Amalala Medium Clinic

Amalala Medium Clinic Amalala Medium Clinic offers general medical services run by two general practitioners.

26/02/2022

ባለማወቅ የሠራነውን በደላችንን ይቅር ይበለን
============================
የበሽታዎችን መንስኤ/ምክንያት ሳያውቁ ከጎረቤት ጋር የሚጣሉ ሰዎች ብዙ ናቸው። ከእነዚህ በሽታዎች ቀዳሚው Seizure( እንደሚጥል በሽታ የእጅና የእግር መወራጨት፣ በአፍ አረፋ መደፈቅ፣ አይንን ግልብጥ ማድረግ፣ ራስን መሳት...) ሲሆን መንስኤውን ባለማወቅ ሰዎች ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሲጣሉ አንዳንዴ ደግሞ ሲገዳደሉ ይስተዋላል፤ የቡዳ መንፈስ ነው ወይም ልክፍት ነው ይሉና ከጠረጠሩት ሰው ጋር ይጣላሉ። ነገሩ ግን እንደዚህ አይደለም። ብዙ መንስኤዎች ሲኖሩት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
1. የጭንቅላት ወባና ከሱ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ውስጥ ስኳር መጠን መቀነስ(Hypoglycemia)፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ሙቀት(Hyperpyrexia)( እንደ አካባቢያችን ዋናውና ቀዳሚው)
2. በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የግፊት ህመም( በአንጎል ውስጥ ያሉ ትናንሽ ደም ስሮች ግፊቱን መቋቋም ባለመቻላቸው ሲፈነዱና አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ)
3. ማጅራት ገትርና መሰል የአዕምሮ ኢንፌክሽኖች
4. የአንጎል ዕጢ
5. የኤሌክትሮላይቶች መዛባት( Na+, Ca++)
6. የተለያዩ የጨቅላ ሕፃናት ህመሞች ለምሳሌ፦
6.1 በወሊድ ጊዜ መታፈንና ተያይዞ የሚከሰት የነርቭ ጉዳት
6.2 በሽታን የመከላከል አቅማቸው ስላላደገ ሙሉ አካላቸውን የሚቆጣጠር ኢንፌክሽን( Neonatal Sepsis)
6.2 ከላይ እንደተጠቀሰው የደም ወስጥ ስኳር መቀነስና የኤሌክትሮላይቶች መዛባት
7. የሚጥል በሽታ( Epilepsy)= ምክንያቱ የማይታወቅለትና የነርቭ ሴሎች ከተፈቀደላቸው ፍጥነትና አግባብ የተዛነፈ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው የሚከሰት
8. በአደጋ ጊዜ የሚከሰት የአንጎል ጉዳት( Traumatic Brain Injury)
9. አንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም ወደ አንጎል የሚሄድ የደም ፍሰት መቋረጥ( Stroke)
=> ስለሆነም ከላይ በዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ የተገለጸው ምልክት በታማሚዎች ላይ ሲታዩ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መውስድና ማሳከም የታማሚውን ሕይወት ለመታደግና ባለማወቅ ከጎረቤት ጋር የሚደረግን ጥል ለማስወገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
እንደ አከባቢያችን ብዙ ጊዜ የሚገጥመን በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ሲሆን የመጀመሪያ እርዳታችን እንደሚከተለው ቢሰጥ ሕይወት መታደግ እንችላለን፤
¤ ቀዝቃዛ ውሃ በንጹሕ ጨርቅ አድርገን የታማሚውን ሰውነት በማርጠብ የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር መሞክር(Cold compression)
¤ ልብሶችን ማውለቅ(exposure)
¤ ታማሚወ ራሱን የሚያውቅ(Conscious) ከሆነ ስኳር በጥብጠን ማጠጣት።

10/05/2021

የማይድኑ ህመሞች(የጨመረ የደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ የሚጥል በሽታ፣ የልብ ህመሞች፣ ወዘተ ) በተመለከተ ነጻ ምክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በማንኛውም ሰዓት ከእኛ ዘንድ ማግኘት ይችላሉ።

Address

Selamber
Arba Minch'
SELAMBER/03

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amalala Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram