Arbaminch General Hospital

Arbaminch General Hospital ይህ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው!

ክትባቶችንና ቅዝቃዜ የሚያስፈልጋቸው ህይወት አድን መድኃኒቶችን ፈዋሽነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርዓትን መዘርጋት ወሳኝ ነው        ____________የጤና ሚኒስትር ዴኤ...
15/05/2026

ክትባቶችንና ቅዝቃዜ የሚያስፈልጋቸው ህይወት አድን መድኃኒቶችን ፈዋሽነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርዓትን መዘርጋት ወሳኝ ነው
____________

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በሀገር አቀፍ የቀዝቃዛ ሰንሰለት አስተዳደር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደገለጹት ጠንካራ የቀዝቃዛ ሰንሰለት አስተዳደር መዘርጋት ለጤና አገልግሎቱ ጥራት ወሳኝ ነው፤ በዚህም ክትባቶችና መድኃኒቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ተጠብቆ ለታካሚዎች እንዲደርሱ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክትባቶችን ጥራት ለመጠበቅና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ፣ በሁሉም የአቅርቦት ሰንሰለቶች በሶላር ኃይል የሚሰሩ መሣሪያዎችን የማስፋፋት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርዓቱ አስተማማኝ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እደሚገባ ወ/ሮ ፍሬህይት አሳስበዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው አስተዳደሩ የቀዝቃዛ ሰንሰለት መሳሪያዎችን የቅድመና የድህረ ብልሽት ጥገናን በመከታተል ትክክለኛ ክትባት በትክክለኛው ቦታ፣ ጊዜ፣ መጠንና ዓይነት እንዲኖር በማድረግ የጤና አገልግሎቱን ጥራት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ የተጠሪ ተቋማትና የአጋር ድርጀቶች ሪፖርት ቀርበው ልምድና ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ የገለጹት ደግሞ በጤና ሚኒስቴር የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ግብዓት አቅርቦት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ረጋሳ ባይሳ ናቸው፡፡

  የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት።                                 ቀን 05/09/2018 ዓም.            አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል   ከተባለ ዓለም ዓቀፍ ...
13/05/2026

የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት።
ቀን 05/09/2018 ዓም.
አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከተባለ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የማርበርግ ወረርሽኝ ከአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የመከላከል፣ ለይቶ ማከምና የባለሙያዎች የአቅም ግንባታና የለይቶ ማከሚያ ሥፍራዎችን በመገንባት ቀላል የማይባሉ ተግባራትን መፈጸሙ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆስፒታሉ በወረርሽኙ ወቅት ሙሉ ለሙሉ አንዱን የላቦራቶሪ የሥራ ክፍል በመዝጋት ለማርበርግ ምርመራ ብቻ በማድረጉ ምክንያት በተቋሙ የተፈጠረው እጥረት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሟሟላት ስራ በመስራት
#የሲቢሲ እና
#ኬሚስትሪ ማሽን በስጦታ መልክ አበርክተዋል።

ለተደረገላቸው ድጋፍም የሆስፒታላችን ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ ተስፋዬ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በድጋሚ ከልብ እናመሠግናለን 🙏

ከተነጣጠሉ ሲስተሞች ወደ የተዋሃደ የዲጂታል ስነ-ምህዳር፦ በመረጃ ላይ ለተመሰረተ ተገልጋይ ተኮር ክብካቤ!ብሔራዊ የመረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንትNational Data and Digital H...
13/05/2026

ከተነጣጠሉ ሲስተሞች ወደ የተዋሃደ የዲጂታል ስነ-ምህዳር፦ በመረጃ ላይ ለተመሰረተ ተገልጋይ ተኮር ክብካቤ!

ብሔራዊ የመረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት
National Data and Digital Health.

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬዉ ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና ሚኒስቴርን የዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል____________የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬዉ ዕለት ባካሄደው 20ኛ ...
12/05/2026

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬዉ ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና ሚኒስቴርን የዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል
____________

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬዉ ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና ሚኒስቴርን የዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት መድረክ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ስኬታማ ስራዎችን ስለማከናወኑ ተገልጿል።

የማርበርግ ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተሰራው አስደናቂ ሥራ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬታማ አቅም በተግባር ያስመሰከረ መሆኑን የገለጹት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት በበሽታ መከላከል፣ ክትባት ተደራሽነት፣ ወረርሽኝ ቅድመ መከላከልና የምርምር ተግባራትም አበረታች ውጤት ማምጣቱን ገልፀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባለት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ በጤናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን በማብራራት በጤና ተቋማት ያሉ የግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ ከዘርፉ አመራሮችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜጎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ አዳዲስ የጤና ተቋማት ግንባታዎችን ከማካሄድ ጎን ለጎን፣ ነባር የጤና ተቋማት ያላቸውን አቅም የማሳደግና በአስፈጊዉ ግብኣት በማሟላት ደረጃቸውን የማሻሻል ሥራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ዶ/ር መቅደስ የጤናዉ ዘርፍ የሀገር ዉስጥ ምርትን በማሳደግ ከዚህ ቀደም 8 በመቶ ብቻ የነበረዉ የሀገር ዉስጥ የጤና ግብዓት ምርት ወደ 46 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል።

የጤና መሰረተ ልማት ስራዎችን ከማስፋፋት አንጻር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ለአብነትም በመላው ሀገሪቱ ከ600 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና የሚሰጡ ኮምፕርሄንስፍ የጤና ኬላዎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን በማንሳት ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ጤና ተቋማትን በማጠናቀቅ በአስፈላጊዉ ግብአት የማሟላትና ቀልጣፋ የሚሰጡት አገልግሎት ለመስጠት የጤና ድጅታላይዜሽን ስራ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።

ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር ሰፊ የሚድያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች መከናወኑን ያነሱት ሚኒስትሯ የእናቶችና የሕፃናት ሞትን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ የተቻለ ሲሆን፣ በተለይም በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶች ሞት ምጣኔ መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጡ ግቦች አንፃር በአገልግሎት ተደራሽነት፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በተቋማት ግንባታና በአምቡላንስ አገልግሎት እንዲሁም በሰው ኃይል ግንባታ እየተሰሩ ያሉ ስራዎቸ‍ በቀጣይነት ይበልጥ ተጠናክረዉ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

👉ለግንዛቤ ያክል ስለ
12/05/2026

👉ለግንዛቤ ያክል ስለ

በጤና መረጃ እና በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን ማሳደግ!ብሔራዊ የመረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንትNational Data and Digital Heal...
12/05/2026

በጤና መረጃ እና በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን ማሳደግ!

ብሔራዊ የመረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት
National Data and Digital Health Week


5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት መካሄድ ጀመረ___________5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት "በጤና መረጃ እና በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ...
11/05/2026

5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት መካሄድ ጀመረ
___________

5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት "በጤና መረጃ እና በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋትን ማፋጠን" በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል።

መረጃን መሰረት ያደረገ የጤና ስርዓት መገንባት የጤና ስርዓትን የምናሳድግበት ዋነኛው ምሰሶ መሆኑን በመደረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለመስጠት መረጃ መሰረት ነው ብለዋል። ለዚህም የመረጃ ስርዓቱን እስከ ታች ድረስ በመዘርጋት የተቀናጀ እና የተናበበ ስርዓት መዘርጋት መቻሉን አስረድተዋል።

የተቋማት የተገልጋይ መረጃን በአንድ ቋት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ዳባ: ለዚህም በበርካታ ተቋማት ከወረቀት ነፃ የኤሌክትሮኒክ ጤና መረጃ (EMR) አሰራር መተግበር መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመረጃ ስርዓቱን በጤና ዘርፍ ለማዘመን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የጤና መረጃን በካሪኩለም ውስጥ በማካተት ብቁ የሰው ኃይል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል።

በጤናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል የጤና መረጃ እና ዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉቀን አርጋው ሲሆኑ: ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የጤና መረጃ እና ዲጂታል ጤና ሳምንት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ውይይቶች ይደረግብታል ብለዋል።

በመድረኩ በጤናው ዘርፍ የተሻለ የጤና መረጃ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና ዩኒቨርሲቲዎች እውቅና ተሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጄኤስአይ ኢትዮጵያ ተወካዮች ጋር የሀገር ውስጥ የጤና ምርትን መደገፍ እና የጤና ሥርዓት ማሻሻል ዙሪያ ተወያዩ​__________​​በውይይት መድረኩ የጤና ...
08/05/2026

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጄኤስአይ ኢትዮጵያ ተወካዮች ጋር የሀገር ውስጥ የጤና ምርትን መደገፍ እና የጤና ሥርዓት ማሻሻል ዙሪያ ተወያዩ
​__________

​​በውይይት መድረኩ የጤና ዘርፉ የልማት ዕቅድ እና የትብብር መስኮችን ለልዑካን ቡድኑ ያብራሩት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ አሁናዊ የሕክምና አቅርቦት እና የሀገር ውስጥ የጤና ምርት ተግዳሮቶች ላይ ተወያይተዋል።

​በተጨማሪም የጤና ፋይናንስ፣ ዲጂታል ጤና ልማት፣ እና የመድሃኒት አቅርቦት ሥርጭት (last mile delivery) ላይ ​ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በJSI ዓለም አቀፍ ዲቪዥን ም/ል ፕሬዜዳንት ኤድዋርድ ዊልሰን የተመራው የልዑክን ቡድን ​ኢትዮጵያ JSI ከሚሠራባቸው አገራት ሁሉ ትልቋ መሆኗን ገልጸው፣ ውጤታማነትን እና ብቃትን ለመጨመር በጤናው ዘርፍ ቴክኖሎጂን ማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

​ኢትዮጵያ ለመድኃኒት ምርት የቀጠናው ማዕከል መሆን እንደምትችል የገለጹ ሲሆን፣ JSI የመድኃኒት ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማምረት (localization) ሂደት እንደሚደግፍ ገልጿል። ​በዘርፉ ለሚታዩ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች (innovation) ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

Facebook:

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የማርበርግ ክትባት ክሊኒካዊ ፍተሻ በስኬት ተጠናቀቀ_________በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) ...
05/05/2026

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የማርበርግ ክትባት ክሊኒካዊ ፍተሻ በስኬት ተጠናቀቀ
_________

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መከላከያ ክትባት የክሊኒካዊ ፍተሻ በስኬት ተጠናቋል።

የፍተሻውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዛሬው እመርታ ሳይንስን ወደ ተግባር የመለወጥ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

ክልኒካዊ ፍተሻው በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ ውጤታማ ምላሽ የመስጠት አቅምን ያሳየ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ: የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላት ያደረጉት የተቀናጀ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ይህ ክሊኒካዊ ፍተሻ፣ ሀገሪቱ በምርምር ዘርፍ ላደረገችው ኢንቨስትመንት ውጤታማ ማሳያ መሆኑን በመግለጽ: በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) በቅርቡ የተመረቁት ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ለማሳደግ እና ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ዶ/ር መቅደስ የገለፁ ሲሆን፣ ለክልኒካዊ ፍተሻው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው፣ ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ምንም ዓይነት ክትባት ባልነበረበት ሁኔታ ኢንስቲትዩቱ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ፣ሌሎች የጤና አጋር ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሽታው በታወቀ በ24 ቀናት ውስጥ የcAd3 - Marburg Vaccine ክትባት ፍተሻ መጀመሩን አስታውሰዋል።

በዕለቱ የክሊኒካዊ ፍተሻውን አጠቃላይ ሂደት የሚያሳይ ገለጻ የቀረበ ሲሆን፣ ለፍተሻው ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ፕሮግራም ተካሂዷል።

Facebook:

01/05/2026

Address

Gamo Zone
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share