
10/04/2023
የመንግስት አቅጣጫና ፖሊሲ ተከትለው የሚሰሩ የጤና ልማት ድርጅቶች ሪፖርት አሰጣጥ ላይ የሚሥተዋሉ ጉድለቶች ሊታረሙ እንደሚገባቸዋ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት አስታውቋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት በሶስት ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ይታወቃል ጤና እና ጤና ነክ ችግር ፍቺ ምርምሮች ላይ የሕብረተሰን ጤና አደጋ ክስተቶች መመልከት እንዲሁም ጥራት ያለው የላብራቶሪ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑን መነሻ በማድረግ ተግባራትን በየደረጃው ይገመግማል በዚህ ረገድ መደበኛና በድንገተኛ ወረርሽኞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ተግባራት በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በጋራ ይፈፀማሉ፡፡
ኢኒስቲቲዩቱ ልዩ ትኩረት ያሻቸዋል ቡሎ ካስቀመጣቸው አሳቦች መካከል ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተግባራት፣ የለሽሚያሲስ በሽታ ቅኝት ፣የክትባት ጥራትን በመደበኛው የክትባት አሰጣጥ ትግበራ ማረጋገጥ ፣በተለያዩ ጊዜያቶች እየቀረቡ ያሉ የማጅራት ገትር በሽታን በላብራቶሪ የማረጋገጥ የሚሉት አሳቦች ተካተውበታል፡፡
የመንግስት አቅጣጫና ፖሊሰ ተከትለው የሚሰሩ የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች አንድ ዕቅድ፣ አንድ በጀት ፣እንድ ሪፖርት መርዕ መነሻ በማድረግ በተገቢው ሪፖርት የሚያደርጉ አካላት የመኖራቸውን ያክል በዞኖችና፣ በልዩ ወረዳ ስራዎችን እና በወረዳዎች ጭምር ስራዎች ቢሰሩም በተገቢው ሪፖርት ከማድረግ ረገድ ተግዳሮት መሆኑን አንስቷል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታሪኩ መለሰ ውይይቱን መርተውታል በንግግራቸው በመደበኛና በወረርሽኝ መልኩ ለሚከሰቱ የመከላከልና መቆጣጠር ተግባራትን አጣምሮ የመምራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ተደርጎ ሊወስድ እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ተከትለው እያጋጠሙ ያሉ ሁኔታዎችን አጽንዖት ሰጥቶ መከታተል በተለይም ከኮሌራ በሽታ ጋር በተያያዘ ሊያጋጥሙ የሚጭሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በተገቢው መስራት እንዲሁም የተወሳሰበ የምግብ እጥረትን መነሻ በማድረግ የልየታ ስራዎችን ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ባካሄደው የሳምንታዊ ውይይት ወባን የወባ በሽታን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር የኩፍኝ ወረርሽኝ በሽታ፣የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ ፣የተቅማጥ በሽታ፣የእናቶችና ህጻናት ሞት፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ከፍተኛ የምግብ እጥረት በሽታ፣ የአንትራክስ በሽታ ክስተት፣የወረርሽኝ ክስተቶች የተወሳሰበ የምግብ እጥረት የልየታ ተግበራ፣የእከክ በሽታ የኮሌራ ያሉበትን ሁኔታ ገምግሟል አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል፡
ዕቅድን መነሻ በማድረግ ነባራዊ ሁኔታና ዋና ዋና ጉድለቶች በማመላከት መልኩ በአጭር በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ የሚከናወን ዋና ዋና ጉዳዮችን መሳካት ተግባራት የጋራ ርብርብን ይሻሉ አሳቦች ቀርበዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ