Nech Sar Hospital / ነጭሳር ሆስፒታል አርባምንጭ

Nech Sar Hospital / ነጭሳር ሆስፒታል አርባምንጭ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nech Sar Hospital / ነጭሳር ሆስፒታል አርባምንጭ, Hospital, Arba Minch'.

ከታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ ቦታዎች መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳደሩ።
12/05/2026

ከታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ ቦታዎች መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳደሩ።

07/05/2026

የእግር እብጠት

ስትሮክ (Stroke)ስትሮክ (Stroke) ወይም የጭንቅላት ደም ዝውውር መቋረጥ የሚከሰተው ወደ ጭንቅላት ደም የሚያደርሱ የደም ስሮች ሲዘጉ ወይም ሲፈነዱ ነው። በዚህ ጊዜ የጭንቅላት ክፍሎች...
06/05/2026

ስትሮክ (Stroke)
ስትሮክ (Stroke) ወይም የጭንቅላት ደም ዝውውር መቋረጥ የሚከሰተው ወደ ጭንቅላት ደም የሚያደርሱ የደም ስሮች ሲዘጉ ወይም ሲፈነዱ ነው። በዚህ ጊዜ የጭንቅላት ክፍሎች በቂ ኦክስጅንና ምግብ ስለማያገኙ የጭንቅላት ሴሎች መሞት ይጀምራሉ።
ይህ የጤና እክል በአፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገለት ለዘላቂ የአካል ጉዳት ወይም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
የስትሮክ አይነቶች
• በደም መርጋት የሚከሰት (Ischemic Stroke): ወደ ጭንቅላት የሚሄድ የደም ስር በደም መርጋት ምክንያት ሲዘጋ ይከሰታል። በአብዛኛው (80%) ስትሮክ በዚህ አይነት የሚከሰት ነው።
• በደም መፍሰስ የሚከሰት (Hemorrhagic Stroke): በጭንቅላት ውስጥ ያለ የደም ስር ሲፈነዳና ደም ወደ ጭንቅላት ሲፈስ ይከሰታል።
• ጊዜያዊ የስትሮክ ምልክት (TIA): ለጥቂት ደቂቃዎች የሚቆይና ወደፊት ለሚመጣ ከባድ ስትሮክ እንደ ማስጠንቀቂያ የሚታይ ነው።
ዋና ዋና ምልክቶች (FAST)
ስትሮክን በፍጥነት ለመለየት የሚከተሉትን ምልክቶች ያስተውሉ፡
• ፊት (Face): የፊት መዛባት ወይም በአንድ በኩል ስንጥቅ ማለት።
• እጅ (Arms): እጅን ወደ ላይ ሲያነሱ አንዱ እጅ የመዛል ወይም የመውደቅ ስሜት።
• ንግግር (Speech): ንግግር መጎርነን ወይም ግልጽ ያልሆነ ንግግር።
• ሰዓት (Time): እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
የስትሮክ ህክምና
የስትሮክ ህክምና እንደ አይነቱና እንደ ደረሰበት ጉዳት ይለያያል፦
• አስቸኳይ ህክምና (Emergency Treatment):
• በደም መርጋት የመጣ ከሆነ የረጋውን ደም የሚያቀልጡ መድኃኒቶች (በመጀመሪያዎቹ 3-4 ሰዓታት ውስጥ ከተሰጠ ውጤታማ ነው)።
• በደም መፍሰስ የመጣ ከሆነ ደሙን ለማቆም የሚረዱ መድኃኒቶች ወይም ቀዶ ጥገና።
• ተጓዳኝ ህክምናዎች:
• የደም ግፊትንና የደም ስኳርን መቆጣጠር።
• የደም መርጋትን የሚከላከሉ መድኃኒቶች (እንደ አስፕሪን ያሉ)።
• ከስትሮክ በኋላ የሚደረግ ማገገሚያ (Rehabilitation):
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (Physiotherapy): የተዳከሙ የሰውነት ክፍሎችን ለማንቀሳቀስ።
• የንግግር ህክምና (Speech Therapy): የመናገር ችግር ካለ ለማስተካከል።
መከላከያ መንገዶች
• የደም ግፊትን ዘወትር መቆጣጠር።
• ጤናማ አመጋገብ (ጨውና ቅባት መቀነስ)።
• አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ።
• ከሲጋራና ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት መቆጠብ።
• የስኳርና የኮሌስትሮል መጠንን መከታተል።
ማሳሰቢያ: ስትሮክ የሰከንዶች ጉዳይ ስለሆነ ምልክቶቹ ሲታዩ ወደ ቅርብ ሆስፒታል መሄድ ወሳኝ ነው።

ቶንሲል፦ ከቀላል የጉሮሮ ህመም እስከ ልብ ህመም! ማወቅ ያለብን ሳይንሳዊ እውነታዎች 🧠ቶንሲል (Tonsillitis) በጉሮሯችን መጨረሻ ግራና ቀኝ የሚገኙት ሊምፍ ኖዶች (Lymph nodes)...
27/04/2026

ቶንሲል፦ ከቀላል የጉሮሮ ህመም እስከ ልብ ህመም! ማወቅ ያለብን ሳይንሳዊ እውነታዎች 🧠

ቶንሲል (Tonsillitis) በጉሮሯችን መጨረሻ ግራና ቀኝ የሚገኙት ሊምፍ ኖዶች (Lymph nodes) በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ምክንያት ሲቆጡ የሚፈጠር የጤና እክል ነው። ብዙዎቻችን እንደ ተራ ህመም ብናየውም፣ አያያዛችን ካልተስተካከለ ግን ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል።

1. ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
የጉሮሮ መቁሰል እና ምግብ ለመዋጥ መቸገር።

የቶንሲል እብጠት፣ መቅላት እና ነጭ መግል መሰል ነጥቦች መታየት።

ከፍተኛ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት።

የራስ ምታት፣ የጆሮ ህመም እና የአንገት ስር እጢዎች ማበጥ።

2. መንስኤዎቹ እና ተጋላጭነት
ቫይረስ፦ አብዛኛው የቶንሲል ህመም በቫይረስ የሚመጣ ሲሆን በራሱ ጊዜ ይሻላል።

ባክቴሪያ (Strep Throat)፦ የግድ በሃኪም የታዘዘ የአንቲባዮቲክ ህክምና ይፈልጋል።

እድሜ፦ ከ5-15 አመት ያሉ ታዳጊዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

ዘር ውርስ (Genetics)፦ ተደጋጋሚ የቶንሲል ህመም በቤተሰብ የመዘዋወር ባህሪ አለው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለተደጋጋሚ ቶንሲል መያዝ 62% የሚሆነው ምክንያት ከዘር ውርስ ጋር የተያያዘ ነው።

3. በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሳይንሳዊ መፍትሄዎች (Proven Home Remedies)
ቶንሲል ገና ሲጀምር ወይም በቫይረስ ምክንያት የመጣ ከሆነ እነዚህን በማድረግ ህመሙን ማስታገስ ይቻላል፦

የጨው ውሃ መጉመጥመጥ፦ ለብ ባለ ውሃ ላይ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው ጨምሮ መጉመጥመጥ ኢንፌክሽኑን ይቀንሳል።

ማርና ዝንጅብል፦ ማር ተፈጥሯዊ የባክቴሪያ መከላከያ (Antibacterial) ሲሆን፣ ዝንጅብል ደግሞ እብጠትን የመቀነስ (Anti-inflammatory) አቅም አለው።

ጥሬ ነጭ ሽንኩርት፦ ነጭ ሽንኩርት "Allicin" የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ባክቴሪያን ለመዋጋት ይረዳል። (በጥሬው ማኘክ ወይም በሻይ መልክ መጠጣት)።

እርጥበትን መጠበቅ፦ ሾርባ፣ ሞቅ ያለ ሻይ እና በቂ ውሃ መጠጣት ጉሮሮ እንዳይደርቅና ህመሙ እንዲቀንስ ይረዳል።

አፕል ሳይደር ቪኔጋር (ACV)፦ በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ኤሲቪ ጨምሮ መጉመጥመጥ የጉሮሮን አሲድነት በማመጣጠን ባክቴሪያ እንዳይራባ ያደርጋል።

4. ቶንሲል በትክክል ካልታከመ ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎች
የልብ እና የመገጣጠሚያ ህመም (Rheumatic Fever)፦ ባክቴሪያው የልብ ቫልቭን በማጥቃት ለዘላቂ የልብ ህመም ሊዳርግ ይችላል።

የኩላሊት መቆጣት (Kidney Inflammation)፦ የኩላሊት ስራን በማስተጓጎል ለደም ግፊትና ለሽንት መጥቆር ምክንያት ይሆናል።

የመግል መከማቸት (Abscess)፦ በቶንሲል አካባቢ መግል ተከማችቶ የመተንፈሻ ቱቦን ሊዘጋ ይችላል።

የመተንፈስ መቆራረጥ (Sleep Apnea)፦ በእንቅልፍ ወቅት ትንፋሽ እንዲቆራረጥና ለከፍተኛ ድካም ይዳርጋል።

5. መቼ ነው ሃኪም ጋር መሄድ ያለብን?
ትኩሳቱ ከ 39.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ከሆነ።

ምግብም ሆነ ፈሳሽ መዋጥ ሙሉ በሙሉ ካቃተ።

ህመሙ ከ 2 ቀናት በላይ እየጨመረ ከሄደ።

ማጠቃለያ፦
ቶንሲልን በባህላዊ መንገድ "መቁረጥ" ወይም "መጥረግ" ከፍተኛ የደም መፍሰስና የኢንፌክሽን አደጋ ስለሚኖረው በፍጹም አይመከርም። ይልቁንም ሳይንሳዊ መንገዶችንና የህክምና ባለሙያ ምክርን መከተል ለጤናችን ዋስትና ነው።

ጥያቄ ለእናንተ፦ እናንተ ቶንሲል ሲይዛችሁ በብዛት የምትጠቀሙት የቤት ውስጥ መፍትሄ ምንድነው? በባህላዊ መንገድ የመቁረጥ ልምድ በቤተሰባችሁ አለ? በኮሜንት እንወያይ! 👇

25/04/2026

ነጭ ሳር ሆስፒታል

23/04/2026

ስለ Hepatitis ህክምና ምን ያህል ያውቃሉ⁉️

    እጅግ ዘመናዊ የሆነው የCT-Scan ማሽናችን እድሳቱን ጨርሶ በድጋሚ ስራ የጀመርን መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን። ነጭ ሳር ሆስፒታል አርባምንጭ
22/04/2026




እጅግ ዘመናዊ የሆነው የCT-Scan ማሽናችን እድሳቱን ጨርሶ በድጋሚ ስራ የጀመርን መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን።

ነጭ ሳር ሆስፒታል አርባምንጭ

በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት ከሚያዝያ 15 ጀምሮ በቋሚነት ✔️ Wisdom tooth (impacted tooth) removal or በተፈጥሮ የአበቃቀል ችግር ያለበትን ጥርስ መንቀልና ማስተካከል✔...
21/04/2026

በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት ከሚያዝያ 15 ጀምሮ በቋሚነት
✔️ Wisdom tooth (impacted tooth) removal or በተፈጥሮ የአበቃቀል ችግር ያለበትን ጥርስ መንቀልና ማስተካከል
✔️Facial Nerve palsey management or የፊት መጣመም እና የፊት ነርቭ ችግሮችን ማከም

✔️ Facial trauma management (jaw fractures & injuries) or በአደጋ ምክንያት የተጎዱ የመንጋጋና የፊት አጥንት ሕክምና
✔️ Oral cysts & tumor treatment or ማንኛውም የአፍና የመንጋጋ ውስጥ እባጭ ሕክምና
✔️ TMJ (jaw joint) disorder management or ማንኛውም የመንጋጋ መገጣጠሚያ ችግሮችን ማከም
✔️ Cleft lip & palate surgery or በተፈጥሮ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ማከም
✔️ Infection management & abscess drainage or ማንኛውም የአፍና የመንጋጋ ውስጥ እንፌክሺን ማከም

አገልግሎቶችን በስፋት የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን ።

21/04/2026

ከፍተኛ ድባቴ(Depression) ምንድነው⁉️
゚viralシ ゚

ታላቅ የምስራች በአንጎልና በነርቭ ህመም ለምትሰቃዩ በሙሉ። ከአዲስ አበባ በሚመጡ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ነጭ ሳር ሆስፒታል የአንጎልና ነርቭ ህክምና  መስጠትን አጠናክሮ ጀምሯል። ፦ከአደጋ ...
20/04/2026

ታላቅ የምስራች በአንጎልና በነርቭ ህመም ለምትሰቃዩ በሙሉ።

ከአዲስ አበባ በሚመጡ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ነጭ ሳር ሆስፒታል የአንጎልና ነርቭ ህክምና መስጠትን አጠናክሮ ጀምሯል።

፦ከአደጋ ጋር የተያያዘ የአንጎል ጉዳት ህክምና
፦የእንጎል ውስጥ እጢ ቀዶ ህክምና
፦የስትሮክ ህክምና
፦የሚጥል በሽታ
፦የጀርባ ህመም እንዲሁም ሌሎች ህክምናዎችን ከሚያዝያ 15-18 ይሰጣሉ።

‼️

ታላቅ የምስራች በአንጎልና በነርቭ ህመም ለምትሰቃዩ በሙሉ። ከአዲስ አበባ በሚመጡ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ነጭ ሳር ሆስፒታል የአንጎልና ነርቭ ህክምና  መስጠትን አጠናክሮ ጀምጀምሯል ፦ከአደጋ...
15/04/2026

ታላቅ የምስራች በአንጎልና በነርቭ ህመም ለምትሰቃዩ በሙሉ።

ከአዲስ አበባ በሚመጡ ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ነጭ ሳር ሆስፒታል የአንጎልና ነርቭ ህክምና መስጠትን አጠናክሮ ጀምጀምሯል

፦ከአደጋ ጋር የተያያዘ የአንጎል ጉዳት ህክምና
፦የእንጎል ውስጥ እጢ ቀዶ ህክምና
፦የስትሮክ ህክምና
፦የሚጥል በሽታ
፦የጀርባ ህመም ህክምና እንዲሁም ሌሎች ህክምናዎችን ከሚያዝያ 15-18 ይሰጣሉ።

‼️

Address

Arba Minch'

Telephone

+251930441177

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nech Sar Hospital / ነጭሳር ሆስፒታል አርባምንጭ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category