure global health” የሚል ሲሆን፤ የዓለማችንን ጤና ለማሻሻል & ነርሶችን ማብቃት እና መብትን ማክበር፤ አስፈላጊ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ማህበሩ ይህንን በዓል የሚያከብረው የነርስነት አገልግሎት በሚሻሻለልበት መንገድ ላይ ያተኮሩ በማድረግ እና ስለ ጤና አገልግሎት መሻሻል በመገናኛ ብዙሃን ለህብረተሰቡ በማስተላለፍ ነው፡፡
የኢትዮጰያ ነርሶች ማኅበር?
የኢትዮጰያ ነርሶች ማኅበር ማነው? መች ተጀመረ ? ስንት አባል አለው? የት የት ተወካይ አለው? ምን ስራዎችን ባለፈው ዓመት ሰራ? አሁናዊ አቋሙ ምን ይመስላል፣ አስቻይና አዳጋች ሁኔታዎች ምን ምን ነገሮች አሉ? በቀጣይ እና በውይይት የሚዳብር ሲሆን ከሚላኩ ሰነዶች መረዳትም ይቻለል፡፡ ነገር ግን የዚህ በዓል አላማ ነርሶችን ማመስገን እና ክብር መስጠት ስለሆነ በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀ መልዕክት ነው፡፡
ለምን እና እንዴት ይከበር?
ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን በዓለም ደረጃ ነርሶችን ቁርጠኝነት፣ ራስን መስጠት እና አስተዋፆዎችን ዕውቅና እና ማመስገኛ ቀን ነው፡፡ የሚከበረውም በዓለም ደረጃ ዘመናዊ ነርሲንግ እንዲያብብ ትልቅ ሚና በመነበራት እና የዘመናዊ ነርሲንግ እናት በምትባለው እንግሊዛዊት ፍሎሬንስ ናይንትንጌል የልደት ቀን እንዲከበር በተወሰነው መሰረት ሁሌም ግንቦት 4 ወይም ሜይ 12 ይከበራል፡፡
የዘንድሮ የማክበሪያ ርዕስ ወይም አበይት መልክት ምንድነው?
የ2022 መልዕክት የሚለው ‘Nurses: A Voice to Lead - Invest in Nursing and respect rights to secure global health. በጥሬ ትርጉሙ ነርሶች የመሪነት ድምፅ፤ የዓለማችንን ጤና ለማሻሻል ነርሶችን ማብቃት እና መብትን ማክበር የሚል ነው፡፡ በህም ርዕስ ለማስተላፍ የተሞከሩት አበይት ሀሳቦች እንደሚከተለው ተብሯርቷል፡፡
1. ነርሶች የለውጥ እና የመሻሻል ድምፅ እና ጉልበት ናቸው፡፡ ይህም ሲባል ነርሶች ካላቸው የሥራ ሚና እና ከሚጫወቱት ወሳኝ ሚና ነርሶችን ሳይዙ ለውጥ ዘበት መሆኑን ለማሳየት እና ሁሉም አካላት ለነርሶች እና ለአስተዋፆአቸው ክብርና ዕውቅና መስጠት እንዳለበት ለማጠየቅ የተጠቀሰ ነው፡፡
2. ለነርሲንግ (አግልግሎት) ላይ መዋለ ነዋይ ማፍስ ለአለም የጤና መጠበቅ፡፡ ነርሲንግ ለዓለም ጤና መጠበቅ ካለው አስዋፅዎ አንፃር ተገበውን የበጀት እና ሀብት ምደባ በማድርግ አስፈላጊ ነው ይገባልም ለማለት ነው
3. ለነርሲንግ ክብርና መብት መጠበቅ ለአለም የጤና መጠበቅ፡፡ ለነርሲንግ እና ነርሶች ተገቢውን ቦታ እና ዕውቅና መስጠት ለዓለም ጤና መጠበቅ የማይተካ ሚና አለው ፡፡
መቼ መከበር ተጀመረ
በዓለም አቀፍ የነርሶች ካውንስል1965 ቢጀመርም ወጥ ሆና የተጀመረው በ1974 በሜይ 12 ነበር፡፡
እንዴት ይከበራል የዓለም አቀፍ ልምዶች
በተለያዩ አገራት በተለያየ ልምድ የሚከበር ሲሆን የሚከተሉት በአብዛኛው የዓለም አገራት እና በእኛም አገር ምናከብርበት ልምድ አለ፡፡
1. የማክበሪያ ማዕቀፍ(ኪት) በማዘጋጀት፡፡ ይህም ለነርሶች እና ሌሎች መሰረታዊ የሙያ መረጃዎችን፣ የዓመቱ መልዕክቶችን በማብራራት ለነርሶች ተገቢው ትኩረት እና ክብር እንዲሰጣቸው ማድርግ የሚያችል መረጃ መሰነድ
2. ለምሳሌ በእንግሊዝ ሻማ ማብራትና የሻማ ቅብብሎሽ መርሃግብር ማድርግ፡፡ ይህም ያለውን የዕውቀትና ክህሎች ቅብብሎሽን ለማጠየቅ እና ለመዘከር ነው
3. በጎ ስራዎችን በመስራት ማለትም ደም በመለገስ፣ ምንዱባንን በመጎብኘት፣ የገንዘብ ልገሳ በማድርግ፣ ነፃ አገልግሎት በመስጠት፣ የደም ግፊት መጠን በአውራ መንገዶች ላይ በመለካት
4. የሙያውን በጎ አስተዋፆ ለመዘከር ኬክ ቆረሳ፣ ሻማ ማብራት፣ የዕግር ጉዞ፣ ቃለ መሃላ መደሻ መድርግን
5. በተመረጡ እና በተወሰኑ ርዕሶች ላይ የፓነል ውይይት በማድርግ ትኩረት እና ሀብትን በማሰባሰብ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ በጎ ተፅኖወችን መፍጠር
6. አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶችን በማድርግ ቀኑን አስቦ መዋል
7. የመስሪያ ቦታዎችን ቀኑን በሚዘክሩ ውብ በሆኑ መልዕክቶች በማስዋብ ነርሶችን ማመስገን
8. የሻማ ምሽት በማድርግ ለሙያው ጥብቅና መቆም የሚያስችሉ መልክቶችን ማስተላለፍ
በመሆኑም የዘንድሮውን የ2014ዓ.ም ክብር በዓል በሚከበርበት ወቅት የሚከቱልትን ወሳኝ ግቦች ማሳካት እንዲችል መቀረፅ እንዳለበት የኢትዮጵያ ነርሶች ማኅበር ምክሩን ይለግሳል፡፡
1. መርሃ ግብሩ ቢበዛ ከ2 እስከ 3ሰዓት ያልበለጠ የአዳራሽ መርሃ ግብር ቢሆን
2. በሁሉም ዝግጅት ላይ ባለ ድርሻ አካላት፣ የቅርብ ሀላፊዎች፣ በጎ ተፅኖ ፈጣሪ ሰዎች ባሉበት ቢሆን
3. አጠቃላይ ትኩረቱ ነርሶችን ማመስገን እና የነርሲንግ ሙያ አስተዋፅዎችን በመዘከር ላይ ያተኮረ ቢሆን
4. የሚከበረው በተቋም ደረጃ ያለውን የሥራ አካባቢ ባህሪያት ያገናዘበ፣ ያለውን አቅምና አስቻይ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡
5. ከተቻለ በጎ ላደረጉ፣ ጡረታ ለወጡ ወይም ለሚወጡ ነርሶች ዕውቅና እና ጋቢ/ካባ (እንደየአካባቢዉ የሚቀየር) የማልበስ ዝግጅት ቢኖር
6. ከጤና ተቋም ውጪ በመገድ ላይ ሙያውን የሚሰብኩ እና በጎ አስተዋጾችን የሚያዘክሩ ባነሮች በራሪ ወረቀቶችን በመለጠፍና፣ በመበተን ማክበር ቢቻል፡፡ ይህም በየደረጃውን ካሉ የአስተዳደር አካላት ዕውቅና እና ፍቃድ በመጠየቅ እንዲሆን እንመክራለን፡፡
በመሆኑም ይህንን በዓል በተለያየ የሃገራችን ክፍል የምትገኙ የማህበራችን ቅርንጫፎች፣ ቻፕተሮች፣ ዴስኮች እና አባለት ከላይ ከተጠቀሱት መርሃግበሮች የምትችሉትን በማድረግ ሙሉ ሳምነቱን መ/ቤቱ በአሉን በማክበር ሙያችንን ተፅእኖ ፈጣሪነቱን ለማሀበረሰቡ አናሳይ!

በድጋሜ እንኳን ለ 2014/2022 ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን አደረሳችሁ!

ከሠላምታ ጋር

ታፈሰ በቀለ
ፕረዘደንት

08/05/2022

Do you know Vitamin B12 deficiency can be fatal?

Vitamin B12 is needed for nerve tissue health, brain function, and the production of red blood cells.

Lifotronic offers rapid fully automated ECLIA detection of VB12 with reliable performance. Let's test to be aware!

Check out the infographic below to learn more about the manifestations of lacking Vitamin B12.

12/04/2022

Address

Arba Minich Gamo Zone
Arba Minch'
NONE

Telephone

+251913481031

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Minch Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Minch Medium Clinic:

Share